Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - April 9, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቼ፣

እንደምታውቁት የፌዴራል ተቀጣሪ ሰራተኞቻችን የአሁኑ መንግስት አስተዳደር በሚወስዳቸው ሃላፊነት የጎደላቸው ውሳኔዎች እና ጭካኔ የተሞላቸው ድርጊቶች ምክንያት ከመቼውም ጎዜ በበለጠ መልኩ አስቸጋሪ በሆነ ውጥንቅጥና ማስፈራራት ላይ ይገኛሉ።

ከምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር 3,500 ሰራተኞችን ጨምሮ ከጤና ዕና የሰብአዊ አገልግሎት መስሪያ ቤት በአጠቃላይ 10,000 ሰራተኞችን ለመቀነስ የትራምፕ አስተዳደር የወሰደው ድንገተኛ ውሳኔ የሃገራችንን እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ መስሪያ ቤቶችን የሚጎዳ እና ቀጥተኛ በሆነ መልኩም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚጎዳ ነው።

እነኚህ የመንግስት ሰራተኞች የሁሉንም አሜሪካውያን ደህንነት እና ጤንነት ለማረጋገጥ ቀን ከቀን የሚተጉ ናቸው። እኔም ማህበረሰቦቻችንን እና በአጠቃላይም ሃገራችንን በትጋት እና በቅንነት ለማገልገል ለመረጡት ለእነኚህ የመንግስት ሰራተኞች ምስጋናዬን ለማቅረብ እና ለነሱ የሚናደርገውንም ድጋፍ እንደምንቀጥልበት በድጋሚ ለማረጋገጥ እወዳለሁ።  

የፌደራሉ አስተዳደር በወሰዳቸው እርምጃዎች ምክንያት ከስራ የተቀነሱ ውይንም ጉዳት የደረሰብዎት ከሆነ ወይንም ሌላ በተመሳሳይ መልኩ ተጸእኖ የደረሰበት ሰው የሚያውቁ ከሆነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ክስተቶች እና እድሎችን ቢመለከቱ ሊጠቀሙ ይችላሉ፤

እንደተለመደው ምንም አይነት ጥያቄ ካላችሁ ወይንም እገዛ ከፈለጋችሁ ወደ ቢሮዬ በመደወል/ማግኘት ይቻላል።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

ኬት ስቴዋርት

የካውንስል ፕሬዚደንት

በሚያዝያ  23 11:30 ኤ ኤም የሚካሄደው ለአገልግሎት እንተባበር ዌቢናር መረጃ

ካውንስሉ ለቤት ባለቤቶች የንብረት ግብር ክሬዲት ብቁነት መስፈርትን አሳደገ

በመንግስት የስራ ሂደት እና የበጀት ፖሎሲ ኮሚቴ የተደገፈውን የቤት ባለቤቶች የግብር ክሬዲት ረቂቅ ህግ እኔ በሊቀመንበርነት በምመራው በካውንስሉ ሙሉ ድጋፍ መጽደቁን ሳበስር ክብር ይሰማኛል። ረቂቅ ህጉ በካውንቲው የሚደገፈውን የሜሪላንድ እስቴት የቤት ባለቤቶች የግብር ክሬዲት ብቁነት የሚያሰፋ ሲሆን ይህም እገዛ በተለይ ውሱን ገቢ ላላቸው የእድሜ ባለጸጋ ነዋሪዎች  እንዲሁም የግብር ክፍያ መጨመር ተጽእኖ ላደረገባቸው ሌሎች ነዋሪዎች በጣም ጠቃሚ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። ስለተስፋፋው የብቁነት መስፈርት እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ላይ  እዚህ በመጫን መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የሚያጎላ መስተዋትና የፒጊባንክ ከበስተጀርባው የሚታዩበት የሞዴል መኖሪያ ቤት

