Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - Feb. 26, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

የተወደዳችሁ ጓደኞቻችን፣

በሜሪላንድ የሚኖሩ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው በፌደራል መንግስቱ በተደረጉ ርምጃዎች/ለውጦች ምክንያት በተጸእኖ ላይ መውደቃቸው ቀጥሏል። እኛም በአካባቢ ደረጃ የእናንተ ተወካይ እንደመሆናችን መጠን ከስቴት፣ ከፌደራል እና ከማህበረሰብ አጋሮቻችን ጋር በጋራ በመሆን በጣም አስፈላጊ እና አብይ የሆኑ የማህበረሰብ ድጋፎች እና ሃብቶች ሳይቋረጡ እንዲቀርቡ እና እንዲቀጥሉ ለማድረግ በቅርበት በመስራት ላይ እንገኛለን።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይም “ለአገልግሎት እና ድጋፍ አቅርቦት እንተባበር” በሚል ርእስ የድረመረብ/ኦንላይን የማህበረሰብ ስብሰባ ያደረግን ሲሆን በውይይቱም ተጽእኖ ለደረሰባቸው የፌደራል ሰራተኞች ሊቀርቡ የሚችሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን እና ሃብቶችን /resources available to impacted federal workers/ በተመለከተ መረጃዎችን ተለዋውጠናል።

ከመጪው መጋቢት ወር ጀምሮም የስራ ቅጥር፣ የሰራተኞችን አቅም ማጎልበት እና የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች፣ የስደተኛ/ኢሚግሬሽን ጉዳዮች፣ ከመኖሪያ ቤት ጋ የተገናኘ እገዛ፣ ጤና አጠባበቅ እና ደህንነት እንዲሁም አቢይ የሆኑ ሌሎች የካውንቲ አገልግሎቶች አሰጣጥ በሚሉ ርእሶች ላይ ያተኮሩ ተከታታይ የኦንላይን የመረጃ/ሃብት ማስባሰቢያ ስብሰባዎችን እንደምናካሂድ መግለጽ እንወዳለን። ሙሉውን የመረጃ ማሰባሰቢያ ስብሰባዎች የጊዜ ሰሌዳ እዚህ ማየት ይችላሉ።

ይህን ፈታኝ ወቅት ለማለፍ ከምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በተጓዳኝም ለማህበረሰባችን አባላት መቅረብ ያለባቸውን የአእምሮ ጤና እንቅብካቤ አገልግሎቶችንም ቅድሚያ መስጠት እና በተጠናከረ መልኩ ማስኬድ እንዳለብን ግድ ይላል። ለዛም ነው በቅርቡ እኔ እራሴ ቁልፍ ከሆኑ የተለያዩ የንግድ ዘርፍ መሪዎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር የአእምሮ ጤናን የተመለከተ ስብሰባ ያደረኩት። በወቅቱም በአሁኑ ወቅት እየተተገበሩ ስላሉ ጠቃሚ ስራዎች/ጅማሬዎች በመወያየት፣  አዳዲስ ሃሳቦችን በማጋራት እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል የምናደርገውን የጋራ ጥረት ለማጠናከር ችለናል።

ይህ አሰራራችን በመጪው አመት ለምንሰራቸውን ስራዎች ሁሉ እንደመመሪያ የሚያገለግል ይሆናል። በቀጣይም ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በሚዘጋጁና የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን የተመለከቱ መረጃዎችን ስለምናቀርብ እንድትከታተሉ እናስታውቃለን።

እንደተለመደው ምንም አይነት ጥያቄ ካላችሁ ወይንም እገዛ ከፈለጋችሁ ወደቢሮዬ ጎራ ማለት/ማግኘት ትችላላችሁ።

ከማክበር ሰላምታ ጋር፣

ኬት ስቴዋርት

የምክር ቤት ፕሬዚደንት

በፐርፕል ላይን የቀላል ባቡር መንገድ ግንባታ ተጽእኖ ለደረሰባቸው የአነስተኛየንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ

በፐርፕል ላይን ኝባታ መክንያት አሉታዊ ተጽእኖ ለደረሰባቸው አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ለሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም ምዝገባ ባሁኑ ሰአት ተጀምሯል። ለድጋፉ ብቁ የሚሆኑና የፐርፕል ላይን በሚያልፍባቸው ጠርዝ መንገዶች ላይ የሚገኙ አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች በፐርፕል ላይን ግምባታ ምክንያት በተፈጠረ የመንገድ መዘጋት ወይንም ተለዋጭ መንገድ መፈጠር ምክንያት በስራቸው ላይ የደረሰባቸውን ኪሳራ ለማጣጣት በሚል እስከ $50,000 የሚደርስ ድጋፍ ለያገኙ ይችላሉ። ለዚህ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር የማመልከቻ ማስገቢያ ጊዜ እስከ መጋቢት 14 ይሆናል። ለድጋፉ ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ለማወቅ  Learn more about eligibility requirements የሚለውን ድረገጽ ይጫኑ።

