ውድ ወዳጆቻችን፣
የፌደራል መንግስት በወሰደው እርምጃ የተነሳ በርካታ ነዋሪዎቻችን እየተጎዱ ሲሆን፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ መሪዎች ለማህበረሰቡ አንገብጋቢ የሆኑ መረጃዎችን መስጠት ላይ በቁርጠኝነት ይሠራሉ። በዚህ አዳጋች እና ግራ የሚያጋባ ጊዜ ውስጥ፣ ለማህበረሰብ ዓባላቶቻችን ብቻቸውን እንዳልሆኑ እና የወደፊት ሁኔታቹሁን ለመከላከል የሚያግዙ የመከላከያ እርምጃዎች እንዳሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።
እንደ ጤና እና የሥራ አጥነት መድህን፣ ቀጣይነት ያለው ትምህርት፣ የሠራተኛ ኋይል ልማት፣ እና እንደ መብራት፣ ስልክ፣ ውሃ እና ጋዝ የመሳሰሉ የፍጆታ ወጪዎችን ለመክፈል የሚያስችሉ የአካባቢው ድጋፍ ሰጪ መርሀግብሮች የመሳሰሉት ርእሶች ላይ አንገብጋቢ የሆኑ መረጃዎችን ለነዋሪዎች ለማቅረብ ካውንስሉ ተከታታይ የማህበረሰብ ዌቢናር(በኢንተርኔት የሚደረግ ስብስባ) በማዘጋጀት ላይ ነው።
የመጀመሪያ ስብሰባ የተከናወነው፣ ሴናተር ክሪስ ቫን ቮለን (Chris Van Hollen) እና የካውንቲው ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ኢልርች (Marc Elrich) በተገኙበት ሲሆን የስብሰባው አጀንዳ ለፌደራል ሠራተኞች፣ ሥራ ተቋራጮች እና ለነዋሪዎች ስለሚሰጡት ድጋፎች የሚመለከት ነው። ሁለተኛው ስብሰባ የተካሄደው የአሜሪካን ምክር ቤት አባል ከሆኑት ጄሚ ራስኪን (Jamie Raskin) ጋር በመሆን ሲሆን የስብሰባው አጀንዳ የሚያተኩረው ስለ አዕምሮ ጤና ድጋፍ ሰጪ ግብዓቶች ነው። ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ [Montgomery County Department of Health and Human Services]፣ ሞኮ ፕራይድ ሴንተር ኢንኮፖሬትድ [MoCo Pride Center, Inc.] ኤቭሪማይንድ [EveryMind]፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ብሔራዊ የአዕምሮ ጤና ህብረት [National Alliance on Mental Illness of Montgomery County] (NAMI MC)፣ እና የጥቁር ሀኪሞች እና የጤና ጥበቃ አውታረመረብ [Black Physicians and Healthcare Network] የተውጣጡ ባለሙያዎች በስብሳባው ላይ ተገኝተው ነበር።
ለእርስዎ ትኩረት የሚሰቡ መጪ ስብሰባዎች ላይ እንደሚሳተፉ ተስፋ እናደርጋለን። ቀጣዩ የማህበረሰብ ግብዓት ዌቢናር (በኢንተርኔት የሚደረግ ስብሰባ) የሚከናወነው ማርች 19 ቀን፣ ከምሽቱ 7 p.m. ሰዓት ላይ ነው መጪዎቹን የዌብናር ስብሰባ መርሀግብሮች እዚህ ላይ ይመልከቱ።
እንደ ሁልጊዜ ሁሉ፣ ማንኛውም ዓይነት ጥያቄዎች ያላችሁ ከሆነ እና ድጋፍ የምትሹ ከሆነ የእኔን ቢሮ ለማግኘት ይዘጋጁ።
ከአክብሮት ጋር፣
የካውንስሉ ፕሬዝደንት ኬት ስቲዋርት [Kate Stewart]
ካውንስሉ ኤፕሪል 7 እና ኤፕሪል 8 ቀን ከምሳ ሰዓት በኋላ 1:30 p.m. ሰዓት እና ከምሽቱ 7 p.m ሰዓት ላይ የታቀደውን $7 ቢሊዮን በላይ FY26 የሥራ ማስፈጸሚያ በጀት በተመለከተ የህዝብ ሸንጎ ላይ ይቀመጣል። የእርስዎ አስተያየት የእኛን በብዝሐነት ላይ የተመሰረቱ ማህበረሰቦችን ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስፈልገውን በጀት ካውንስሉ እንዲተምን ይረዳዋል።
