Skip to main content

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - Jan. 8, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞች፣

አዳሽ እና በደስታ የተሞላ የዓመት በዓል ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። አዲሱ ዓመት ላይ ስንገባ እና ለወደፊቱ ስለሚመጣው እርግጠኛ የማንሆንበት መጪ ጊዜ ላይ ስንዘጋጅ፣ ብዙ ጊዜ የሚፈጅብን የህግ ማውጣት ሂደት እና ለወደፊቱ የታቀዱትን የሚማርኩ ኢንሼቲቮችን ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ነኝ።  

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ብሩህ ተስፋ እንዲኖር በጋራ ከእናንተ ጋር ለመስራት እና ለሁሉም ነዋሪዎቻችን እጁን ዘርግቶ የሚቀበል እና አካታች ማህበረሰብ መሆናችንን ለማስቀጠል ዝግጁ ነኝ።

መልካም አዲስ ዓመት! 

እንደ ሁልጊዜው ሁሉ፣ ማንኛውም ዓይነት ጥያቄዎች ያላችሁ ከሆነ እና ድጋፍ የምትሹ ከሆነ የእኔን ቢሮ ለማግኘት ይምጡ። 

ከአክብሮት ጋር፣

ኬት ስቲዋርት

የካውንስሉ ፕሬዝደንት

ከካውንስሉ ፕሬዝደንት ኬት ስትዋርት (ዲስትሪክት 4) የሚል “2025 መልካም አዲስ ዓመት” የሚል ርችቶች ያሉበት ሰማያዊ ምስል።

የMLK (የማርቲን ሉተር ኪንግ) የመታሰቢያ ቀን

የMLK (ማርቲን ሉተር ኪንግ) መታሰቢያ ቀን ሲከበር በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ልዩነት እየፈጠሩ ካሉት የበጎፈቃድ ተሳታፊዎች ጋር ይቀላቀሉ። ቅዳሜ ጃንዋሪ 18 ቀን የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች ላይ የሚከናወኑት የአካባቢው የመታሰቢያ ፕሮጀክት ላይ ይሳተፉ፣ ወይም እሁድ ጃንዋሪ 19 ቀን በቤተሳዳ ማርዮት ኖርዝ [Bethesda North Marriott} ኮንፈረንስ ማዕከል ውስጥ የሚደረገው ዓመታዊው የመታሰቢያ ቀን ላይ ይቀላቀሉን። የመታሳቢያ ቀን ፕሮጀክቶቹ  ከቤት መውጣት ለማይችሉ አዛውንቶች የበረዶ ቀን ምግብ ከቤት የማድረስ ["Snow Day" boxes with Meals on Wheels] የሚያስችሉ ነገሮችን መፍጠር፣ መጠለያ አልባ ለሆኑ ነዋሪዎች የመጸዳጃ ጥቅል ዕቃዎችን እና የመክሰስ ከረጢቶችን ማዘጋጀት፣ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች እና ቤተሰቦችን የሚጠቅሙ ሌሎች ተግባራቶችን መፈጸም ይጨምራሉ።

የበለጠ ይወቁ እና ይመዝገቡ

የአሜሪካ ባንዴራ ያለበት የMLK መታሰቢያ ቀን ምስል እና የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጅንየር አኒማ ምስል።

ለአየርንብረት ተስማሚ የሆኑ የገና በዓል ዛፎችን መጣል

የቆረጧቸው የተፈጥሮ የገና ዛፎች ሪሳይክል ሊደረጉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? ሁሉንም የገና ዛፍ ማስጌጫዎችን፣ መብራቶችን፣ ገመዶችን እና ፕላስቲኮችን ካነቃቀሉ በኋላ ፣ የእርስዎ የገና በዓል ዛፍ እና የአበባ ጉንጉኖች በመደበኛው ሪሳይክል የማድረጊያ መርሀግብር ቀን 7 a.m ሰዓት ላይ ከመንገድ ጎን የሚገኘው የእግረኛ መንገድ ላይ ማስቀመጥ ይቻላል። በአፓርታማ ወይም በኮንዶሚኒየም ቤት ውስጥ የምትኖሩ ከሆነ፣ ለቦታው የሚመጥን መመሪያዎችን ለማግኘት ከንብረት አስተዳዳሪው ጋር ይነጋገሩ። ስለዚህ የገና በዓል ዛፍዎን ማስወገድ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የDepartment of Environmental Protection ድረገጽ ላይ ይሂዱ።

