Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - April 23, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቼ፤

የሞንትጎመሪ ካውንቲ በኋይት ሃውስ አማካኝነት በተፈጸመው የፌደራል ሰራተኞች ቅነሳ እና አጠቃላይ ምስቅልቅል ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የካውንቲውን ነዋሪዎች እና ቤተሰቦችን ማገዙን አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት በሲልቨር ስፕሪንግ በሜሪላንድ ስቴት እና በበታች የአካባቢያዊ አካላት አዘጋጅነት የተካሄደው የስራቅጥር ኤግዚቢሽን በአካባቢ እና በስቴት ደረጃ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ውስጥ ከሚገኙ ቀጣሪዎች ጋር ለመገናኘት በሚፈልጉ የስራ ፈላጊዎች ተሞልቶ ነበር የሰነበተው። በነዚህ ክስተቶች መገኘት አልቻሉ ከሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ዝግጅቶች ላይ ለመካፈል በአካባቢያችን ዙሪያ የሚገኙ የስራ እድሎች እና የመረጃ ኤግዚቢሽኖች የሚለውን ድረገጽ ይጫኑ።

ካውንስሉ በአሁኑ ጊዜ ለአገልግሎት እና እገዛ እንተባበር የዌቢናር ስብሰዎችን በየሁለት ሳምንቱ ማዘጋጀቱን የቀጠለ ሲሆን በዚህም ዌቢናር ላይ የካውንቲው ነዋሪዎች የሚፈልጓቸውን እገዛዎች በተገቢው መልኩ እንዲያገኙ የሚረዱ ከተለያዩ ባለሞያዎች የሚሰጡ ሃሳቦች፣ የመረጃ ሃብቶች፣ እንዲሁም በተለያዩ በጣም ጠቃሚ የሆኑ አርእስቶች ላይ የሚያተኩር ውይይቶች ይደረጋሉ።

ቀጣዩ ዌቢናር የሚካሄደው ዛሬ በ 11:30 ኤ ኤም ሲሆን በካውንስል አባል ናታሊ ፋኒ ጎንዛሌዝ አስተናባሪነት የሚካሄድ እና በተለይ የሚያተኩረውም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኢንተርፕረነርሺፕ ስነምህዳር/ኢኮሲስተም፤ የቢዝነስ ስራ ፈጣሪዎች እና ለፌደራል ተቀጣሪ ሰራተኞች የሚያስገኙት እደል በሚለው ርእስ ላይ ይሆናል። ዛሬ በ 11:30 ኤ ኤም ላይ በዙም በሚካሄደው ወቢናር ላይ ለመሳተፍ በዚህ ድረገጽ ይመዝገቡ። ዛሬ መሳተፍ ካልቻሉ የዌቢናር ማካሄጃ ሙሉ ፕሮግራሙን ይህን የካውንስሉን የዩትዩብ ገጽ በመክፈት ዝርዝሩን ማግኘት ይችላሉ።

ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ በምንጣጣርበት በዚህ ወቅት እርስ በርሳችን በመደጋገፍ፣ ጎሬቤቶቻችንን በመንከባከብ እንዲሁም አብረን በመስራት እና በመተባበር ይሄን ጊዜ በጋራ በመሆን እንወጣዋለን   -  ይህ ነው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሁልጊዜም አካሄድ።

እናንተን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ፤

ኬት ስቴዋርት

የካውንስል ፕሬዚደንት

የካውንቲው ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢርሊች፤ የካውንስሉ ፕሬዚደንት ስቴዋርት እና ሌሎች የካውንቲው መሪዎች “የመንግስት ሰራተኞችን አግዙ” እና “ለመንግስት ሰራተኞች እናመሰኛችኋለን” የሚሉ ምልክቶችን ይዘው ባአንድነት በመንበር ላይ ቆመው የሚያሳይ ፎቶ.