አጠቃላይ የቤተሰብ ገቢያቸው $67,000 ወይም ከዚያ በታች የሆኑ የካውንቲው ነዋሪዎች በCommunity Action Agency’s Volunteer Income Tax Assistance (VITA) ፕሮግራም በኩል ነፃ የግብር አከፋፈል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። እስከ ኤፕሪል 10 ቀን ድረስ በርቀት እና በአካል በመገኘት የሚሰጡ ቀጠሮዎች ይሰጣሉ። VITA ግብር ከፋዮች ልክ እንደ Earned Income Tax Credit (EITC) እና Child Tax Credit የመሳሰሉ የግብር ቅናሾችን ማግኘት ላይ እገዛ ይሰጣል። ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥር 240-777-1123 ላይ ይደውሉ ወይም በድረገጽ ላይ ኦንላይን ቀጠሮ ያስይዙ።
Read Across America Weekን ለማክበር ላገዛቹህኝ የሮክቪል ነርሰሪ ትምህርት ቤት እና መዋዕለ ሕፃናት [Rockville Nursery School and Kindergarten] እና ቺልድረስን አፖርቱኒቲ አሊያንስ [Children's Opportunity Alliance] ለማመስገን እወዳለሁ! ማንበብ በሁሉም ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ሰዎች የሚጠቅም ተመራጭ ተግባር ነው እና በጋራ ማንበብ ልጆች የራሳቸውን ድምጽ እንዲያገኙ እና ከሌሎች ለመማር እንዲችሉ የሚያስችል ምርጥ መሣሪያ ነው።
ስለ እኛ አካባቢ አስተዳደር እና ስለ ተግባራቶቹ በቅርብ ትምህርት ካገኙ በኋላ የሮሊንግ ቴራስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት [Rolling Terrace Elementary School] ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በመነጋገሬ ደስተኛ ነኝ። ተማሪዎች ስለ መንግስት አስተዳደራችን እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ አንድ ሐሳብ እንዴት ወደ የሕግ ረቂቅነት እንደሚቀየር እና በመቀጠል እንዴት ሕግ እንደሚሆን ስንወያይ ለመማር ያላቸው ተነሳሽነትን ማየት በጣም አስገራሚ ነበር።
የሴቶች ታሪክ ወር! በየዓመቱ ማርች ወር ላይ፣ ለእኛ አርዓያ የሆኑ፣ ያስተማሩን እና ማህበረሰባችንን የቀረጹ ሴቶችን እንዘክራለን። የፈጠራ ሰዎች፣ መሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ ወይም የምንወዳቸው ሰዎች ይሁኑ፣ መሰናክሎችን ሰብረው ያለፉ እና ለመጪው ትውልድ በር ከፋች የሆኑ ሴቶችን እንዘክራለን። ይሄንን የህዝብ አገልግሎት ስራ ስሰራ በመላው ሕይወቴ ውስጥ ለእኔ ድጋፍ የሰጡኝ እና መሪ የሆኑኝ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሴቶች አሉ። በተለይ አብላጫ የሴቶች ድምጽን የሚወክለው የካውንስሉ አካል በመሆን ለካውንስል የመጀመሪያ ሴት ፕሬዝደንት ስለሆንኩኝ ኩራት ይሰማኛል። የእኔ የሥራ ባለደረባዎች -- የካውንስሉ ዓባላት ማርሊን ባልኮምቢ [Marilyn Balcombe]፣ ናታሊ ፋኒ-ጎንዛሌዝ [Natali Fani-González]፣ ዳውን ሉዴትኬ [Dawn Luedtke]፣ ክሪስቲን ሚንክ [Kristin Mink]፣ እና ላውሪ አን ሳይልስ [Laurie-Anne Sayles] -- በየቀኑ በጥንካሬያቸው፣ በጥበባቸው እና ለሌሎች በሚያሳዩት ርህራሄ ያበረታታኛል።
