Skip to main content

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - Jan. 22, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቼ

የካውንቲው ዋና አስፈጻሚ ለ2026 የበጀት አመት የካፒታል በጀት ያዘጋጁት ረቂቅ እንዲሁም በ2025-2030 የበጀት አመት የካፒታል ማሻሻያ መርሃግብር (CIP) ላይ የተደረጉትን ማስተካከያዎች በተመለከተ የተላከው ሰነድ ለምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት ደርሶናል። በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ምክርቤቱ የቀረበውን ረቂቅ በጀት በጥንቃቄ የመመርመር ስራውን ይጀምራል። በመጪዎቹ ወራትም ዲስትሪክት 4ት ላይ ተጽእኖ የሚያደርጉ ፕሮጀችቶችን በተመለከተ መረጃ የምሰጣችሁ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ፕሮጀችቶች በጥሩ ሁኔታ እንዲካሄዱ ለማረጋገጥ የምንሰራቸውን ስራዎችም በተመለከተ አስረዳለሁ። በፌብሩዋሪ/ የካቲት 5 እና 6 በ1፡30 ፒ ኤም እና በ 7 ፒ ኤም በሚካሄዱት የውይይት መድረኮች ላይም እንድትገኙ እና ሙሉውንም የካፒታል በጀት ይህን  በመጫን እንድታነቡ አጋብዛለሁ።

በተጨማሪም በ2025 በሚካሄደው የሜሪላንድ አጠቃላይ የህግ አውጪዎች ጉባኤ ላይ ዲስትሪክት 4ትን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ካውንቲው ላይ ተጽእኖ የሚያደርጉ ይርተወሰነ ቁጥር ያላቸው ፕሮጀችቶችን እና ረቂቅ ህጎችንም በቅርብ እንደምከታተል ለመግለጽ እወዳለሁ።  ከህግ አውጪ አካላት ጋር በመቀናጀት የሞንትጎመሪ ካውንቲን እና ብሎም አጠቃላይ የሜሪላንድን የወደፊት እጣ ለመቅረጽ ርብርብ በምናደርግበት በአሁኑ ወቅት በዚህ ሂደት ላይ ሊገጥሙን የሚችሉ እድሎችን ለመጠቀን እና ተግዳሮቶችንም ለመጋፈጥ በጥሞና እና በጉጉት በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ። 

በመጨረሻም አዲሱን የፌዴራላዊ አስተዳደር የመጀመሪያ ጥቂት የስራ ቀናት ለመቀላቀል በምንዘጋጅበት በአሁኑ ጊዜ ያሉንን ሃብቶች እና እገዛዎች ለሁሉም ነዋሪዎቻችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የምናቀርብበት እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ እየተገበርን ያለነውን አካታች እና እንግዳ ተቀባይ የሆነ ባህላችንን ወደፊትም ለማስቀጠል ቃል በመግባት ነው።  ጠቃሚ ስለሆኑ የመረጃ ሃብቶች ለማወቅ ይህን ይጫኑ፤ Learn more about essential community services available to you.

እንደተለመደው ምንም አይነት ጥያቄ ካላችሁ ወይንም እገዛ ከፈለጋችሁ ወደቢሮዬ መምጣት/ማግኘት ትችላላችሁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር

ኬት ስቴዋርት

የምክርቤቱ ፕሬዚደንት

የካውንስሉ ፕሬዚደንር ስቴዋርት ሴኔተር ዊል ስሚዝ እና ዴል ጄኒል ዊልኪንስ  ጋ በመሆን በአናፖሊስ የተካሄደውን በ2025 የተካሄደውን ጠቅላይ ጉባኤ የማስጀመሪያ ስነስርአት ላይ።.

ጀግና ሲታወስ

ሌሎችን ከአደጋ የመታደግ የእለት ተእለት ስራውን በሚያከናውንበት በአጋጣሚ ህይወቱን ባጣው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት እና የአደጋ አገልግሎት ዋና/ማስተር የእሳት አደጋ ባለሞያ በክሪስቶፈር ሂጊንስ አሳዛኝ ሞት ሞንትጎመሪ ካውንቲ የተሰማውን ልባዊ ሃዘን ይገልጻል።  ዋና/ማስተር የእሳት አደጋ ባለሞያ ሂጊንስ ከ23 አመት በላይ የሆነውን የእድሜውን ክፋይ ማህበረሰባችንን በፍቅር እና እንክብካቤ በተሞላበት አኳኋን በማገልገል እና በመጠበቅ ስራ ያሳለፈ እውነተኛ ጀግኛ ነበር። የዋና/ማስተር የሳት አደጋ ባለሞያ ሂጊንስን ህይወት እንዲሁም ሌሎችን ለመርዳት የነበረውን ጽኑ አቋም ሁሌም እንደምናስብ እየገለጽን ከሱ ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩትም የሱን አደራ/ቅርስ እንደሚያስቀጥሉ በጽኑ እንተማመናለን። የሱ ማስታወሻ ለሁሉም እሱን ለሚያውቁት በረከት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