ኪልማር አብሬጎ ጋርሲያን ወደቤቱ አምጡት

ባለፈው ሳምንት ከሜሪላንድ የላቲኖ ተወካይ ቡድን/ ኮከስ ጋር አብሬ በመሆን ፣ ከላቲኖ መሪዎች፣ በህዝብ ከተመረጡ ባለስልጣናት፣ እንዲሁም በመቶዎች ከሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን ሴኔተር ክሪስ ቫን ሆለን የህግ መብቱን ባልጠበቀ መልኩ ባለፈው ወር ከሃገር እንዲባረር የተደረገውን እንዲሁም የትራምፕ አስተዳደር የፍርድ ቤቶችን ትእዛዝ ባለማክበር ሊመልሰው ፈቃደኛ ያልሆነውን  ኪልማር ዲያጎ ጋርሲያን የተባለውን የሜሪላንድ ነዋሪ ወደ ቤቱ ለማስመጣት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍ አብረን መቆማችንን አሳይተናል። በዚህ መልኩ መሰረታዊ የሆኑ ህገመንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አደጋ ላይ በሚወድቁበት ጊዜ ሁላችንም ድምጻችንን ማሰማት እና በታሪክ ፊት ከትክክለኛው ወገን መቆማችንን ማሳየት ይኖርብናል። ሴኔተር ክሪስ ቫን ሆለን ለሚያደርጉት ልበ ሙሉነት የተሞላው አመራር አመሰግናቸዋለሁ።

“ኪልማር ዲያጎ ጋርሲያን ወደቤቱ እናምጣው” የሚል ምልክት ባለበት መንበር ላይ  የካውንስሉ ፕሬዚደንት ስቴዋርት በህዝብ በተመረጡ ባለሰልጣናት እና ደጋፊዎች ታጅበው ንግግር ሲያደርጉ የሚያሳይ ፎቶ።

በበጀት ላይ በሚደረጉ ህዝባዊ ክርክሮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስተያየትሰጡ

በቅርቡ በተካሄዱ አሚስት የበጀት ህዝባዊ ክርክሮች ላይ 230  ነዋሪዎች በአካል ተገኝተው ምስክርነት የሰጡ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ በጽሁፍ፣ በድምጽ እና በቪዲዮ ምስል ምስክርነት እና አስተያየታቸውን አቅርበዋል። ሁላችሁም በህዝባዊ ክርክሩ ላይ በአካል ለተገኛችሁ፤ በድረገጽ/ኦንላይን ለተከታተላችሁ እና በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ ሃሳባችሁን ላካፈላችሁ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ለ2026 አ ም የተመደበውን የ7.7 ቢሊዮን ዶላር የስራማስኬጃ በጀት በተመለከተ በተለያዩ ኮሚቴዎች አማካኝነት በመከራከር እና በምንሰጣቸው አስቸጋሪ የሆኑ ውሳኔዎች እና አጠቃላይ ሂደት ላይ የናንተ ግብረመልስ እና አስተያየት ዕገዛ እንደሚያደርግልን ለመግለጽ እንወዳለን።

በበጀት ላይ በሚደረጉ ህዝባዊ ክርክሮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስተያየት ሰጡ

ለእንክብካቤ ሰጭ ሰራተኞች በ$10 የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ በአሁኑ ሰአት በበተዝዳ፣ በሲልቨርስፕሪንግ እና ዊተን አካባቢ ለሚኖሩ ቤት አልባዎች እንክብካቤ ለሚሰጡ እና መስፈርቱን ለሚያሟሉ የህጻናት እንክብካቤ ሰጪዎች የቅናሽ የመኪና ማቆሚያ ፈቃድ በመስጠት ላይ ይገኛል። ይህን አስፈላጊ ለሆኑ የአገልግሎት ሰጪዎች ወጪ ለመቀነስ የሚረዳ አሰራር ከጅምሩ ጀምሮ የመራሁት እኔ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል። ለህብረተሰባችን እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለሚያቀርቡ አካላት ተመጣጣኝ እና በቀላሉ ተደራሽነት ያለው የትራንስፖርት አማራጭ ማቅረብ የነሱን በጎ ስራ ማገዝ የምንችልበት አንዱ መንገድ ነው። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ያግኙ.

