Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - Nov. 26, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቼ

በሚቀጥለው ሳምንት የምክር ቤቱ ፕሬዚደንትነት የስራ ጊዜዬን የማገባድድ ሲሆን ካውንስሉም አዲስ አመራሩን ለመምረጥ ድምጽ የሚሰጥ ይሆናል። በዚህ አመት ባስገኘናቸው ከፍተኛ መጠን ያላቸው የስራ ውጤቶች ኩራት እንደሚሰማኝ እየገለጽኩ እነኚህንም ስኬቶች ለማስመዝገብ የቻልነው የሚገጥሙንን ተግዳሮቶችን በማሸነፍ እና በትራምፕ አስተዳደር አማካኝነት በማህበረሰቦቻችን ላይ የሚደርሰውንም ጉዳት ለመቀነስ በመስራት መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ።

ቤኔ አመራር ሰጪነት ምክር ቤቱ በዚህ የፌደራል መንግስት አስተዳደር የጥቃት ኢላማ የተደረጉ የማህበረሰብ አባሎቻችንን ለመርዳት እና ለመጠበቅ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል። ከስቴት እና ከፌደራል አጋሮቻችን ጋር አንድ ላይ ተጣምረን በመስራት ደሞክራሲያዊ እሴቶቻችንን ለማስጠበቅ እንዲሁም ከነዋሪዎቻችን ጋር በአንድነት በመሆን ለጎረቤቶቻችን መብት እና በአጠቃላይም ለህገመንግስታዊ መብቶቻችን መከበር ዘብ ቆመናል።

አስቸጋሪ የሆነ የኢኮኖሚ አውድ በገጠመን ሁኔታም ቢሆን የግብር ተመን ደረጃን ሳንጨምር ጠንካራ የሆነ ባጀት ማጽደቅ ከመቻላችንም በላይ የካውንቲያችንን የቆየ የትሪፕል ኤ ቦንድ ሬቲንግ /ደረጃ/ ጠብቀን ማቆየት ችለናል። ለነዋሪዎቻችንን እና ለንግዱ  ህብረተሰባችንም የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት የቻልን ሲሆን በተጓዳኝም እንግዳ ተቀባይ እና ሁሉን አቃፊ የሆነ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንንም ላማስጠበቅ ችለናል።

ያለፈውን አመት ግምገማ እዚህ በመጫን ይመልከቱ

አብረን ካስገኘናቸው መሻሻሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ  የሚከተሉት ናቸው

ለፌደራሉ መንግስት አስተዳደር ያደረግነው ምላሽ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኝ ሁሉም ሰው መሰረታዊ ፍላጎት እንዲሟላ እና መብቱም እንዲረጋገጥ አመቱን ሙሉ ሁላችንም በአንድ ላይ በመሆን አገለግሎት እና እገዛ ለነዋሪዎቻችን ስንሰጥ ቆይተናል።

የእኔ የስራ ቡድንም ‘ለአገልግሎት እና እገዛ እንተባበር የማህበረሰብ ሃብት’ / United in Service and Support Community Resource Fair / የተባለውን ኤግዚቢሽን በመምራት እና በማዘጋጀት የተሳተፈ ሲሆን በፌደራል ደረጃ በተወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት እና በጅምላ የስራ ቅነሳ እርምጃዎች ምክንያት የተጎዱ ቤተሰቦችን እና ሰራተኞችን ለማገዝ 12 ክፍል ያለው የዌቢናር /በኢንተርኔት መረብ የሚካሄድ/ ውይይትም አካሂደናል።

የፌደራል ሰራተኞችን ለማገዝ ከወርክ ሶርስ ሞንትጎመሪ ጋር በቅንጅት የተፈጠረውን እና በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የተፈናቀሉ የፌደራል ሰራተኞችን ለማገዝ የተደራጀውን የሞንትጎመሪ ፌዴራል ተቀጣሪዎች ማደራጃ እና የስራ ማፈላለጊያ ማእከልን /Mobilize Montgomery Federal Workforce Career Center/ የማስተዋወቅ እና የማጠናከር ስራ ስንሰራ ቆይተናል።

