ውድ ጓደኞቼ
በአሁኑ ጊዜ ሞንትጎመሪ ካውንቲ እንንዲሁም መላው የዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን አካባቢ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት እጥረት እጥረት አደጋ እያጋጠመው ነው። ይህንን ውስብስብ የሆነ ችግር ለመፍታት እና የነዋሪዎቻችንን የጤና እና የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በአስተማማኝ መልኩ መሟላቱን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ የሆነ የአሰራር ዘዴ ልንቀይስ እና ልንተገብር ይገባል።
ይህንንም ለማሳካት ሲባል የካውንቲው ምክር ቤት በቅርቡ ተጨማሪ የመኖሪያ ቤት አይነቶች እንዲገነቡ የሚያደርግ የአከላለል /zoning/ አሰራርን ያጸደቀ ሲሆን በዚህም አማካኝነት የተመረጡ የትራንስፖርት መመላለሻ ኮሪደሮችን አስታኮ ድርብ እና ባለሶስት ተቀጣጣይ ቤቶች፣ ታውንሃውሶች እንዲሁም መጠነኛ/ቀለል ያሉ እና አነስተኛ የፎቅ ቁጥር ያላቸው አፓርትመንት ህንጻዎችን እንዲገነቡ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።
ይህንን አንድሪው ፍሪድሰን እና ናታሊ ፋኒ ጎንዛሌዝ በተባሉት የምክርቤታችን አባላት የሚመራውን እርምጃ አብሬ ስፖንሰር ሳደርግ እኔም ታላቅ ኩራት ይሰማኛል። ከሚገነቡት ቢያንስ 15 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች ለአካባቢው ከተሰላው የገቢ መጠን 120 በመቶ የሚሆን የገቢ መጠን ካላቸው ቤተሰቦች አቅም ጋር በተመጣጠነ መልኩ እንዲመደብላቸው ስለሚያደርግ ይህ እርምጃ በተለይ አብዛኛውን የመካከለኛ ገቢ ያላቸውን ቤተሰቦች/ነዋሪዎቻችንን እና ያአካባባኢያችንን የሰራተኛ ሃይል ያግዛል የሚል እምነት ተጥሎበታል።
ይህ እርምጃ በተጨማሪም የተለያየ የገቢ መጠን ላላቸው ነዋሪዎች አስተማማኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሳደግ፣ ወጪዎችን ለመቀነስ እንዲሁም በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሚገኙ ሰራተኛ ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች የቤት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ መንገዶችን ለማፈላለግ ካውንስሉ እየወሰዳቸው ካሉ እርምጃዎች መካከል አንዱ ነው። ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው የመኖሪያ ቤት አቅርቦት በተለይ በአሁኑ ጊዜ በብዛት እየተፈጠሩ ላሉት እና ተቀጥረው በሚሰሩበት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ኑሮን ለማሸነፍ ፈተና እየገጠማቸው ላሉት ብዙ ቁጥር ያላቸው መምህራን፤ የህዝብ ደህንነት ጥበቃ ኦፊሰሮች እና የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች በተለየ ሁኔታ በጣም አስፈላጊ ነው።
እኔም ከስራ ባልደረባዎቼ እንዲሁም ከማህበረሰባችን አባላት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሬ በመስራት ውስብስብ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት የሚረዱ እና ሁሉም የማህበረሰብ አባላቶቻችን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የመኖር፣ የመስራት እና የመዝናናት በቂ እድል እንዲኖራቸው ለማረጋገጥ የሚረዱ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ እና ለማቅረብ እተጋለሁ።
ከሰላምታ ጋር
ኬት ስቴዋርት
