ውድ ጓደኞቼ፣
ስራ የሚደራረብበት የምክር ቤቱ የበጀት ወቅት በይፋ ተጀምሯል። የምክርቤቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ የ$7.7 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ቀመር ያቀረቡ ሲሆን ይሀው የበጀት ፕላን አሁን ወደ ምክርቤቱ ተልኮ ጥንቃቄ የተሞላበት ክለሳ እና ዝርዝር ጥናት ይደረግበታል።
እሴቶቻችን በትራምፕ አስተዳደር የጥቃት ኢላማ በሆኑበት ወቅት፣ በፌዴራል እና በስቴት ደረጃ የበጀት ቅነሳዎች ሊደረጉ በታሰቡበት፣ እንዲሁም የአስተማሪዎች የጡረታን ወጪን የመጋራት የመሳሰሉትን የሚጨምረውን በካውንቲያችን ላይ ስቴቱ ሊያስተላልፍ የሚችለው የበጀት መጋራት ግዴታን የሚሉት ጉዳዮች በምናስብበት ጊዜ ይህ ጊዜ ከታላቁ የአለም የኢኮኖሚ ወድቀት ከተጀመረበት ወዲህ ከተከሰቱ በጣም ፈታኝ ከሆኑ ጊዜያት ይህ አንዱ ነው ብለን መፈረጅ እንችላለን።
በመሆኑም በዚህ ታይተው በማይታወቁ ክስተቶች መሃል በምናልፍበት በአሁኑ ጊዜ ያሉንን ሃብቶች በጥንቃቄ በመመርመር እና ሳይጠበቁ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ነገሮች ቀደም ብለን በመዘጋጀት አስፈላጊ የሆነውን ትምህርትን፣ የህዝብ ደህንነትን እና መሰረታዊ የሆኑ የማህበራዊ አገልግሎቶችን የመስጠት እና የማስቀጠል ቁርጠኝነታችንን ማረጋገጥ መቻል ይኖርብናል።
ስለዚህ በአጠቃላይ የኛ አላማዎች መሆን ያለባቸው ለነዋሪዎቻችን የእለት ተእለት ኑሮ ቁልፍ የሆኑ አገልግሎቶችን ማረጋገጥ እና ማስቀጠል ሲሆን ይህንንም ስናደርግ ደሞ በማያቋርጥ መልኩ የሚከሰቱትንም ተለዋዋጭ ፈተናዎች ጉልህ እና ግልጽነት በተሞላው መልኩ መከታተልና እርምጃ መውሰድ ያስፈልገናል።
የማህበረሰቦቻችንን ፍላጎቶች ማእከል አድርገን መንቀሳቀስ የሚለውን የስራ ባህላችንን የምንቀጥልበት ሲሆን ይህንንም ስናደርግ ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ የኢኮኖሚ ማእበሎችና የኮቪድንም አደጋ ጭምር በአግባቡ እንድንታገለው ያስቻለንን በጀትን በአግባቡ የመምራት ተግባራችንም ማስቀጠል ይኖርብናል።
በመሆኑም በበጀት አፈጻጸሙ ሂደት መሃል አንዱ ቁልፍ የሆነው ተግባር ነዋሪዎቻችን የሚሉትን ማዳመጥ ነው! የናንተ አስተያየት እና ሃሳብ የእያንዳንዱን የሞንትጎመሪ ካውንሪ ነዋሪ ጥቅም የሚያስከብር በጀት ለመቅረጽ ይረዳናል።
በሚያዝያ 7 እና 8 ከ 1:30 ፒ ኤም እና 7 ፒ ኤም በሚደረጉ የ 2026 የበጀት አመት የክርክር መድረኮች በአካል ወይንም በኢንተርኔት ይካፈሉ ወይንም በአጠቃላዩ የበጀት ሂደት በማናቸውም ሰአት ምስክርነትዎን ይስጡ ።
ከማክበር ሰላምታ ጋር፣
ኬት ስቴዋርት
የካውንስሉ ፕሬዘደንት
