Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - Aug. 20, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቻችን፣

በዲሲ ውስጥ የአደገኛ ወንጀሎች ቁጥር በ30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም የወንጀል ስጋቶችን በሚል ምክንያት ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንቱ እና አስተዳደራቸው የፌዴራል መንግስት የሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ እና የዋሽንግተን ዲሲ ብሔራዊ ጥበቃን እንዲያስተዳድር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይህ አስደንጋጭ እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀው የትራምፕ አስተዳደር የውሳኔ እርምጃ መጠነ ሰፊ ተፅዕኖ የሚያመጣ ሲሆን፣ በሀገራችን ዋና ከተማ ላይ የሚከሰተው ነገር በሞንጎመሪ ካውንቲ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር እናውቃለን።

በአጎራባች ግዛቶች ላይ ዲሲ በፌደራል ስር መሆንዎ የሚያሳድረው ሙሉ ተፅእኖ እስካሁን በእርግጠኝነት አይታወቅም። እዚህ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የአካባቢውን ነዋሪዎችና የንግድ ድርጅቶች ለመደገፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። 

ICE በድንገት ወደ መሥሪያ ቤታቸው ቢመጣ ሰራተኞቻቸውን እንዴት መጠበቅ እና ማዘጋጀት እንደሚችሉ ለማሳወቅ በቅርቡ ከ100 በላይ ከሚሆኑ የበጎ ፈቃደኛ ድርጅቶች ጋር በመሆን በአካባቢው ከሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ጋር መረጃ ለማካፈል ወደ CASA ተቀላቅያለሁ። የካውንቲው ኤጀንሲዎች እንደ የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ እና የምግብ ግብዓቶች ያሉ የማህበራዊ ደህንነት መረብ አገልግሎቶችን ለሚፈልጉ ለሰዎች ቁጥር ጭማሪ ለመዘጋጀት ከአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በጋራ እየሰሩ ነው።

ማህበረሰባችን ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ እንዲቆይ በኢንቨስትመንቶች እና ስትራቴጂዎች ላይ በማተኮር በዲሲ ውስጥ አብረውን ለሚኖሩት ጎረቤቶቻችን መሟገታችችን እንቀጥላለን።

ከአክብሮት ጋር፣

ኬት ስቲዋርት

የካውንስሉ ፕሬዝደንት

ወደ መሰረታዊ ትምህርት መመለስ

የአዲሱ የትምህርት አመት መጀመሪያ እየተቃረበ ነው!

የ2025-2026 የትምህርት አመትን ለማስጀመር ቤተሰቦች ቅዳሜ ነሃሴ 23 ከ10 ኤ ኤም እስከ 1 ፔ ኤም በዌስትፌልድ ዊተን በሚካሄደው በአመታዊው ኤምሲፒኤስ ወደ ትምህርት ተመልሶ የመምጣት ኤግዚቢሽን /MCPS Back-to-School Fair at Westfield Wheaton ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል። በእለቱ በሚካሄደው ስነስርት ለሁሉም ቤተሰቦች በነጻ የሚታደሉ ቁሳቁሶች፤ ሌሎች ስጦታዎች እና የነጻ የክትባት መስጫ ክሊኒክ እንዲሁም የተለያዩ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ ይምጡና ይታደሙ።

ከዚህም በተጨማሪ ከፕሪ ኬ ደረጃ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት እድሜ ክልል ላሉ ልጆች በካውንቲው በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ከአሁን ጀምሮ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ የሚሰጡትን ነጻ ወደ ትምህርት መመለሻ ክትባቶች /free back-to-school vaccinations/ መውሰድ ይቻላል።

ከዚህም በላይ የኤምሲፒኤስ ጊቭ ባክፓችክስ ዘመቻ /MCPS GIVE BACKpacks campaign/ ላይ በመሳተፍ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በትምህርታቸው ስኬትን እንዲያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይችላሉ። ወደ 70,000  የኤምሲፒኤስ ተማሪዎች በድህነት በሚኖሩበት በአሁኑ ጊዜ በተለይ ለተማሪዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ እና ተማሪዎችም የትምህርት አመቱን በጠነከረ ሁኔታ እንዲጀምሩ በማስቻል ረገድ የርስዎ እገዛ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

የኤምሲፒኤስ/MCPS/ ወደ ትምህርት የመመለስ ኤግዚቢሽን። ቀኑን መዝግበው ይያዙ!