የተከራዮችን ጥበቃ ለማጠናከር የተቀረጸ የሸማቾች ጥበቃ ረቂቅ ህግ

ከውንስሉ በቅርቡ የሸማቾች ጥበቃ ቢሮ ከአከራይ ተከራይ ጉዳዮች ጋር የሚያያዙ እና ትክክለኛ ያልሆኑ የንግድ አካሄዶችን በተጠናከረ መልኩ እንዲከታተል እና ለተከራዮች ጠንካራ የሆነ ጥበቃን የሚያጎናጽፈውን እንዲያስጠብቅ የሚያስችለውን 6-25 የተባለውን ረቂቅ ህግ አውጥቷል። የተከራዮችን ጥበቃ ማጠናከር በአጠቃላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎችን ክብር እና ደህንነት ለማስጠበቅ እና ለማረጋገት ቁልፍ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ሁሉም ነዋሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸውን የሚያስችለውን ረቂቅ ህግ እንዲጸድቅ እኔም በጋራ ስደግፍ/ ኮስፖንሰር ሳደርግ እና በሙሉ ድምጽ ሲጸድቅ ሳይ ኩራት ይሰማኛል። ይህንን ረቂቅ ህግ ማዘጋጀት እና በመምራት እንዲሁም ተገቢ ያልሆኑ የንግድ አካሄዶችንም በመዋጋት እረገድ ላደረጉት አስተዋጾ የምክርቤቱ አባል የሆኑትን ክሪስቲን ሚንከንን ላደንቅ እወዳለሁ።

ስቴዋርት በ 2023 በተካሄደው የኪራይ ተመን ማረጋጊያ ህግ የፊርማ ስነስርአት ላይ ንግግር ሲያደርጉ

የሞንትጎመሪ ካዊንቲ የክፍት የስራ ቦታዎች ቦርድ

በካውንቲው የስራ አመራር ቦርድ ኮሚቴዎች እንዲሁም ኮሚሲዮኖች ላይ የሚኖር የህዝብ ተሳትፎ የካውንቲው ስራ እንዲቀላጠፍ ከመርዳቱም በላይ ለማህበረሰቡም ጠቃሚ የሆነ አገልግሎት ለማቅረብ ይረዳል። በመሆኑም በአሁኑ ሰአት በቤተዝዳ የከተማ ጥምረት ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲሁም በኢስት ካውንቲ የዜጎች አማካሪ ቦርድ ውስጥ ለመሳተፍ እድሎች አሉ። የማመልከቻ ጊዜው የመጨረሻ ቀነ ገደብ ሚያዝያ 14 ነው።

ለቦርድ፣ ለኮሚቴ እና ለኮሚሽን ቦርድ የስራ ማስታወቂያዎችን ለማየት እና ለማመልከት እዚህ ይጫኑ።

‘አሁኑኑ ያመልክቱ’ የሚል የተጻፈባቸው የተለያየ ቀለም ያላቸው ስቲከሮች

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ለቢዝነስ ክፍት ነው

በካውንቲው የግዢ ቢሮ በተዘጋጀው እና ሞንትጎመሪ ካውንቲ ለቢዝነስ ዝግጁ ነው በሚለው የጥምረት/ፓርትነርሺፕ መፍጠሪያ  ዝግጅት ላይ ንግግር በማድረጌ ደስተኛ ነኝ። ይህ ዝግጅት የፌደራል ኮንትራክተሮች ከበታች በየመዋቅሩ ካሉ የመንግስት አካላት ጋር እንዲገናኙ፤ አብረው እንዲሰሩ እና አዳዲስ እድሎችንም አብረው እንዲያመቻቹ እድል የሚፈጥር ክስተት ነበረ። ኮንትራክተሮች በፌደራል የበጀት አመዳደብ ላይ በሚደረጉ ለውጦች አማካኝነት ተጽእኖ እየደረሰባቸው ባለበት በአሁኑ ወቅት በጣም አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን  እና ፕሮጀችቶችን ለማህበረሰባችን በማቅረብ እና ለመተግበር እንዲሁም የተለያዩ ቢዝነሶችን እና እድሎችን ለማቅረብ ቀጣይነት ባለው መልኩ መስራታችንን እንቀጥላለን። በታም ፈታኝ በሆኑ ወቅቶችም ቢሆን የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት የሆኑትን የአካባቢ ሰራተኞች፣ የንግድ ተቋማት እና ነጋዴዎች ለማገዝ እንጥራለን።   