የካውንስሉ ፕሬዚደንት
ባሳለፍኳቸው የሙያዊ/የስራ አመታት ሁሉ ወጣቶች በአካባቢያዊ የመንግስት አስተዳደር ውስጥ በተግባር ገብተው እንዲሰሩ እና እንዲለማመዱ እንዲሁም በህዝባዊ ፖሊሲ አወጣጥ እና ስራዎች ላይም እንዲሳተፉ እና ጠቃሚ የስራ ልምድ እንዲያገኙ ለማስቻል ስቀሰቅስ ኖሬያለሁ። በካውቲው የምክር ቤት አባልነቴ ሳስበው ደግሞ ይህ የተለማማጅ ሰራተኞችን የመቅጠር/ ኢንተርንሺፕ/ አሰራር ለስራ ቡድናችን እራሱ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ እና ለተማሪዎቻችንም በቂ ተግባራዊ ልምድ እንዲያገኙ እና በዛውም ለወደፊት ሌሎች የስራ እድሎችን እንዲያገኙ በር የሚከፍት እና የሙያ ግንኙነቶችንም እንዲያዳብሩ እንደሚረዳ እምነት አለኝ።
የኔ ቢሮም አመቱን ሙሉ በክፍያ የሚሰሩ ተለማማጆችን የሚቀጥር በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች ሁሉ ከመስከረም ወር ጀምሮ እስከ አመቱ መገባደጃ ለሚቆየው የበልግ ወራት የግማሽ አመት የተለማማጅነት ቅጥር እድል እንዲያመለክቱ አበረታታለሁ።
የ2025 የበጋ ወራት ተለማማጆችን/ኢንተርኖችን ይተዋወቁ:
ሜሮን አጋ የኡኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ የቅርብ ምሩቅ ስትሆን በህብረተሰብ/ፓብሊክ ፖሊሲ እና የመንግስት አስተዳደር እንዲሁም ከአለማቀፍ ግንኙነት ላይ ያተኮረ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ጥምር ዲግሪ አግኝታለች ። ሜሮን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ኩሩ ነዋሪ ስትሆን ማህበረሰቦቿንም ቢሮዋንም በተለያዩ ደረጃዎች በማገልገል ላይ ትገኛለች ። ከስራ ሃላፊነቶቿ መካከልም የአካባቢ ተወካይ ነዋሪዎቿን/ኮንስቲቱወንት ማገልገል፣ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አስተዳደር፣ እንዲሁም የማህበረሰብ ተደራሽነት የሚሉት ይገኙበታል። የፖሊሲ ፍላጎቶቿ የሚያተኩሩት ደግሞ በኢሚግሬሽን፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ ትምህርት ላይ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ማኖኔ ጁካም የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ስትሆን ሳመር ራይዝ የተባለው ፕሮግራም ተለማማጅ ሰራተኛ/ኢንተርን/ ነች፤ በዚህም ሚናዋ የማህበረሰብ ተደራሽነትን፣ የማህበረሰብ አባላት አገልግሎት እንዲሁም የአስተዳደር አገልግሎት ስራዎችን ታከናውናለች ። በቅስቀሳ እና በኮምፒዩተር ሳይንስ ላይም እየሰራች ሲሆን እነኚህን ችሎታዎቿን በመጠቀም በቂ ትኩረት ያልተሰጣቸውን የማህበረሰብ አካላት ለመምራት እና ለማሳደግ እና ድምጻቸው እንዲሰማ ለማድረግ ጥረት ታደርጋለች። ማኖኔ ፍትሃዊነት/እኩልነት እና ወጣቶችን ማሳደግ/ማብቃት የሚሉት አላማዎች ላይ ጽኑ አቋም ያላት ሲሆን ፍትሃዊ እና አካታች የሆነ ስርአት እንዲኖርም አስተዋጽኦ ለማድረግ ትጥራለች ።
እነዚህ ሁለት አመርቂ የሆነ ችሎታ ያላቸው ወጣት ሴቶች በኛ ቡድን ውስጥ ተካተው በህዝባዊ ፖሊሲ ትግበራ እና በአካባቢያዊ የመንግስት አስተዳደር ስራዎች ላይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ መመልከት በመቻሌ ላመሰግን እወዳለሁ።
