Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Press Releases - County Council

For Immediate Release: Wednesday, August 13, 2025

በአስቸኳይ የሚለቀቅ፦ እሮብ፣ ኦገስት 13 ቀን፣ 2025 .

በሜሪላንድ ጎዳና ላይ ባለው ቡናማ ጣሪያ ስር የተገነባው ተደራሽ የሆነው የሕዝብ መግቢያ

 

ሮክቪል፣ ሜሪላንድ፣ ኦገስት 13 ቀን፣ 2025 . 100 ሜሪላንድ ጎዳና Stella Werner Council Office Building [በስቴላ ዌርነር የካውንስል ቢሮ ሕንፃ] ኦገስት 14 ቀን፣ 2025 . በድጋሚ ይከፈታል። ይህ መግቢያ የሚገኘው በምስራቅ ጄፈርሰን ጎዳና እና በሜሪላንድ ጎዳና መገናኛ አቅራቢያ በሚገኘው ቡናማ ጣሪያ ስር ነው። ይህ የሕዝብ መግቢያ በሁለተኛው ፎቅ ላይ በሚደረገው የሕዝብ መጠቀሚያ ቦታ እድሳት ወቅት የነዋሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ለጊዜው ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውሯል።   

ለህዝብ አጠቃቀም የሚውለው አዲሱ ቦታ ለማህበረሰቡ ዓባላቶች እና ለጎብኚዎች የሚሆን የስብሰባ ቦታዎችን እና ምግብን በሱቅ መልክ ያለ መቀመጫ ቦታ ለደንበኞች የሚሸጡ ሱቆች ይኖሩታል። የምግብ ሻጮቹ ሴፕቴምበር 1 ቀን በይፋ ይከፈታሉ። በተጨማሪም የጸጥታ ምርመራ ጣቢያው በሁለተኛው ፎቅ ላይ እንደገና ተቋቁሟል።

በሜሪላንድ ጎዳና ላይ በሚገኘው ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኙት ደረጃዎች አናት ላይ ያለው ጊዜያዊ የሕዝብ መግቢያ በር ወደ የሠራተኛ መግቢያ በርነት ይመለሳል። ጎብኚዎች በድጋሚ ወደተከፈተው የሕዝብ መግቢያ እንዲሄዱ የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ።   

የምክር ቤቱ ቢሮ ህንፃም ተደራሽ የሆነ የመጀመሪያ ፎቅ የህዝብ መግቢያ አለው። ይሄ የመግቢያ በር የህዝብ መኪና ማቆሚያ ጋራጅ ጎን በአጎራባችነት ይገኛል። የህዝብ መኪና ማቆሚያ ጋርጅ መግቢያ በር በሮክቪል ውስጥ በምስራቅ ጄፈርሰን ጎዳና ላይ ወጣ ብሎ ይገኛል። 

የካውንስሉን ሕንፃ መጎብኘት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የካውንስሉን  ድር ጣቢያ ይጎብኙ።  

# # #

የተለቀቀበት መታወቂያ ቁጥር፦ 25-276
የሚዲያ እውቅያዎች፦ ሶንያ ሄሊ [Sonya Healy] 240-777-7926 ሉሲያ ጀመኔዝ [Lucia Jimenez] 240-777-7832

Release ID: 25-308
Media Contact: Sonya Healy 240-777-7926, Lucia Jimenez 240-777-7832