በካውንቲው ‘ለቢዝነሥ ክፍት ነን’ ዝግጅት ወቅት የካውንስሉ ፕሬዚደንት ስቴዋርት ከ ዳብሊው ጄ ኤል አ ከተባለው የዜና ማሰራጫ ባልደረባ ሌልየ ሊን ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ

ሴቶቻችን ታሪክ እየሰሩ ነው

የተለያዩ ማነቆዎችን በመስበር ለወደፊት ትውልዶች የተለያዩ እድሎችን ለመፍጠር አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሴት እህቶቻችንን ለማሰብ በተዘጋጀው እና የሴቶች ታሪክ ወር ተብሎ በተሰየመው ማብቂያ ላይ የተደረጉ የተለያዩ ልዩ ዝግጅቶችን ለማየት በመቻሌ እና በዚህ ታላቅ አከባበር ላይም በመገኘቴ ክብር ተሰምቶኛል። በዚህ በካውንስሉ አባል በሆኑት ላውሪ አን ሳይልስ በተዘጋጀው ክስተት ላይ  ከተገኙት ልዩ እንግዳዎች ዩ ኤስ ሴኔተር አንጄላ ኦልሶብሩክስ እና የሴቶች ለሴቶች የመማማር ድርጅት አስፈጻሚ ዳይሬክተር ከሆኑት አማንዳ ዊተነር ጋር አብሬ በዚህ የሴቶች ታሪክ መዘከሪያ ወር ላይ በመሳተፌ ደስታ ተሰምቶኛል። ታሪክ ሰሪ ሴቶች በተባለው የሽልማት ስነስርአት ላይም ተሳትፌያለሁ። በዚህ አመት በአጠቃላይ ለሙያቸው እና ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች/ማህበረሰቦች አስተዋጽኦ  ላደረጉ  32 ልዩ የሆኑ የክብር ተሸላሚዎች እውቅና ሰጥተናል።

በሴቶች ታሪክ መዘከሪያ ወርን በማስመልከት በተዘጋጀው ስነስር አት ላይ ስቴዋርት ንግግር ሲያደርጉ

ተሻጋሪ ጾታ/ትራንስ የማህበረሰብ አባላትን የማጉላት ቀን

የተሽሻጋሪ ጾታ/ ትራንስ የማህበረሰብ አባሎቻችንን የማጉላት ቀንን ለማሰብ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የፕራይድ ማእከል እና ሊቭ ኢን ዩር ትሩዝ የተባለው ድርጅቶች ላደረጉት በጣም ልዩ የሆነ ዝግጅት ላመሰግናቸው እወዳለሁ። የትራንስ ማህበረሰብ አባሎቻችን መደመጥ፣ መጠበቅ እና መወደስ ይገባቸዋል! በትራንስ ማህበረሰቦቻችን የማወደሻ ቀን እንዲሁም በእያንዳንዱ ቀን እሴቶቻችንን በማክበር የኤል ጂ ቢ ቲ ፕላስ ማህበረሰብ አባሎቻቻንን በክብር ማሰብ እና ለነሱም ጥብቅና ልንቆም ይገባል።