የዩኒቨርሲቲ ቡልቫርድ የኮርነር ፕላን የህዝብ ችሎት

ካውንስሉ የዩኒቨርሲቲ ቡልቫርድ ኮሪዶር /University Boulevard Corridor (UBC)/ ፕላንን በመጭው የበልግ ግዜ አንስቶ የሞወያይ ሲሆን በዚህም ችሎት በተለይ በ I-495 አውራ ጎዳና እና በ ዊትን መካከል በሚገኘው ሶስት ማይል የሚሆነውን የዩኒቨርሲቲ ቡልቫርድ መንገድ  ባስታከከ መልኩ የትራፊክ ደህንነት፣ የአካባቢያዊ መስመር ግንኙነቶች፣ የአካባቢ አየር ጥበቃ ዘላቂነት፣ በኮሪደር ላይ ያተኮረ እድገት እና አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገትን በተመለከቱ ርእሶች ላይ ይወያያል።  እሮብ መስከረም 10 በ 7 ፒ ኤም  በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ማክሰኞ መስከረም 16 በ 7 ፒ ኤም  ሮክቪል በሚገኘው የካውንስሉ ጽህፈት ቤት ህንጻ ላይ የህዝብ ችሎት/ ውይይት እናካሂዳለን። የማህበረሰብ አባላት በቅርብ በሚካሄዱት የህዝብ ችሎቶች ላይ ሃሳባቸውን እንዲሰጡ ወይንም ወደካውንስሉ በመደወል/በማግኘት እንዲሳተፉ እናበረታታለን።

ከህዝብ ችሎት ውይይቱ በኋላ በእቅድ ማውጣት፣ በመኖሪያ ቤት ጉዳይ አና በፓርኮች ኮሚቴዎች በሚደረጉ በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው ስብሰባዎችንና የስራ ክፍለጊዜዎችን በማካሄድ በመጨረሻም ለሙሉ የካውንስሉ አባላት የሚጠቅሙ ምክሮች እና ሃሳቦች እንዲሰባሰቡ ይደረጋል።

በዉድሞንት የገበያ ማእከል ያለ የመንገድ መጋጠሚያ። ፎቶ: ሞንትጎመሪ ፕላኒንግ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኑዛዜ እና ውርስ መዝገብ ሹም የነበረውን የተከበሩየጆሴፍ ኤም ግሪፍን ህልፈት በማስመልከት ሞንትጎመሪ ካውንቲ ሃዘኑን ይገልጻል።

ከመላው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጋር በመሆን የተከበሩ ጆሴፍ ኤም ግሪፍን ህልፈት በማስመልከት ሃዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ። ሚስተር ግሪፍን በሞንትጎመሪ ካውንቲ የውርስ እና የኑዛዜ ሹምነት ለሰባት ጊዜ በመመረጥ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የስራ አፈጻጸም ሪኮርድ ያስመዘገበ በጣም ጽኑ እና ተአማኒነት ያለው የህዝብ አገልጋይ ነበር። በስራ ጓደኖቹ እና እኩዮቹ እንዲሁም በሚያውቁት ሁሉ በጣም የተከበረ ሰው ነበረ። ጆ በሞንትጎመሪ ካውንቲ እድሜውን ሙሉ የኖረ ሲሆን ሙሉ ግላዊ እና ሙያዊ ህይወቱን ለሚወደው ማህበረሰቡ በመስጠት አገልግሏል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ እና ለሜሪላንድ እስቴት የሰጠውን የህይወት ዘመን  አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ በማክበር ለቤተሰቡ እና ለሚወዱት ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