‘ለአገልግሎት እና እገዛ እንተባበር” የዌቢናር ስብሰባዎች አሁን እስከ መጪው ሃምሌ ድረስ ባሉት ጊዜያት ፕሮግራም ወጥቶላቸው ይካሄዳሉ። እነኚህ የስልጠና ፕሮግራምች በካውንስሉ የተዘጋጁት በፌዴራል ደረጃ እየተፈጠሩ ባሉ ተግዳሮቶች ምክንያት ተጽእኖ የደረሰባቸውን የፌደራል ተቀጣሪ ሰራተኞችን እና የማህበረሰባችንን አባላት ለመደገፍ ነው። እያንዳንዱ ስብሰባ በአንድ ልዩ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሲሆን በዚህም ላይ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችን፤ ተግባራዊ የሆኑ መፍትሄዎችን በማመንጨት እንዲሁም ያሉትን ተግዳሮቶች ለይቶ በማወቅ የነዋሪዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን የሚያጋሩ ባለሞያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል። በመጪው እሮብ ሚያዚያ ሁለት በ 7 ፒ ኤም ላይ የሚካሄደው ስብሰባም ከፌደራል ሰራተኝነት ወደ ሌሎች አዳዲስ የስራ እድሎች የሚሸጋገሩ ሰራተኞች ላይ የሚያተኩር ይሆናል።
ሙሉውን ፕሮግራም እዚህ ይመልከቱ View the full schedule.
በካውንስሉ ምክትል ፕሬዚደንት ዊል ጃዋንዶ የቀረበውን ለተፈናቀሉ የፌደራል ሰራተኞች በሞንትጎመሪ ካውንቲ መንግስት ውስጥ ቅድሚያ የቅጥር እድል የሚፈቅደውን ረቂቅ ህግ አብሬ ሳቀርብ/ ኮስፖንሰር በማድረጌ ኩራት ይሰማኛል። ይህ የቅጥር ቅድሚያ የመስጠት ህግ በፈዴራል ደረጃ ለተደረገው እና በአሁኑ የትራምፕ አስተዳደር ጊዜ ግምት ከ 1000 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ስራቸውን በማሳጣት በሞንትጎመሪ ካውንቲ መንግስት ላይ ትልቅ ተጸኖ ያመጣውን የስራ ቅነሳ ምላሽ የሚሰጥ ነው። ለተፈናቀሉ የፌደራል ሰራተኖች የስራቅጥር ቅድሚያ በመስጠት ይህ ህግ ብዙ የስራ ልምድ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች አዳዲስ እድሎችን በመፍጠር ሊከተል የሚችለውን የፋይናንስ አለመረጋጋት ለመቀነስ እንደሚረዳ ይታመናል። በዚህ ባልተረጋጋ ወቅት የካውንቲው መሪዎች በትራምፕ አስተዳደር ያልተጠበቁ እርምጃዎች ምክንያት ተጽእኖ ለደረሰባቸው ነዋሪዎች መጠነ ሰፊ ስራዎችን በመስራት እና እድሎችን ለመፍጠር በመትጋት ላይ ይገኛሉ።
በሚያዚያ 1 ለህዝብ ክፍት የሆነ ውይይት ይካሄዳል።
በአሁኑ ጊዜ ካውንስሉ የነዋሪዎችን የአእምሮ ጤና አገልግሎት ድጋፍ ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እየቀጠለበት ይገኛል። የስነባህሪ ጤና መጓደልን ክፍል ለማሻሻል እና የተንቀሳቃሽ የአደጋ መከላከል ቡድን (MCOT) የተባለውን የሙከራ ፕሮግራም በገንዘብ ከመንግስት በተደረገ ወጪ ለመደጎም በቅርቡ የሶስት ሚሊዮን ብር በጀት አጽድቀናል። የገንዘብ እርዳታው በተለይ ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዲቀጠር እና የማረጋጊያ ክፍሉን በማጠናከር እና በመተግበር ስለሚያግዝ በዚያውም የአገልግሎቶቹን አሰጣጥ አቅም እና ተደራሽነት በእጅጉ እንደሚያሻሽል ይታመናል።