የፐርፕል ላይን ቀላል ባቡር። ፎቶ ከፐርፕል ላይን የተገኘ።

ካውንስሉ “የራስዎን ከረጢት ይዘው ይምጡ” /ቢ ዋይ ኦ ቢ/ የሚለውን ህግ አጸደቀ።

ምክርቤቱ በቅርቡ “የራስዎን ከረጢት ይዘው ይምጡ” / Bring Your Own Bag (BYOB) Bill/ የሚለውን እና አንድ ጊዜ ተጠቅመው የሚጥሏቸውን የመሸመቻ የላስቲክ ከረጢቶች እንዳይጠቀሙ የሚከለክለውን ህግ በቅርቡ አጽድቋል። ከዚህ ህግ መተግበር የሚገኘው ገቢ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ለወደፊቱ ጽዱ የሆነ አየርንብረት ለመፍጠር የሚረዱ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የውሃ ጥራት መጠበቂ ያ ፕሮጀክቶችን ወጪ ለመሸፈን ይውላል። ይህ አዲስ ህግ በስራ ላይ መዋል የሚጀምረው በታህሳስ 1፣ 2026 ይሆናል።

የምክር ቤቱ ፕረሲደንት ኬት ስቴዋርት በካውንስሉ መንበር ላይ ቁጭ እንዳሉ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ከረጢት ይዘው የሚያሳይ ፎቶ።

የተከራዮችን መብት ጥበቃ ማጠናከር

ብዙ ተከራይተው የሚኖሩ ነዋሪዎች ከሚገኙበትን ወረዳ ተወክዬ የተቀመጥኩ የምክር ቤት አባል እንደመሆኔ መጠን ፣የተከራዮችን መብት ለመጠበቅ እና ለማጠናከር የሚረዳውን አዲሱን ረቂቅ ህግ / legislation that would enhance tenant protections / ከሌሎች አባላት ጋር ሆኜ እንዲጸድቅ ሳቀርብ /ኮ ስፖንሰር ሳደርግ/ ኩራት እየተሰማኝ ነበር። የቀረበው ህግ በምክር ቤት አባል ክሪስቲን ሚንክ አነሳሽነት የተዘጋጀ እና ለሚፈጽሟቸው ተደጋጋሚ ለሆኑ የመኖሪያ ቤት ህግ ጥሰቶች አከራዮችን ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ ነው። ይህ ህግ ነዋሪዎቻችን ደህንነቱ የተጠበቀ መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ለማረጋገጥ ያለንን የማያለሰልስ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። በዚህ ህግ መውጣት ሂደት ረገድ ላሳዩት አመራር የምክርቤት አባል ሚንክን ላመሰግን እወዳለሁ።

የካውንስሉ ፕሬዚደንት ኬት ስቴዋርት በነሃሴ 2024 በተካሄደውና በተከራዮች ደህንነት ላይ ያተኮረ የጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት

የመኖሪያ ቤት ባለቤቶች የንብረት ቀረጥ ክሬዲት ብቁነትን ማስፋፋት

የመንግስት የኦፕሬሽን/ስራዘርፎች እና የበጀት ፖሊሲ ኮሚቴ በቅርቡ ካውንቲው ለመኖሪያ ቤት ባለቤቶች ለሚያደርገው የንብረት ግብር ክሬዲት ድጎማ የሚፈለገውን የብቁነት መስፈርት ለማስፋት የሚረዳ ህግ /expand eligibility for the County’s Supplement to the Homeowners Property Tax Credit (HOTC)/ አቅርቧል። ይህ ረቂቅ ህግ /HOTC/ ነዋሪዎቻችን የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖራቸው እና በተለይም ውሱን ገቢ ያላቸው የእድሜ ባለጸጋዎች እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ክፍያ የሚጣልባቸው ወገኖች በመኖሪያ ቤታቸው ተረጋግተው እንዲቆዩ የሚያበረታታ ነው። የሚጸድቅ ከሆነ ይህ ህግ በዛ ላሉ እና ውሱን የገቢ ምንጭ ላላቸው የመኖሪያ ቤት ባለቤቶች  በጣም አስፈላጊ የሆነ የንብረት ግብር ክሬዲት ድጎማ እንዲደረግ ይረዳል። በዚህ ጉዳይ ላይ ለህዝብ ክፍት የሚሆን ሙግት/ስብሰባ በመጋቢት 4 ይካሄዳል።