የሚስተር ግሪፍን ጉርድ ፎቶ

ፓርከር የተባለውን የሴኩሪቲ ሮቦት ይተዋወቁ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት መምሪያ (MCDOT) ፓርከር የተባለውን የሴኩሪቲ ሮቦት በመጭዎቹ ሳምንታት ለሲልቨር ስፕሪንግ ማህበረሰቦች በማስተዋወቅ ለሙከራ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ሊሆን የሚችል የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ በመሞከር ላይ ይገኛል።  ይህ 360 ዲግሪ የሚያይ ካሜራ የተገጠመለት ተንቀሳቃሽ ሮቦት የህዝብ ደህንነትን ለማጠናከር ለታለመ የሙከራ ፕሮግራም ይረዳ ታስቦ በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው የታውንስኩዌር የመኪና ማቆሚያ ጋራጅ አካባቢ እንቅስቃሴ ሊያደርግ ይችላል። እኔም የሙከራ /ፓይለት/ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት ለትንሽ ጊዜ እንዲቆም እና መንግስትም ማህበረሰቡ የሚሳተፍበትን ፕሮግራም እንዲያዘጋጅና ሃሳቦችንም እንዲሰበስብ እንዲሁም በተለይ በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ አካባቢ በአማርኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች መረጃ እንዲሰራጭ ጠይቄ ነበር። በመሆኑም ስለፕሮግራሙ፣ ወጪው እና ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት መምሪያ የአፈጻጸም ፕላን ለማወቅ በማሰብ ካውንስሉ በሃምሌ 29 የግንዛቤ መውሰጃ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። ሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርርት ቢሮ የፓይለት ፕሮግራሙን በተመለከተ የህዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ይረዳው ዘንድ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራትም ማህበረሰቡን ለማነጋገር የሚረዱ ዝግጅቶችን ያካሂዳል።

Knightscope K5 Autonomous Security Robot. Credit: Knightscope.

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ

ብሄራዊ ከቤት ውጭ ምሽት የማሳለፍ ፕሮግራም

ዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግን፣ታኮማ ፓርክን፣ ሊትንስቪልን እና ኬንሲንግተንን ጨምሮ በመላ ዲስትሪክቱ በተካሄዱ ከቤት ውጭ ምሽትን የማሳለፍ ብሄራዊ ፕሮግራሞች ላይ በጣም ብዙ ጓደኞቼን እና ጎረቤቶችን ተሳትፈው በማየታችን ተደስተናል። ይህ  የማህበረሰብ መገምቢያ ፕሮግራም በጎረቤቶቻችን እና በፖሊስ አባላት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በማገዝ ካውንቲያችን ለመኖር፣ ለመስራት እና ለመዝናናት በሚመች መልኩ ደህንነቱ  የተጠበቀ እንዲሆን ያግዛል።  ይህ ታላቅ ክስተት በየአመቱ በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋጅ የሚያግዙትን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ መምሪያ፣ የህዝብ ደህንነት ባለሞያዎቻችንን እንዲሁም ሌሎች  ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የማህበረሰባችን አባላትን ማመስገን እንወዳለን።

ብሄራዊ ከቤት ውጭ ምሽት የማሳለፍ ፕሮግራም

በፐርፕል ላይን የባቡር መንገድ ላይ የሚገኙ የአነስተኛ የንግድ ተቋማትእና ደህንነታቸው

ቢሮአችን በፐርፕል ላይን የባቡር መንገድ ግምባታ ምክንያት ተጽእኖ ከደረሰባቸው ነዋሪዎች እና የአካባቢ የንግድ ተቋማት ጎን መቆም እና አብሮአቸውም መስራቱን ይቀጥላል። በመካሄድ ላይ የሚገኘው የፐርፕል ላይን የባቡር መንገድ ግንባታ በፐርፕል ላይን ኮሪደር ላይ በሚገኙ የንግድ ተቋማት እና ነዋሪዎችን ላይ ተጸኖ እንዳሳደረ ይታወቃል።

የሜሪላንድ ስቴት ተወካይ አባል ሎሪግ ቻርኩዲያን፣ የአካባቢያዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄከብ ኒውማን እንዲሁም የድንገተኛ ማስተባበሪያ እና የአገር ውስጥ የደህንነት ቢሮን  በሃምሌ 25 እለት በፐርፕልላይን ግምባታ ላይ በደረሰ የውሃ መስመር መፈንዳት ምክንያት  የተፈቀናቀሉ ነዋሪዎቻችንን በማገዛቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ሃያ የሚሆኑ ቤተሰቦች የተፈናቀሉ ሲሆን የተወሰኑ የአካባቢያችንን ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ከካውንቲው ጋር በመሆን እነኚህን የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ለማገዝ በዚህ ረገድ ላደረጉት ጥረትም ላመሰግናቸው እወዳለሁ። የሞንትጎመሪ የመኖሪያ ቤት ግምባታ ጥምረት / Montgomery Housing Partnership (MHP/ ከዚህ ጋ በተያያዘ እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል ድረገጽ አዘጋጅቷል