በተጨማሪም ካውንስሉ የ7.75 ሚሊዮን ዶላር የፓብሊክ ሰርቪስ እገዛ ድንጋጌን በማጽደቁም ኩራት ተሰምቶኛል። ይህ የፋይናንስ እደላ ፓኬጅ አሁን እየቀጠለ ባለው የፌዴራል መንግስት መዘጋት እና የፌደራል አስተዳደር ፖሊሲዎች ምክንያት ለተጎዱ ነዋሪዎች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የበለጠ ድጋፍ ይሰጣል ብለን እናምናለን።  

በጣም አስፈላጊ በሆኑ የማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች

በዚህ አመት ከሰራኋቸው ስራዎች መካከል በአብይነት የሚጠቀሰው የካውንስል ፕሬዚደንቷ የአእምሮ ጤና ኢኒሽየቲቭ ወይንም ፕሮግራም ነው። ከዚህ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ በመቶዎች ከሚቆጠሩ የህክምና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ስብሰባዎችን ያደረግን ሲሆን ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ቡድኖች እና ድርጅቶች ጋርም በመገናኘት የአእምሮ ጤና እንክብካቤ አሰጣጥን ለማሳደግ ጥረት አድርገናል። ብዛት ካላቸው ወጣት ቡድኖች እና ተማሪዎች ጋር በመገናኘት የወጣቶችን የአእምሮ ጤና ፍላጎት ማሟላት የሚቻልበትን መንገድ በበለጠ ለመረዳት ጥረት አድርገናል።

በዚህ አመት ባጀታችን ላይ ለማህበራዊ ሴፍቲ ኔት ፕሮግራሞች ለሚውሉ ሃብቶች ቅድሚያ ሰጥተናል። ፕሮግረስ ፕሌስ በሚባለው መጠለያ ለሚሰሩ የፖሊስ መኮንኖች በጀት በመመደብ የመኖሪያ ቤት አልባነት ችግር የገጠማቸው ግለሰቦችን ደህንነት የሚያረጋግጡ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩም ግፊት አድርገናል። የስነባህሪ ጤና እና የአደጋ ዝግጁነት አገልግሎቶችንም በጀት ያሳደግን ሲሆን የዚህ አላማም የአእምሮ ጤናን ለማሳደግ እና ለህጻናት፣ ለወጣቶች እና ለቤተሰቦች እንዲሁም ለአዋቂዎች እና የስነባህሪ ችግር ላለባቸው የእድሜ ባለጸጎች የተሟላ የህክምና አገልግሎት እና ተደራሽነት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው።

የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው ፕላስ ማህበረሰብ አባላትን ለማገልገል ተብሎ በካውንቲው በሚገኝ ስፍራ የተቋቋመው እና በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕራይድ ማእከልን /MoCo Pride Center/ ታሪካዊ የመክፈቻ ስነስርአት አክብረናል። የኔ ቡድንም በተጨማሪ የባኬትስ ኤንድ ቢትስ የወጣቶች ብሎክ ፓርቲን በማዘጋጀት እና በማህበረሰቡ ውስጥ የተከሄዱንም ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሌሎች ዝግጅቶችንም ለማካሄድ ድጋፍ ሰጥተናል።

የካውንቲው አመራሮች በሞኮ ፕራይድ ማእከል መክፈቻ ላይ የሮዝ ቀለም ያለው ሪባን ሲቆርጡ የሚያሳይ

ቅድመ የህጻናት እንክብካቤ እና ትምህርት

ለትርፍ ያልርውቋቋሙ ድርጅቶች እና ለህጻናት እንክብካቤ ሰጪዎች ቅናሽ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ክፍያ መጠን እንዲሁም ለህጻናት እንክብካቤ ሰጪዎች የተሻሻለ የንብረት የግብር ክሬዲት የሚያሰጥ አዋጅም አጽድቀናል። የ7.6 ቢሊዮን ዶላር በጀታችን በአይነቱ እስካሁን ድረስ ትልቅ የሚባል $3.6 ቢሊዮን ለህዝብ ትምህርት ቤቶች የተመደበ በጀት እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ባጀትን ሙሉ በሚባል ደረጃ ለመሸፈን የሚያስችል የ345 ሚሊዮን ዶላር ድጎማ የሚጨምር ነበር።

