የሞንትጎመሪ ካውንቲ እሴቶችን ዳግመኛ የሚያረጋግጥ መልእክት
ውድ ጓደኞቼ
ከማክበር ሰላምታ ጋር
በፌዴራል መንግስት ደረጃ የታዩ ለውጦች በማህበረሰባችን ላይ ስጋት እና አለመረጋጋትን ፈጥረዋል። በስደተኞች፣ የLGBTQ+፣ እና ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው የማህበረሰቡ ዓባላት ላይ በተለየ ሁኔታ ተጽእኖ ፈጥሯል። እነዚህን ስጋቶች ተረድተናል እናም የነዋሪዎቻችንን መሰረታዊ መብቶች ብቻ ሳይሆን የአካባቢያችንን አስተዳደር የማስተዳደር አቅም ጭምር ለማስከበር በቁርጠኝነት መስራታችንን እንቀጥልበታለን። በህግ ስር ለመልካምነት፣ ለፍትህ እና ሁሉንም በእኩል ሁኔታ የማስተናገድ ቁርጠኝነታችን ላይ በጽኑ ሁኔታ እንሰራለን።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ መሪዎች በአስደናቂው ብዝሐነት የተሞላው ካውንቲያችን ውስጥ ለአንድ ሚሊዮን ነዋሪዎቿ አገልግሎት እና ድጋፍ መስጠት ላይ በህብረት እየሰሩ ይገኛሉ። ማህበረሰባችን የመኖር፣ የመስራት፣ የማምለክ እና ቤተሰብ የማሳደግ ተግባራት ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እና እንግዳ ተቀባይ ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ የአካታችነት፣ የግንኙነት እና የርህራሄ እሴቶችን ከፍ እንዲያደርግ በቁርጠኝነት እንሰራለን።
እንደ Department of Health and Human Services [የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ] የመሳሰሉት የካውንቲ ኤጀንሲዎች፣ በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት ለሚሹ ወይም የሚያገኙ ሰዎችን የኢሚግሬሽን ሁኔታ በተመለከተ መረጃ አይሰበስቡም። ካውንቲው የሁሉንም ነዋሪ የግላዊነት ሁኔታን ቅድሚያ ይሰጣል እና የግላዊነት መብት ህጎች እና ደንቦችን ለማስፈጸም በትጋት ይሰራል። የMontgomery County Police Department [የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ መመሪያ] እና Sheriff’s Office [የሼሪፍ ቢሮ] የU.S. Immigration and Customs Enforcement (ICE) [የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አስፈፃሚ] አካል አይደሉም። የኢሚግሬሽን ህግ የማስከበር ስራ የፌደራል መንግስት ሃላፊነት ነው። የእኛ ካውንቲ ህግ አስከባሪ የህዝብ ደህንነትን የማስጠበቅ ወሳኝ ተልእኮው ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም ማህበረሰቡን መጤውን ጨምሮ በሁሉም የማህበረሰባችን አካላት መካከል መተማመንን እንዲኖር ይጠይቃል።
የማህበረሰቡን የመተማመን ሁኔታ የሚጠብቁ፣ የዘር ፍትሃዊነትን እና ማህበራዊ ፍትሃዊነትን የሚያበረታቱ እና በሁሉም መልኩ ጥላቻን እና መድልዎን የሚዋጉ ፖሊሲዎችን ማበረታታችንን እንቀጥልበታለን። የዘር ፍትሃዊነት እና ማህበራዊ ፍትሃዊነት ለሁሉም ለመፍጠር በትጋት ስንሰራ መግባባት፣ መቻቻል እና መከባበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልዩ መለያዎች ናቸው።
70,000 የሚደርሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች የሚሰሩት ለፌደራል መንግስት ሲሆን እነሱ የሚሰጡት የህዝብ አገልግሎት ለእኛ ዲሞክራሲ ዋጋ ይኖረዋል እና አብዛኛዎቹ የስጋት ሁኔታ ውስጥ ገብተዋል። የእኛ ማህበረሰብ የሥራ ዕድሎችን፣ የሰው ሃይል ልማት ፕሮግራሞችን፣ እና የሥራ ማጣት ሁኔታን ለሚያጋጥማቸው የማህበረሰቡ ዓባላት ዕድሜ ልክ የትምህርት ዕድሎችን ይፈጥራል።
ከፌደራል መንግስት ቀጥሎ ስለሚወሰነው ውሳኔ በእርግጠኛነት የምናውቀው ነገር የለም፣ ነገር ግን የሞንትጎመሪ ካውንቲን እሴቶችን ለማቆየት እና ለማጠናከር የተቻለንን ሁሉ እንደምናደርግ ለነዋሪዎቻችን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ለነዋሪዎቻችን ጠቃሚ መረጃዎች
የተለዩ ሁኔታዎች ያላቸው ከሆነ የማህበረሰቡ ዓባላት ጠበቃ ማማከር ሊያስፈልጋቸው ይችላል።
ኬት ስቴዋርት
የምክርቤቱ ፕሬዚደንት