እኔም ባለፈው ሳምንት ከሜሪላንድ የትራንስፖርት ቢሮ ከአስተዳዳሪዋ ከሆሊ አርኖልድ ፣ ከፐርፕል ላይን ተወካዮች እንዲሁም ከንግድ ተቋማት ባለቤቶች እና ነዋሪዎች ጋር በሎንግ ብራንች አካባቢ ተገናኝተን የግምባታው የስራ ሂደት የት እንደደረሰ ለማወቅ፣ ግምባታው የአካባቢውን የንግድ ተቋማት እና ነዋሪዎች ላይ እንዴት ተጽእኖ እያደረገ እንዳለ፣ እንዲሁም እነኚህን በጎ ያልሆኑ ተጽእኖዎች ለማስወገድ ምን አይነት ለውጦችን ማድረግ እንደሚቻል ከአስተዳዳሪው አርኖልድ ለመስማት ጥረት አድርጌያለሁ።

ከዚህ በተጨማሪም የሜሪላንድ የትራንስፖርት መምሪያ የአነስተኛ ንግድ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ፖግራም ተጽእኖ ለደረሰባቸው ንግድ ተቋማት የሁለት ዙር የገንዘብ ድጎማ አድርጓል። ለሰስተኛ ዙር የገንዘብ ድጎማ ማመልከቻ ለማስገባት ከጥቅምት 6 2025 ጀምሮ ክፍት ይሆናል። የኛ ቢሮ ከካውንቲው ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ከዲስትሪክት 16፣ 18 እና 20 ተወካዮች ጋር አብሮ በመሆን በዛ ያሉት የንግድ ተቋማቶቻችን ለገንዘብ ድጋፉ ብቁ እንዲሆኑ በሚያደርግ መልኩ በገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለትራንስፖርት ዋና ጸሃፊ ዊድፊልድ ልከናል።

በነሃሴ 8 ከፐርፕል ላይን ትራንዚት ፓርትነርስ ኩባንያ፣ ከፕሪንስ ጆርግስ ካውንቲ የካውንስል አባል ዋኒካ ፊሸር እንዲሁም ከመንገድ ደህንነት ተሟጋቾች  ጋር አብሬ በመሆን ሻይን ኤንድ ራይድ /“Shine and Ride”/ የተባለውን የቅስቀሳ ዘመቻ አብስሬያለሁ። ይህ የቅስቀሳ ዘመቻ በፐርፕል ላይን ኮሪደር ላይ የሚጓጓዙ እግረኞችን እና የብስክሌተኞችን ደህንነት ፤ በተለይም የተማሪዎችንና የወጣቶችን ደህንነት ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች እና እርምጃዎች አካል ነው።.

Purple Line tour.

የእርሻ ፋይር ማሳያ ኤግዚቢሽን

በአመታዊው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእርሻ ኤግዚቢሽን ማሳያ እና ምሳ ግብዣ ስነስርአት ላይ ተገኝቼ ጥሩ ጊዜ አሳልፌያለሁ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የ እርሻ ማእከል እርሻን በካውንቲው ውስጥ ጠብቆ በማቆየት፣ ህዝቡን በማስተማር እንዲሁም በእርሻ ለሚተዳደሩም ሆነ የእርሻ ሙያ ስራቸው ላልሆነ የህብረተሰብ አካላት ትምህርት የመስጠት ትልቅ ሚና ይጫወታል። የእርሻ ማእከሉን እያመሰገንኩ አባላቶቹ እና የበጎ ፈቃድ ሰራተኞቹም በበኩላቸው  የማህበረሰቡ አባላት እርሻ በህይወታቸው ላይ የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና እንዲረዱ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል። 