ስለተለማማጅ ተቀጣሪነት ዝርዝር መረጃዎችን እና ስለሚያስፈልጉ መስፈርቶች መረጃ በማግኘት ዛሬውኑ ያመልክቱ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት በቅርቡ የትራምፕ አስተዳደር በወሰዳቸው እርምጃዎች ምክንያት ስራቸውን ያጡ የቀድሞ የፌደራል ተቀጣሪ ሰራተኖችን ለመርዳት በማሰብ በካውንቲው ስራ አቀጣጠር ላይ ለፌደራል ሰራተኞች ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያደርግ ህግ በቅርቡ አሳልፏል። ይህ ህግ የሚሰራው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ የሆኑ እና በታህሳስ 1 እለት ወይንም ከዛ በኋላ የሚሰሩበት የስራ መደብ እንዲወገድ ወይንም የሰው ሃይል ቅነሳ እንዲደረግ በሚል ከስራቸው እንደተቀነሱ የሚገልጽ ማሳወቂያ የደረሳቸው የቀድሞ የፌደራል መንግስት ተቀጣሪዎች ላይ ነው። ይህ እርምጃ ነዋሪዎቻችንን ለማገዝ እና የተፈናቀሉ የቀድሞ የፌዴራል ሰራተኞችን በመንግስት ስራ ላይ እያገለገሉ የመቆየት እድል እንዲያገኙ ለማድረግ የወሰድነው አንዱ እርምጃ ነው። የካውንስሉ ምክትል ፕሬዚደንት ጃዋንዶ የዚህ ህግ ዋናው ስፖንስር ሲሆን እኔም አብሬ ስፖንሰር በማድረጌ ኩራት ይሰማኛል።
የዚህ አመት የበጋ ወቅት ዘጠኝ እጅግ ምርጥ ቀናት አሁን ደርሰዋል። አመታዊው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእርሻ ምርቶች አውደርእይ ከአርብ ነሃሴ 8 እስከ ቅዳሜ ነሃሴ 16 ይካሄዳል። በወቅቱ በሚካሄዱት የካርኒቫል/ሰርከስ/ ጉዞዎች፣ የእንስሣት አውደርእዮች እንዲሁም ለጎብኚ ቤተሰቦች ምግብ እና መዝናኛዎች ስለሚኖሩ መጥተው የዝናኑ። 11 አመት እና ከዛ በታች እድሜ የሆኑ ህጻናት ሁል ቀን በነጻ ይስተናገዳሉ! በተጨማሪም በሞንትጎመሪ ኮሌጅ የነጻ መኪና ማቆሚያ/ ፓርኪንግ ይጠቀሙ _ በሮክቪል እና ጀርመንታውን በሚገኙ ጋራጆች መኪናዎን ማቆም ይችላሉ፤ እንዲሁም አውደርእይ ወደሚካሄዱባቸው ቦታዎች ነጻ የአውቶቡስ/ሻትል/ አገልግሎትም ይቀርባል። የዝግጅቶቹን የፕሮግራም ቅደም ተከተል እዚህ በመመልከት ቲኬትም ይግዙ።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ማህበረሰቦች ማክሰኞ ነሃሴ 5 እለት ብሄራዊ የቤት ውጪ የምሽት መዝናኛ ፕሮግራም ያካሂዳሉ። እነዚህ ነጻ እና ለቤተሰቦች እንዲመቹ ተደርገው የሚዘጋጁ ዝግጅቶች ነዋሪዎችን እና ፖሊሶችን፣ የእሳት አደጋ እና የአደጋ መከላከል እና የፈጣን ምላሽ ሰጭ ሰራተኖች አንድ ላይ በመሆን የሚገናኙበት እና አንድ ላይ የሚዝናኑበት አጋጣሚዎች ናቸው። እባክዎን ከአካባቢዎ ማህበረሰቦች ጋር በመቀላቀል በሚቀርቡት የምግብ ግብዣዎች፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እና በሙዚቃዎች ይዝናኑ፤ በተጨማሪም ታላቅ የሆኑትን የአደጋ ምላሽ ሰጭ ሰራተኖቻችንንም የማግኘት እና የመተዋወቅ እድል አያምልጥዎ።
የሜሪላንድ የኢንሹራንስ አስተዳደር የጤና ሽፋን የእገዛ ቡድን (H-CAT) የሜሪላንድ ነዋሪዎች የጤና ሽፋንን በተመለከተ ያሏቸውን ጥያቄዎች ለመመለስና እና በጤና አቅርቦት ላይም የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶችን በተመለከተ ግንዛቤ በመስጠት እገዛ ይሰጣል። ማንኛውም ግለሰብ፣ ወዳጆች፣ ወይንም በሜሪላንድ የሞኖሩ የነሱ ተወካዮች ይህንን ቡድን በማኘት ጥያቄዎችን መጠየቅ እና ከጤና ኢንሱራንስ አጠቃቀም፣ ከጤና ፕላን ወይንም ከጤና ሽፋን፣ እንዲሁም የእጽ መጠቀም ችግሮችን እና/ ወይንም የአእምሮ ጤናን ጨምሮ ከምንም አይነት የጤና ወይንም የህክምና አገልግሎት እና አቅርቦት ጋር የተታያዘ እገዛ መጠየቅ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ እና የጤና ሽፋን እርዳታ ቡድኑን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።
በበርተንስቪል የሚገኘው የዶሜይን ፊትነስ እና ፐርፎርማንስ ማእከል /Domain Fitness+Performance/