የካውንስሉ ፕሬዚደንት ስቴዋርት ከካውንቲው አመራር እና ከተማሪዎች ጋር በትምህርት ክፍል ውስጥ አንድ ላይ ሆነው የሚያሳይ

የአየር ንብረት፣ መሰረተ ልማት እና የመኖርያ ቤት

በዚህ አመት ደህንነቱ እና ቀጣይነቱ የተረጋገጠ የወደፊት እጣችንን የሚያጠናክሩ የመሰረተ ልማት፣ የመኖሪያ ቤት እና የአየር ንብረት ፕሮግራሞችን ስናስፈጽም ቆይተናል። የ ራይድ ኦን የህዝብ መመላለሻ አውቶቡሶች ለሁሉም ተጠቃሚዎች በነጻ እንዲያገለግሉ በማድረግ የአውቶቡስ አጠቃቀምን ማስፋፋት እና የአየር ንብረት ጥበቃችንንም ማጠናከር ችለናል። በኔ አመራር ሰጭነት ካውንስሉ ሰዎች  በተደጋጋሚ ለመጠቀም የሚያስችሉ የራሳቸውን የእቃ መግዣ ከረጢቶችን በማምጣት እንዲጠቀሙ የሚያደርገውን እና የፕላስቲክ ውጤቶችን አጠቃቀም የሚቀንሰውን ‘ብሪንግ ዩር ኦውን ባግ’ ቢል የተባለውን ደምብ አጽድቋል። ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው እና ታዳሽ የሆኑ የሃይል አጠቃቀም አማራጮችን ለነዋሪዎቻችን ለማቅረብ የሚረዱ የማህበረሰብ ምርጫ ማመጣጠኛ የሙከራ ፕሮግራም /Community Choice Aggregation pilot program/ ለመፍጠር የሚያስችል ደምብ ማጽደቅም ችለናል።

ከዚህ በተጨማሪም የኬራይ ቤት የክፍያ እገዛ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመስራት እና ጠብቆ ለማቆየት የሚረዱ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ ጥረት እና እገዛ አድርገናል። ባካውንቲውም የሚታዩትንም ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች አሰራር እና የታዩ መሻሻሎችንም ማሰብ እና ማድነቅ ችለናል።

የካውንቲ እና የመኖሪያ ቤት አመራሮች ፈር ቀዳጅ በሆነው የቻይምስ ዝግጅት ላይ አካፋዎችን ይዘው የሚያሳይ

ቢሮአችን በፐርፕል ላይን የከተማ ባቡር መስመር ግንባታ ምክንያት የተጎዱ ነዋሪዎችን እና የንግድ ተቋማትን ለማገዝ እና አብሮ ለመስራት የሚያደርገውንም ጥረት እንደቀጠለ ነው። ከተጎዱ የአነስተኛ የንግድ ተቋማት ጋር ያደረግነውን ውይይት ተከትሎ የሜሪላንድ የትራንስፖርት መምሪያ  (MDOT) የአነስተኛ የንግድ ተቋማት የገንዘብ ድጎማ ፕሮግራም የሚሻሻልበትን ሁኔታ ለማሳደግም ሰርተናል። በተጨማሪም ስፍር ቁጥር በሌላቸው የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት ሰልፎች ላይ በመሳተፍ እና ከፐርፕል ላይን የትራንዚት አጋሮች እና ከመንገድ ደህንነት ተሟጋቾች ጋር በመሆን በፐርፕል ላይን መስመር አካባቢዎች ላይ የእግር መንገደኞችን ደህንነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎችን ሰርተናል።

የፐርፕል ላይን የግምባታ ሳይት የቡድን ጉብኝት

በዚህ አመት የሁላችንንም ህይወት ለማሻሻል በማሰብ በኩራት በአንድነት መስራት ችለናል። በቀጣዩም አመት እንዲሁ በአንድነት እና በትብብር አብረን እንደምንሰራ እጠብቃለሁ።

ደስታ የተሞላበት የታንክስጊቪንግ እንዲሁም ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ለረፍት የሚመች የበአል ወቅት እንዲሆን እመኝላችኋለሁ!