የመካከለኛው ምስራቅ ቅርስ ወር [Middle Eastern Heritage Month] ማክበር ላይ ከካውንቲው ሥራ አስፈፃሚ እና ከካውንስሉ የተላለፈውን የጋራ መግለጫ በማቅረቤ ኩራት ይሰማኛል። የመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቅርስ [Middle Eastern American heritage] ነዋሪዎች፣ የካውንቲው የመካከለኛ ምስራቅ የአሜሪካ አማካሪ ቡድን [Middle Eastern American Advisory Group] እና የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ [Office of Human Rights] ጨምሮ ተሟጋቾች እና የማህበረሰብ መሪዎች በዝግጁት ላይ ተገኝተዋል።
ባለፈው ሳምንት፣ ከሙስሊም ጓደኞቻችን እና ጎረቤቶች ጋር በመሆን የቅዱስ ረመዳን ወር ሲጀመር በጋራ አክብረናል እና ሁሉም የአሜሪካ ሙስሊም ማህበረሰብ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚሰጡትን አስተዋጽዖ አክብረናል። ይህ የረመዳን ወር ለሚያከብሩት በሙሉ የደስታ፣ የሰላም እና የበረከት ጊዜ ይሁንላቸው። ረመዳን ሙባረክ!
የሮክቪል ቤተመፃሕፍት ተከታታይ የጤንነት እሮብ ቀናት ዝግጅት እንዲሚያዘጋጅ ያውቃሉ? አዕምሮ፣ አካል፣ እና መንፈስ ላይ ለማተኮር ከሳምንት ውስጥ ጊዜ ይመድቡ። ለጤንነት ወርክሾፖች፣ ዮጋ እና የቻክራ ማሰላሰል በየሳምንት እሮብ ምሽት ላይ ይገኙ። በመርሀግብር የተያዙትን ዝግጅቶች ይመልከቱ።
WSSC ውሃ አሁን ያግኙ ፕሮግራም የገቢ-እጥረት ላጋጠማቸው ደንበኞች ያልከፈሉት የውሃ/የፍሳሽ ወጪ ላይ ድጋፍ ይሰጣል። ይሄንን ጊዜያዊ የውሃ ደረሰኝ ክፍያ ድጋፍ ሰጪ መርሀግብርን ይጠቀሙበት እና ስለ ብቁነት መስፈርቶቹ የበለጠ ይረዱ። WSSC Water በመኖሪያ ቤት ውስጥ ለሚከሰቱ የቧንቧ ማፍሰስ ችግሮችን ለመፍታት ከHabitat for Humanity Metro Maryland ጋር አብሮ ይሰራል። አዲሱ CAP ማፍሰስ ጥገና ፕሮግራም የሚያፈሱ ቧንቧዎችን በመለየት እና በመጠገን ደንበኞች ወጪ እንዲቆጥቡ እና ውሃን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳል። መስፈርቱን የሚያሟሉ ደንበኞች የቧንቧ ጥገና አገልግሎቶች ላይ በዓመት እስከ $9,000 ድረስ ማግኘት ይችላሉ። ስለ CAP ማፍሰስ ጥገና ፕሮግራም የበለጠ ይወቁ እና ድጋፍ ለማግኘት ዛሬውኑ ያመልክቱ።
የPepco የሒሳብ ደረሰኞችን በተመለከተ ድጋፍ የሚሹ ከሆነ፣ pepco.com/BillSupport ድር ጣቢያን መጎብኘት እና የPepco የደንበኛ ማስተናገጃ ማዕከልን በስልክ ቁጥር 202-833-7500 ላይ ደውለው ማግኘት ይችላሉ። የPepco አዲሱ ድጋፍ መፈለጊያ [Assistance Finder] መሣሪያ የገንዘብ ድጋፍ፣ የሒሳብ ደረሰኝ ማስተዳደር፣ እና ኋይል ቆጣቢነት እና ወጪ የመቆጠቢያ መረጃዎችን ጨምሮ ደንበኞች ለፍላጎታቸው የሚመጥኑ የተሻሉ ፕሮግራሞችን እንዲያገኙ ያግዛል።