የእግረኛ መንገድ ላይ የገና በዓል ዛፍ

ሰብዓዊ መብቶች ላይ በሰሩት ሥራ የክብር መዝገብ ላይ የሰፈሩሰዎች ዝርዝር

በካውንቲው ውስጥ እና ከዛም በላይ የሰብዓዊነት እና የሰብዓዊ መብቶች ላይ ላበረከቱት ተምሳሌትነት ሞንትጎመሪ ካውንቲ ስድስት ሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች ላይ በሰሩት ሥራ የክብር መዝገብ ላይ የሰፈሩ ሰዎች ዝርዝር (Human Rights Hall of Fame) ውስጥ እንዲሰፍሩ አድርጓል። የሶስት የምርጫ ዘመን ተመራጭ የሆኑት የካውንቲው ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዳግ ዳንከን፣ ካትሪን ሌጌት፣ ሼርሊን ሉካስ፣ የቀድሞ የህዝብ ምክር ቤት ተመራጭ ኮኒ ሞሬላ፣ ሬቨረንድ(ቄስ) ዶ/ር ጋሬዝ ኢ ሙራይ እና ካርል ኤ ፕራተር ሲንየር የተደረገላቸው የክብር ዝግጅት ላይ በመገኘቴ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል። እያንዳንዱ እነዚህ ግለሰቦች በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ እና ነባራዊ የሆነ ውጤት አምጥተዋል እና በሰሩት ስራ እኔ ተበረታትቼአለሁ። ከዚህ ቀደም በሞንትጎመሪ ካውንቲው ውስጥ የማይጠፋ ታሪክ ከሰሩት ከ100 በላይ የሚሆኑ የክብር መዝገብ ላይ ከሰፈሩ ሰዎች ጋር በዚህ ዓመት የተቀላቀላችሁት እንኳን ደስ ያላቹህ እና ይሄንን ዝግጅት ላዘጋጀው ለሰብዓዊ መብቶች ቢሮ እናመሰግናለን።   

የካውንቲው ባለስልጣናት እና የክብር መዝገብ ላይ የሰፈሩት ሰዎች በመድረኩ ላይ በጋራ ፎቶ ሲነሱ

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ

የእኛን የጤና ጥበቃ ጀግናዎችን ማጎልበት

ከPrimary Care Coalition እና  WorkSource Montgomery ጋር በጋራ በመተባበር በAMSS Certified Nurses Assistants Scholarship and Employment Program በኩል ከ 100 በላይ የሚሆኑ ዕውቅና የተሰጣቸው የነርስ ረዳቶችን የምረቃ በዓል ለማክበር ከ American Muslim Senior Society (AMSS)፣ የማህበረሰቡ ዓባላት እና የካውንቲው መሪዎች ጋር በመሆን በዝግጁቱ ላይ ስለተገኘሁ ኩራት ይሰማኛል። ይሄ ስኬታማ ኢኒሼቲቭ አዛውንቶች የሚገባቸውን ጥራት ያለው እንክብካቤ እንዲያገኙ ያስችላል እና ለብቁ ለሆኑ ለካውንቲው ነዋሪዎች ደግሞ በጤና ዘርፍ የትምህርት፣ የስልጠና እና የስራ ቅጥር ዕድሎችን ይፈጥርላቸዋል።