Ag fair

በሆሊ ክሮስ ማእከል የፕራይመሪ ኬር ኮአሊሽን /Primary Care Coalition/ ጉብኝት

በቅርቡ የ Primary Care Coalition ከተባለው የመሰረታዊ የጤና ጥምረት ጋር አብሬ በመሆን በሲልቨር ስፕሪንግ የሚገነውን የሆሊ ክሮስ ማእከል ጎብኝተናል። ሆሊ ክሮስ ሰዎች Montgomery Cares በተባለው የጤና አገልግሎት መስጫ ፕሮግራም አማካኝነት ለመገናኘት እና አገልግሎቶችን መላግኘት ከሚችሉባቸው ክሊኒኦች መካከል አንዱ ነው። ሞንትጎመሪ ኬርስ የሚባለው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለሚኖሩ በአዋቂ እድሜ ላይ ያሉ እና የጤና ኢንሹራንች ለሌላቸው እና ለአገልግሎቱ ብቁ ለሆኑ ግለሰቦች የጤና እንክብካቤ የሚሰጥ በመሆኑ አገልግሎቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጠቃሚ ሆኗል። በአቅራቢያዎ ክሊኒክ ለማግኘት ይህን Find a clinic near you ይጫኑ።

በሆሊ ክሮስ ማእከል የፕራይመሪ ኬር ኮአሊሽን /Primary Care Coalition/ ጉብኝት

የአእምሮ ጤና ኮርነር

የአዲስ ጅማሮ አጋዥ ቡድን /New Beginnings Support Group/

አዲስ ጅማሮ ወይንም ኒው ቢጊኒንግስ የሚባለው በ ዲ ሲ ሜትሮ አካባቢ ለሚኖሩ እና በትዳር መለያየት እና ፍቺ ምክንያት ኑሮአቸው ለተቃወሰባቸው ሰዎች እገዛ እያደረገ የሚገኝ ብቸኛው ቡድን ሲሆን አገልግሎቱንም የሚሰጠው ልጆች ይኑራቸው ወይንም አይኑራቸው ለማንኛውም ግለሰብ ክፍት ነው። ድርጅቱ በየአባላቱ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተለያዩ ውይይቶች እንዲደረጉ የሚያመቻች ከመሆኑም በላይ በባለሞያዎች የሚደረጉ ንግግሮችን እና ልዮ የግንዛቤ መፍጠሪያ ማህበራዊ ዝግጅቶችንም ያዘጋጃል። ኒው ቢጊኒንግስ በአመት ሁለት ጊዜ ለስድስት ስድስት ሳምንታት የሚቆዩ የህዝብ ማስተማሪያ ዝግጅቶችን በማድረግ በነዚህ ስብሰባዎች ላይ ዲቮርስ 101 / Divorce 101/ የተባለው እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያሉትን 13 በጣም ከፍተኛ የቤተሰብ ህግ ባለሞያኦችን በመጠቀም በሜሪላንድ ውስጥ ፍቺን በተመለከተ መጠነ ሰፊ የሆን ገለጻ ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ Learn more

በቅርብ የሚዘጋጁ የኤቭሪማይንድ/EveryMind/ስልጠናዎች

ኤቭሪማይንድ የአእምሮ ጤና ስልጠናዎችን እና የኢንተርኔት ሴሚናሮችን/ ዌቢናሮችን/ እንደሚሰጥ ያውቁ ነሯል? ነጻ የአእምሮ ጤና ስልጠና ለማግኘት እና መረጃውንም ለሌሎች ለማሰራጨት ይችሉ ዘንድ  ይመዝገቡ። ለአገልግሎት ሰጬ ሰራተኛ፣ ለማህበረሰብ መሪዎች ወይንም ለወጣት መብት ተሟጋችም ሆነ ለሌሎች እነኚህ ስልጠናዎች በጣም አጋዥ እና በአእምሮ ኤና የዳበረ ማህበረሰብን ለመገንባት የሚረዱ ናቸው። በቅርብ ስለሚካሄዱ ፕሮግራሞች በበለጠ ለማወቅ እና ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

“የአእምሮ ጤና ጉዳዮች” የሚል በስክሪኑ ላይ የተጻፈበት አይፓድ