ስቴዋርት በትራንስ ማህበረሰብ አባላት የመተዋወቂያ ዝግጅት ላይ ንግግር ሲያደርጉ

የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች ምርቃት

የላቲኖ ጤና ኢኒሺዬቲቭ የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች ሰርቲፊኬሽን ስልጠና ፕሮግራም ተመራቂዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።እነኚህ ተመራቂዎች የጤና አጠባበቅ አሰራሮችን እና አተገባበርን የተመለከቱ ስልጠናዎችን እንዲሁም ተገልጋዮች ለጤና እንክብካቤ የሚኖራቸውን ተደራሽነት ለማሳደግ የሚያስችላቸውን ስልጠና ወስደዋል። እነኚህ ሰልጣኝዖች ነተጨማሪም የተለያዩ አጋዥ አገልግሎቶችንና ሃብቶችን ለማቅረብ እንዲሁም ተገቢ አገልግሎቶችን በበቂ ሁኔታ ለማይደርሳቸው የማህበረሰብ አባላት አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ የጤና ባለሞያዎች ቁጥር ከማሳደግ አንጻር አስተዋጾ የሚያደርጉ ናቸው።

ተመራቂዎችጥቁር እና ነች የላቲኖ የጤና አጠባበቅ ፕሮግራም/ኢኒሺዬቲቭ ማስታወቂያ ባነር  ፊትለፊት ከ ካውንስል ፕሬዚደንት ስተዋርት ጋር የተነሱት ፎቶ

የአረብ አሜሪካውያን ቅርስ ማሰቢያ ወር

ሞንትጎመሪ ካውንቲ ሚያዝያ የአረብ አሜሪካውያን ቅርስ የማሰቢያ ወር እንዲሆን እውቅናውን ይሰጣል። ከማህበረሰብ መሪዎች እና የአረብ አሜሪካን የማህበረሰብ አባላት  ጋር በመሆን የማህበረሰቡን ታላቅ ታሪክ እና አስተዋጽኦ የሚያጎላውን እና ለአረብ አሜሪካውያንን ስኬት እውቅና የሚሰጠውን የካውንስሉን የአረብ አሜሪካውያን ቅርስ ማሰቢያ ወር እወጃ ስናደርግ ክብር ተሰምቶናል።

የአረብ አሜሪካውያን ቅርስ ማሰቢያ ወር

እምሮ ጤና ኮርነር

የአእምሮ ጤና የቪዲዮ ዝግጅት

የአእምሮ ጤና የሁላችንንም የህይወት የሚነካ እንደመሆኑ መጠን በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን እና ሃብቶችን ለማጉላት እና ለማስፋፋት የሚረዱ የአእምሮ ጤና የቪዲዮ ፕሮግራሞችን እንዲዘጋጁ አድርጌያለሁ። በመጀመሪያ የተዘጋጀውም የቻይናውያን የባህል እና የማህበረሰብ አገልግሎት ማእከል የሚሰራቸውን ታላቅ ስራዎች የሚያሳየው የቪዲዮ ዝግጅት ነው።

ቪዲዮውን እዚህ ይመልከቱ

CCACC group photo

ናሚዎክስ ሞንትጎመሪ ካውንቲ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአእምሮ እመም ብሄራዊ ጥምረት /National Alliance on Mental Illness of Montgomery County (NAMI MC)/ የተባለው ድርጅት የአእምሮ ጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው እገዛ፣ ትምህርት እንዲሁም የማንቂያ ስራዎችን የሚያካሂዱ የማህበረሰብ ጥምረቶችን ለማገዝ እና ለማስፋፋት የሚሰራ ተቋም ነው። ለግለሰቦች እና ቤተሰቦቻቸው ነጻ የእገዛ ቡድኖችንና የስልጠና ክፍለጊዜዎችን ያዘጋጃል።

ናሚዎክስ ሞንትጎመሪ አመታዊ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የናሚዎክስ ቅዳሜ ግምቦት 3 በ 9 ኤ ኤም በጌትስበርግ በሚገኘው የሪዮ ሌክፍሮንት  ዝግጅት ነዋሪዎች እንዲሳተፉ ይጋብዛል። ከተለያዩ አካላት ጋር ለመገናኘት እና እጅግ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ የጤና ፕሮግራሞች ገንዘብ ለማሰባሰብ ለመርዳት ናሚዎክስን ይቀላቀሉ። ለተጨማሪ መረጃ እና ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

በናሚዎክስ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ተሳታፊዎች እጅብ ብለው ተሰባስበው የሚያሳይ ፎቶ