ስለ ፕሮግራሙ የመለጠ ይወቁ።

የረዳት ነስር [CNA] ተመራቂዎች፣ የAMSS አባላቶች እና የካውንቲው መሪዎች የቡድን ፎቶ ሲነሱ

ኢሞሪግሮቭየእግርጉዞጉብኝት

በቅርብ በጌትርስበርግ ውስጥ የሚገኘው ታሪካዊው የኢሞሪ ግሮቭ [Emory Grove] አፍሪካዊ አሜሪካዊ ማህበረሰብ የሚያዘጋጀው የእግር ጉዞ ጉብኝት ላይ ከሬቨረንድ ቲሞቲ ዋርነር እና ከማህበረሰቡ ዓባላት ጋር ተቀላቅያለሁ።  ኢሞሪ ግሮቭ [Emory Grove] ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው በ 1864 ዓ.ም ውስጥ ነፃ በወጡ አፍሪካዊ አሜሪካዊያን ነው። የእግር ጉዞው ስለ ማህበረሰቡ ታሪክ የበለጠ ለማወቅ የሚያስችል ዕድል ነው፣ በተለይ በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ላይ የከተማ ዕዳሳት በሚል መርሀግብር ያልተገበሩት ቃሎች ያመጡትን ጎጂ ተጽእኖ እና ከዚህ ቀደም የነበሩትን ኢፍትሃዊነቶችን በሚያስቀር እና  እውቅና በሚሰጥ መልኩ የተቀላቀለ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ባለቤትነት እና ሌሎች የመኖሪያ ቤት አገልግሎቶችን በቦታው ላይ ለማቅረብ አልሞ የተዘጋጀውን የመልሶ ልማት ፕሮጀክትን ለመረዳት ያስችላል። ፕሮጀክቱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ፣ የቤቶች ዕድል መፍጠር ኮሚሽን (Housing Opportunities Commission)፣  የኢሞሪ ግሮቭ (Emory Grove) መሪዎች፣ ሃብቲታ ፎር ሁማኒቲ (Habitat for Humanity) እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር የሚተገበር ሲሆን፣ ከአዲስ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ ታሪካዊውን የኢሞሪ ግሮቭ ዩናይትድ ሜተዲስት ቤተክርስቲያን የከተማው ማዕከል ያደርጋል።

የማህበረሰቡ ዓባላት የአፐር ካውንቲ ኮምዩኒቲ ሴንተር የግድግዳ ስነጥበብ ስራን እየተመለከቱ

ሎክስ እና የህግ አውጪዎች ቁርስ

ዓመታዊው የታላቋ ዋሽንግተን JCRC የህግ አውጪ ቁርስ ጉባኤ ላይ በጋራ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለመወያየት ወደ መቶ የሚቆጠሩ አይሁዳዊያን ማህበረሰቦች እና የተመረጡ መሪዎች ጋር መገናኘታችን መልካም ነበር። ለማህበረሰባችን JCRC ላበረከታቸው ሁሉንም ጠቃሚ ሥራዎች በጣም አመሰግናለሁ፣ ይሄም የሚያካትተው ሁሉንም እምነቶች እና የዳራ ታሪክ ያላቸውን ሰዎች በጋራ ማቀራረብ፣ ለትርፍ ላልተቋቋሙ እና ለእምነት ቡድኖች የመጠባበቂያ ድጎማዎችን ማሳደግ ላይ መሟገት፣ እና ጥላቻ እና መድሎን መታገል ነው።

የ JCRC አርማ ያለበት መድረክ ላይ የካውንስሉ ፕሬዚደንት ስቲዋርት ሲናገሩ።

የአዕምሮ ጤና ሕክምና ጥግ፦

በነፃ የሚታደሉት የRecFit ማለፊያ ትኬቶች በመጠቀም በአዲስ ዓመት ላይየሰውነት እንቅስቃሴ ያድርጉ

የሰውነት ማጎልመሻ እና እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ለሰውነት ጤና ብቻ ሳይሆን የእርስዎን የአዕምሮ ጤና ያሻሽላል፣ የእርስዎን የስሜት ሁኔታ እና የራስ መተማመን ሁኔታን ያጎለብታል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመዝነኛ ማዕከል የRecFit መግቢያ ትኬቶች በ2025 ዓ.ም ላይ ለሞንትጎመሪ ነዋሪዎች በነፃ መሰጠታቸውን ይቀጥላሉ፣ ይሄም ማለት የተሟላ የሰውነት ማጎልመሻ መሳሪያዎች የተገጠመላቸውን ክፍሎች፣ ክፍት የጂም እንቅስቃሴዎችን እና የጨዋታ ክፍሎችን በማህበረሰቡ የመዝናኛ ማዕከል ውስጥ በነፃ ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው። በአዲሱ ዓመት ላይ ራስን መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጡት ተግባር ያድርጉ እና የRecFit መግቢያ ትኬት ለማግኘት የማዕከሉ ቦታን ይጎብኙ። የሰውነት ማጎልመሻ ትኬቱ የውሃ ዋና ቦታዎችን መግቢያን አይጨምርም።

በትሬድሚል ላይ የሚራመዱ እና የጂም መሣሪያዎችን የሚጠቀሙ ሰዎች። የስዕሉ ባለቤት፦ ሞንትጎመሪ መዝናኛ ማዕከል