አነስተና ከእንጨት የተቀረጸ “የንብረት ግብር” የሚል የተጻፈበት የመኖሪያ ቤት ሞዴል።  ፎቶ ካንቫ።

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ

የጥቁሮች ታሪክ የሚታሰብበት ወር

የጥቁሮች ታሪክ የሚወሳበት ወር በዚህ አመት የተከበረው “አፍሪካ አሜሪካውያን እና ስራ” በሚል ብሄራዊ ጭብጥ ነበር።  እኛ የሞንትጎመሪ ካውንቲ አመራሮች በካውንቲው ውስጥ በየአያንዳንዷ እለት በሚያሳዩት ቁርጠኝነተና አመራር ሰጪነት ስራቸው ሃገራችን ከፍ እንድትል ከፍተኛ አስተዋጾ በማድረግ ላይ ያሚገኙትን የአፍሪካን አሜሪካን ሰራተኞች አይተኬ የሆነ አስተዋጽኦ በጣም እናከብራለን። ተመጣጣኝ ክፍያ እንዲተገበር እና የሰራተኞች መብትም እንዲከበር ሲያደርጉት የነበረው ታሪካዊ የሆነ ትግል እና ጥብቅና ማህበረሰባችን እንዲጠናከር እና የበለጠ መሻሻል እንዲመጣ የማነሣሳት አስተዋጽኦ አበርክቷል።  ይህንን በጎ  የሆነ ቅርስ እኛም እኩልነትን እና ፍትሃዊነትን ለማስፈን በምናደርገው የእለት ተእለት ጥረት እናስከብረዋለን።

የምክርቤቱን የጥቁሮች ታሪክ መታሰቢያ ወር አመታዊ አከባበር የሚያሳየውን ቪዲዮ እዚህ ይመልከቱ - Watch the Council’s annual Black History Month video highlight.

በካውንስሉ ጽ/ቤት የተካሄደውን በጥቁሮች ታሪክ መታሰቢያ ወር አከባበር የሚያሳይ የግሩፕ ፎቶ።

የኢሳያስ “ኢኬ’ ሌጊት የስራ አስፈጻሚ ቢሮ የሚገኝበትን ህንጻ እንደገናየመሰየም ስነስርአት

ለካውንቲው ዋና ስራ አስፈጻሚ ክብር በተዘጋጀው የስራ አስፈጻሚ ቢሮው የሚገኝበትን ህንጻ እንደገና የመሰየም ስነስርአት ላይ በመገኘቴ ክብር ተሰምቶኛል።. በካውንቲ ስራ አስፈጻሚነት፣ በምክርቤት ፕሬዚደንትነት እንዲሁም በምክር ቤት አባልነት በቆዩባቸው 28 የአገልግሎት አመታት ሁሉ ኢ ኬ ሌጊት መንግስታችን ለሁሉም ነዋሪ በእኩልነት እንዲሰራ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ይህ እንደገና የመሰየም ተገባር የ ኢ ኬ ሌጊትን ለህዝባዊ አገልግሎት በጽናት መስራት፣ ለእኩልነት እና ፍትሃዊነት መታገል እንዲሁም የህዝብ ተወካይ ባለስልጣናት እንደመሆናችን መጠን እያንዳንዱን የሞንትጎመርይ ካውንቲ ነዋሪ ህይወት መሻሻል መስራት አለብን የሚለውን አደራቸውን የሚያጠናክር ይሆናል። በመሆኑም ይህ ስያሜ የካውንቲው ስራ አስፈጻሚ ለነበሩት ለሌጊት በጣም ክቡር የሆነ እና  የሚመጥን ተግባር ነው።  

የኢሳያስ “ኢኬ’ ሌጊት የስራ አስፈጻሚ ቢሮ የሚገኝበትን ህንጻ እንደገና የመሰየም ስነስርአት

የአእምሮ ጤናን የሚመለከት መረጃ

የቤተሰብ ፍትህ ማእከል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቤተሰብ ፍትህ ማእከል ለማንኛውም በቅርብ አጋር/ወዳጅ በተሰነዘረ ጥቃት እየተጋለጠ ያለ ወይንም ለጥቃት ተጋልጦ የሚያውቅ ግለሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል ነው። በማእከሉ የሚሰጡት ሁሉም አገልግሎቶች በነጻ የሚቀርቡ እና በተለያዩ ቋንቋዎችም የሚሰጡ ናቸው። ምንም ቀጠሮ መያዝ ሳያስፈልግ ወደ ማእከሉ ጎራ ማለት  እና አገልግሎት ማግኘት ይቻላል። የቤተሰብ ፍትህ ማእከሉ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ደህንነትን፣ ጤናን እና ማገገምን እንዲያገኙ  ይረዳል። የበለጠ መረጃ ለማኘት የቤተሰብ ፍትህ ማእከሉን ድረ ገጽ በዚህ አድራሻ Family Justice Center web page ይጎብኙ ወይንም በ(240) 773-0444 ስልክ ይደውሉ።

ሰማያዊ ፊደላት እና ሃምራዊ ቀለም ያላት ቢራቢሮ ያሉት የቤተሰብ ፍትህ ማእከል (MCFJC) አርማ