ከማክበር ሰላምታ ጋር

ኬት ስቴዋርት

የካውንስሉ ፕሬዚደንት

 Thanksgiving Day Parade opening ceremony.

የአእምሮ ጤና ኮርነር

የአእምሮ ጤና የቪዲዮ ፕሮግራሞች

የአእምሮ ጤና ጉዳይ ሁሉንም ሰው የሚነካ በመሆኑ በአእምሮ ጤና ላይ በማተኮር በጣም ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶችን እየሰጡ ያሉ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ድርጅቶችን ስራ የሚያሳዩ ተከታታይ የሆኑ የአእምሮ ጤና ቪዲዮ ፕሮግራሞችን ሳስጀምር ኩራት ተሰምቶኝ ነበር። በነኚህ ቪዲዮዎች የተካተቱት መረጃዎች ከድንገተኛ አደጋ እገዛ እስከ ስነልቦናዊ ምክር እንዲሁም የማህበረሰብ ፕሮግራሞችን አጉልቶ በማሳየት በፕሮግራሞቹ ላይ የሚቀርቡት ታሪኮች ነዋሪዎቻችን እና ጎረቤቶቻችንን ለማገዝ የተዘጋጁ ሃብቶችን በተመለከተ የሚያስገነዝቡ መረጃዎችን የያዙ ናቸው። ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ሊኖር የሚችልን የማግለል ሁኔታ በአንድ ላይ ሆነን ለመስበር ያስችለን ዘንድ እነኚህን ቪዲዮዎች በመመልከት መረጃ እና እውቀትን ይገብዩ።  

በዚህ አመት ጎልተው እንዲታዩ የመረጥናቸውን እጅግ በጣም ጥሩ የሚባሉ ድርጅቶች ይመልከቱ፤

የካውንስሉ ፕሬዚደንት ስቴዋርት በየካቲት 2025 በተካሄደ የአእምሮ ጤና ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ

በመሰረታዊ እንክብካቤ አሰጣጥ ጥምረቱ የሚተገበረው የሞንትጎመሪ ኬርስ የስነባህሪ ጤና ፕሮግራም

አካላዊና ስነልቦናዊ የጤና እንክብካቤ በአንድ ጥላ ስር የሚሰጥበት መድረክ! በመሰረታዊ እንክብካቤ አሰጣጥ ጥምረቱ የሚተገበረው የሞንትጎመሪ ኬርስ ጥምረት የስነባህሪ ጤና ፕሮግራም (MCBHP) በካውቲው ከሚገኙ የሴፍቲ ኔት የጤና ማእከላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ታካሚዎች የጤና እንክብካቤ በሚያገኙባቸው ቦታዎች ላይ የስነልቦና ጤና አጠባበቅ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ለማድረግ ይሰራል። ሁለት ቋንቋ የሚናገሩ የስታፍ አባላቱም በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች አገልግሎቶችን በቀጥታ የሚሰጡ ሲሆን በሌሎችም ቋንቋዎች ታካሚዎችን ለማገልገል ዝግጁ ናቸው። የስነባህሪ ፕሮግራሙ (MCBHP) በግለሰብ ደረጃ እና በቡድን የምክር አገልግሎት፣ የጤና ሁኔታ ግምገማ፣ የመድሃኒት አሰጣጥ ክትትል፣ እንዲሁም እንደ የምግብ እገዛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን የመሳሰሉ የሚያስገኙ ሃብቶች ጋር ታካሚዎችን የማገናኘት ስራዎችን ይሰራል። እነኚህ አገልግሎቶች በአጋር ድርጅቶች የህክምና አገልግሎት ለሚያገኙ ለሞንትጎመሪ ኬርስ ተሳታፊዎች በነጻ የሚሰጡ ናቸው። አገልግሎቶቹ በሚከተሉት ጣቢያዎች በቴሌ ሄልዝ /የርቀት ህክምና/  የሚሰጡ ሲሆኑ ለበለጠ መረጃ እና በእንክብካቤ ፕሮግራሙ ለመመዝገብ እባክዎን እያንዳንዱን የጤና ማእከል በማግኘት ያማክሩ።

በሞንትጎመሪ ኬርስ ለመመዝገብ የበለጠ ይወቁ .