እኔም እራሴ የአደጋ መከላከል ማእከሉን የመጎብኘት እና ከአደጋ መከላከል ቡድኑ ጋርም አብሬ የመጓዝ እድል ያጋጠመኝ ሲሆን በዚህም አጋጣሚ ቡድኑ ለማህበረሰባችን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአይኔ ለመመልከት ችያለሁ። ቡድኑ ከስነባህሪ ጤና ጋር የተያያዙ ድንገተኛ ችግሮችን ለመታደግ 24 ሰአታት እና 7 ቀናት ሙሉ ይሰራል። የአደጋ ሁኔታ ግምገማ በማካሄድ አደጋዎችን መቆጣጠር፣ እና ህክምናን መስጠት እና ወደ ሌሎች ሆስፒታሎችም ረፈራል እና መረጃ የመስጠት ስራዎችንም ያከናውናል። የአደጋ መከላከል ማእከሉን በ (240) 777-4000 ስልክ በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ መምሪያ የ 78ኛ ተመራቂዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። ይህ ድንቅ የሆነ የተመራቂዎች ቡድን የስልጠና አካዳሚውን የጨረሰ በመሆኑ አሁን በመላው ካውንቲ የነዋሪዎችን ደህንነት የመጠበቅ ስራ ላይ ይሰማራል። አዲሶቹ የህግ አስከባሪ አካላት ማህበረሰባችንን ለመጠበቅ እና ለማገልገል ፈቃደኛ ስለሆናችሁ እናመሰግናለን።
የሚንትጎመሪ ካውንቲ የቤት አልባዎች ጥምረት ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ሱሲ ሲንክሌር ስሚዝን በጡረታ መገለል ለማክበር በተዘጋጀው ስነስርአት ላይ በመሳተፌ ክብር ተሰምቶኛል። ሱሲ ሙሉ ህይወታቸውን ሌሎችን ለመርዳት እና በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ነዋሪዎችን በማገዝ ስራ አሳልፈዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቤት አልባዎች ጥምረት በየአመቱ በግምት 1600 አዋቂ ወንድ ሴት እንዲሁም ህጻናትን የሚረዳ ሲሆን አላማውም ቤት አልባነት እየቀረ እንዲሄድ፤ ጊዜያዊ እንዲሆን እና እስከናካቴውም ቤት አልባነት እንዲወገድ ጥረት ማድረግ ነው። ለብዙ አመታት ለሰጡት አገልግሎት እና ድጋፍ ሱሲን እናመሰግናለን።
ስር የሰደደ የዘረኝነት እና የእኩልነት አለመኖር በሜሪካ ባሉ የጥቁር ማህበረሰቦች ላይ የሚታይን የአእምሮ ጤና ችግር የማባባስ ሁኔታ ይፈጥራል። በአእምሮ ላይ ያተኮሩ ስራዎች በጤነናም በታማሚም የህብረሰብ አባላት ላይ የአእምሮ ጤና መሻሻልን ሲያመጡ ታይተዋል።
የአፍሪካን አሜሪካን የአእምሮ ጤና ትኩረት ፕሮግራም/AAHP/ በነጻ በዙም/ኢንተርኔት የሚቀርብ ፕሮግራም ሲሆን አላማውም አእምሮአዊ እና ስሜታዊ ጤንነትን መደገፍ ነው። የሚያተኩረውም በመረጃ ላይ በተመረኮዘ እና የጭንቀትን ዳግመኛ መከሰት የሚከላከል የአእምሮ ተኮር ቴራፒ በመስጠት ላይ ነው። ከ 100 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች ፕሮግራሙ ከተጀመረበት ከ2022 አመተ ምህረት ጀምሮ የተሳተፉ ብዙ ሰዎችም በደህንነታቸው ላይ መሻሻልን አይተዋል።
ይህ ትምህርት ልዩ የሆነ እና ግለሰቦች በየቀኑ በአስሮች የሚቆጠሩ መልመጃዎችንና የተግባር ልምምዶችን የሚያደርጉበት ነው።
የፕሮግራሙ ውጤቶች:
ይህ የስድስት ወር ፕሮግራም በሚያዝያ 8 ይጀምራል። በሚከተለው አድራሻ ይመዝገቡ፤ https://tinyurl.com/aahpmindful2025.