የሃዘን ጥቁር መስመር የተደረገበት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ እና ማዳን አገልግሎት አርማ

የሙስሊም አሜሪካውያን ቅርስ ማሰቢያ ወር

ባለፈው ሳምንት ምክር ቤቱ ከሙስሊም አሜሪካውያን የማህበረሰባችን አባላት ጋር በመሆን የአሜሪካውያን ሙስሊሞችን የቅርስ መታሰቢያ ወር አክብሮ ነበር። በተባበረው የሜሪላንድ  ሙስሊሞች ካውንስል መረጃ መሰረት ከ60 የተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ ወደ 350000 ሙስሊም አሜሪካውያን በሜሪላንድ የሚኖሩ ሲሆን ወደ 3 ፐርሰንት ይሚጠጉት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎችም ሙስሊም አሜሪካን ናቸው። ይህ ልዩ የሆነ የመታሰቢያ ዝግጅት ብዝሃነት ያለውን የሙስሊሙን ማህበረሰብ ባህል እንድናከብር እና እንዲሁም የሙስሊም አሜሪካውያን በሃገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያደረጉትን መጠነ ሰፊ አስተዋጽኦ በክብር እንድናስበው እድል ፈጥሮልናል።

የሙስሊም አሜሪካውያን የቅርስ ወር ማሰቢያ ላይ የተወሰደ የግሩፕ ፎቶ

የኮሪያን አሜሪካውያን ቀን

ከካውንቲው ዋና አስፈጻሚ ማርክ ኤርሊች ጋ አብሬ በመሆን በ1903 በሃዋይ ግዛት አድርገው ወደ አሜሪካ የፈለሱትን የኮርያ ስደተኞችን አስቦ በሚውለውና የኮሪያ አሜሪካውያንን መጠነሰፊ አስተዋጽንኦ በሚዘክረውን ስነስርአት ላይ  ተካፍያለሁ። በዚሁ ስነስርአት ላይ ዋና ቺፍ ቹንግ ኬ ፓክና በሜሪላንድ እስቴት የሚኖሩ ታዋቂ የኮሪያ አሜሪካውያንና የኤዥያ የማህበረሰብ መሪዎች ተገኝተዋል።

የኮሪያ አሜሪካውያንን ቀን ማሰቢያ ላይ የተወሰደ የግሩፕ ፎቶ

ለኖርዝ ቤተዝዳ ባቡር ጣቢያ/ሜትሮ ማሻሻያ የ24.8 ሚሊዮን ዶላርየገንዘብ ድጋፍ

መልካም ዜና፤ ሞንትጎመሪ ካውንቲ በኖርዝ በተዝዳ ሜትሮ ስቴሽን ያለውን ሁለተኛ መግቢያ እና በአካባቢው ለሚደረጉ የማሻሻያ ስራዎች የሚውል የ24.8 ሚሊዮን ዶላር ድጎማ እንዲያገኝ “የአሜሪካን መሰረተ ልማት ቀጣይነት እና ፍትሃዊነት ባለው መልኩ መልሶ መገምባት” /ሬይዝ/ ከተባለው የገንዘብ ፕሮግራም ተመርጧል።   

ይህ የልገሳ ገንዘብ ካውንቲው በኖርዝ በተዝዳ የህይወት ሳይንስ ጋር የተያያዙ ስራዎችን እንዲያፋጥን / accelerating life sciences in North Bethesda / ከማገዙም በላይ የኖርዝ በተዝዳን ሜትሮ ስቴሽን ብዙ በእግር ርምጃ የሚደረሱ መገልገያዎች ያሉት ዘርፈ ብዙ የባቡር ጣቢያ እንዲሆን ያስችለዋል።

የኖርዝ በተዝዳ የሜትሮ መሳፈሪያ

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ

የዶ/ር ማርቲን ሊተር ኪንግ ትሩፋት/ቅርስን ማክበር

ያለፈውን ሳምንት ያሳለፍኩት የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግን ህይወት እና የህይወት ትሩፋት ለማክበር በካውንቲው ውስጥ በተካሄዱ የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በመካፈል ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በኮፊልድ የማህበረሰብ ጣቢያ በተካሄደው “ክራፍት ፎር ኤ ኮዝ ዊዝ ኦንሊ ሜክ ቢሊቨ” የተባለው እንዲሁም በኖርዝ በተዝዳ የተካሄደው አመታዊው የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የአገልግሎት ቀን እና በስትራዝሞር የተካሄደው የማርቲን ሉተር ኪንግ ቀን የምስጋና ቀን ይገኙበታል።