የተካሄደው ምርቃት እና ታላቅ የመክፈቻ ስነስርአት አከባበር ትልቅ ስሜት የሚሰጥ ነበር! የማእከሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች ጄሰን ማስሪ በካውንቲያችን ያደረጉትን ታላቅ ኢንቨስትመንት እና የቅንጅት አስተዋጽኦ ሳላደንቅ አላልፍም። እንዲሁም ሁላችሁም ይህን ድንቅ የሆነ አዲስ ማእከል እንደምትጎበኙት እምነቴ እንደሚሆን ለመግለጽ እወዳለሁ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሙስሊም ፋውንዴሽን የሲኒየሮች ፕሮግራም (MCMF) ያዘጋጀውን የሽርሽር ፕሮግራም ከቤተሰቦች፣ ከጓደኖች እና ጎረቤቶች ጋር በመሆን በማክበራችን ትልቅ እርካታን ፈጥሮልናል! ፕሮግራሙ በተለያዩ ትውልድ/የእድሜ ክልልባሉ ሰዎች መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር የሚያደርግ ሲሆን በዚህ ሁኔታም እድሜያቸው የገፋ አዋቂ ሰዎች፣ የነሱ የልጅ ልጆች እና የቤተሰብ አባላት አንድ ቀን አብረው በመዋል ምግብ በመመገብ እና የተለያዩ መዝናኛዎችን በመጫወት እንዲሁም እርስ በርሳቸው ቁርኝትን በመፍጠር ጥሩ ጊዜ ያሳልፋሉ። በፕሮግራሙ ላይ የስቴት እና የካውንቲ አጋሮቻችን የሆኑት የስቴት ተወካይ ፓቭሎቪች ካር፣ የስቴት ተወካይ ዊምስ፣ የስቴት ተወካይ ዎሌክ፣ የካውንቲው ስራ አስፈጻሚ ኢርሊች፣ የምክርቤት አባል ባልኮምብ እና ሌሎችም ከኛ ጋር አብረው ተሳትፈዋል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ከሚገኙ በጣም ግዙፍ ከሚባሉ የስነባህሪ ጤና አገልግሎት ሰጪ ማእከላት አንዱ እንደመሆኑ መጠን ኮርነርስቶን ሞንትጎመሪ በከባድ የአእምሮ ጤና ችግር ለሚሰቃዩ እና በእጽ ሱስ ለተጎዱ ሰዎች ለ50 አመት ያህል አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ማህበረሰብን መሰረት ባደረጉ የህክምና፣ የመልሶ ማቋቋም፣ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና የተለያዩ የሙያ ነክ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ኮርነርስቶን ወጣቶችን፣ አዋቂዎችን እንዲሁም ወደ እድሜ ባለጸጋነት የተሸጋገሩ ሰዎችን ጨምሮ በየአመቱ ከ3000 በላይ ለሚሆኑ የሜሪላንድ ነዋሪዎች ግልጋሎት ይሰጣል። አሁን ስላሉ ክፍት ቦታዎች ለማወቅ እዚህ ላይ ይጫኑ በተጨማሪም አጭር የማስተዋወቂያ ቪዲዮ እዚህ ይመልከቱ።
ክሪኤት ካልም Create Calm የተባለው በመረጃ ላይ በተመሰረተ የቴራፒ/ህክምና እንዲሁም ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ትምህርትን በመጠቀም የስነባህሪ እገዛ ለማይደርሳቸው ህጻናት፣ ታዳጊዎች እና የወጣት አዋቂዎች ያለፈ ጉዳትን ያገናዘቡ፣ ከእድሜ/አእምሮ እድገት ደረጃ ጋር የሚጣጣሙ የእንቅስቃሴ እና የአስተዋይነት አገልግሎቶችን የሚያቀርብ ፕሮግራም ነው። “ክሪኤት ካልም እክሴል ቢዮንድ ዘ ፔል” ከተባለው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የስነባህሪ እና አካላዊ ጤና እገዛን ለታይትል አንድ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት በቀጥታ ያቀርባል። ከትምህርት ሰአቶች ውጭ የሚተገበሩ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ህጻናት የማይቋረጡ እና ፍቅርን የተላበሱ የስሜት ማረጋጊያ፣ የሰውነት አካላት ምንነት ግንዛቤ ማዳበሪያ እና አካዳሚያዊ እና ግላዊስኬትን ሊያሳድጉ የሚችሉ የጽናት ማጠናከሪያ ዘዴዎችን እንዲማሩ ይደረጋል። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ያገኛሉ.