በተጨማሪም የአልፋ ፋይ አልፋ ወንድማማችነት የአዮታ ዩፕሲሎን ላምባዳ ቅርንጫፍ ባዛጋጀውና ኮሌጅ መግባት ለሚፈልጉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች ስኮላርሺፕ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚረዳው የ48ተኛውን የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የስኮላርስሺፕ የቁርስ ዝግጅት ላይም ተካፍያለሁ። ለሁላችንም የተሻለ የወደፊት ህይወት በጎ እድሎችን ለመፍጠር የሚረዱትን የዶክተር ኪንግን ስራዎች ለማስቀጠል በሚል አላማ ከነዚህ ብዛት ካላቸው የካውንቲው ነዋሪዎች እና የአመራር አባላት ጋር አብሬ መሳተፌ ትልቅ እርካታ የሚሰጥ ክስተት ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

MLK Day

ለእድሜ ባለጸዎች የሚደረግን እንክብካቤ የወደፊት አሰራር በበጎ ጎኑ መቅረጽ

የ2025 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህግ አውጪዎች ጉባኤ በሚጀመርበት በዚህ ወቅት የድሜ ባለጸጋዎች ደህንነት ተቀርቋሪ መሰረታዊ ድርጅት / Grass Roots Organization for the Well-being of Seniors (ግሮውስ) / ከተባለውን ተቋም ጋር በመገናኘት የእድሜ ባለጸጋዎችን ደህንነት እና የቤት ለቤት እንክብካቤ አሰጣጥን የተመለከቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በመቻሌ ደስታ ተሰምቶኛል። ድርጅቱ /ግሮውስ/ ለሚያደርገው የድሜ ባለጸጋ ለሆኑ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍና በአጠቃላይም እድሜያቸው ለገፋ የህብረተሰብ አባላት ደጋፊ የሆነ ጥምረት ለመፍጠር የሚያከናውናቸውን የቅስቀሳ ስራዎችንም አደንቃለሁ።   የእድሜ ባለጸጋ የማህበረሰብ አባላት በጣም በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኙ የህዝባችን አካል በመሆናቸው ለነሱ የሚሆን ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት ሁላችንም ተያይዘን ከማህበረሰብ ድርጅቶች ጋራ በጥምረት ልንሰራ ይገባናል።

የካውንስሉ ፕረዚደንት  ስቴዋርት የቤት እና የማህበረሰብ  አገልግሎትን በተመለከተ ንግግር ሲያደርጉ .

ኮሚሽነር ተረንስ ሂል ሲታወሱ

በሞት የተለዩንን ተረንስ ሂልን ለማሰብ በተዘጋጀው የማስታወሻ ስነስርአት ላይ ከቤተሰቦቻቸው እና ከወዳጆቻቸው ጋር አብሬ  ለመገኘት በመቻሌ ምስጋና አቀርባለሁ።  ሚስተር ሂል የቤት አልባነት ኢንተሬጀንሲ ኮሚሽን የተባለው ጥምረት ውስጥ በጽናት ያገለገሉ ኮሚሽነር ነበሩ። በተለይ በጣም ርህራሄ እና ለጋስነት በተሞላው መልኩ ያደርጉት የነበረው የጸረ ድህነት ተሟጋችነትታቸው እና ቀታይነት ባለው መልኩ ህብረተሰባችንን ለመርዳት ሲደርጉት የነበረው ጥረት ሲታወስ ይኖራል። ሚስተር ሂል በአጠቃላይ በቀና አስተሳሰባቸው፣ በጽኑነታቸው እና ሁሌም የተቸገሩትን ለመርዳት በሚያሳዩት ጥረት በበጎ ሲታወሱ ይኖራሉ።  

Terence Hill

የአእምሮ ጤናን በተመለከተ

ምክር ቤቱ የአደጋ ማሳወቂያመስመር / Crisis Hotline/ አገልግሎቶችን ለመደገፍ ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ አጸደቀ

የ 9-8-8 የአደጋ ማሳወቂያ የመስመር አገልግሎቶችን ለመደገፍ ምክር ቤቱ በቅርቡ ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ ገንዘብ ድምጽ ሰጥቶ አጽድቋል። ይህ የተጨማሪ ገንዘብ በሜሪላንድ የስነባህሪ ጤና አስተዳደር በተገኙ ሁለት የገንዘብ ልገሳ ፕሮግራሞች አማካኝነት የተሰጠ ነበር።  ይህ ድጎማ የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን፣ የሰራተኛ ቅጥር ፍላጎትን፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ ኦዲት፣ እንዲሁም የ 9-8-8 የአደጋ ማሳወቂያ መስመር አገልግሎቶችን ለመሸፈን ይረዳል ተብሎ ይታመናል። ይህን እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ሃብት ለማገዝ በስቴቱ የተደረገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ ሳላደንቅ አላልፍም።

988 Crisis Lifeline.