በዳውንታውን አካባቢ ለሚገኙ የመኪና ማቆሚያ ጋራጆች የፓርኪንግ ምልክት እና ቀስት ያለው ቅስት

የጠርዝ ላይ የኤሌክትሮኒክ ባትሪ መሰብሰቢያዎችን ማስፋፋት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ በጥሪ/ኦን ኮል የኤሌክትሮኒክስ እና የባትሪዎችን የመሰብሰብ ስራን በማካተት የጠርዝ ላይ የእንደገና ጥቅም ላይ የማዋል ፕሮግራምን በማስፋፋት ላይ ይገኛል። ይህ አገልግሎት ገና እየተጀመረ ሲሆን ከካውንቲው የእንደገና ጥቅም ላይ የማዋል አገልግሎት እያገኙ ላሉ ተጠቃሚ ነዋሪዎች የጥሪ አገልግሎቱ በታህሳስ 1 2025 እንደሚጀምር ይጠበቃል።  የመሰብሰብ የጥሪ አገልግሎት ቀጠሮ ከማስያዝዎ በፊት ፕሮግራሙ ስለመጀመሩ በፖስታ ማሳወቂያ ደብዳቤ ሊደርስዎት ይገባል።ያስታውሱ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች እና ባትሪዎች በጠርዝ ላይ በሚገኙ የእንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ እቃዎች ማከማቻ ላይ ወይንም ከመደበኛ ቆሻሻ ጋር መቀላቀል አይችሉም፤ ምክንያቱም እሳት የማስነሳት አደጋ/ስጋት ስለሚያመጡ ነው! ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ይጫኑ.

የእንደገና ጥቅም የሚውሉ እቃዎች ማጠራቀሚያ.

የሞንትጎመሪ የፕላን አካዳሚን ይቀላቀሉ

የሞንትጎመሪ የፕላን መምሪያ በሰኔ ወር ለሚጀመረው የማህበረሰብ የፕላን አካዳሚ የምዝገባ ጥያቄ ፎርሞችን እየተቀበለ ይገኛል።  በመሆኑም በአካባቢዎ ስለሚተገበር የፕላን አወጣጥ ሂደት እንዲሁም ስለ ዞን አከላለል፣ ስለማስተር ፕላን አወጣጥ እንዲሁም ሌሎች ማህበረሰቡ ላይ ተጸኖ ስለሚያሳድሩ ቁልፍ ጉዳዮች ማወቅ ጥቅም ይኖረዋል። በመጭው የፎል/መሀር ወቅት በአጠቃላይ ካውንቲው ውስጥ ተለቆ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ያለዎትን አስተያየት እና ግብረመልስ በመለገስ በፕሮግራሙ አቀራረጽ ላይ የራሥዎን ሚና በመጫወት በዛውም እንዴት ለመኖሪያ አካባቢዎ በጎ አስተዋጾ ማበርከት እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ። እዚህ በመጫን montgomeryplanning.org/planningacademy ዛሬውኑ ይመዝገቡ!

ሁለት ሴቶች የማስታወሻ ደብተር ይዘው በፈገግታ የተነሱት ፎቶ። ጽሁፉ የሚለው፤ የሞንትጎመሪ ፕላን መምሪያ የማህበረሰብ እቅድ አወጣጥ አካዳሚን ይቀላቀሉ! ስለፕላን ሂደቱ እና እንዴት ለማህበረሰቡ ጥብቅና መቆም እንደሚችሉ ይወቁ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ መምሪያ የፖሊሲ ክለሳ አስተያየት መስጫ ፖርታልአወጣ

የማህበረሰብ አባላት ከአሁን ጀምሮ ለክለሳ ክፍት በሆኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ፖሊሲዎች ላይ አስተያየታቸውን መስጠት ይችላሉ። ይህን ሂደት ለህዝብ ክፍት ማድረግ መምሪያው የሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ከማህበረሰቡ ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያስችለዋል። የበለጠ ለማወቅ የመምሪያውን /MCPD/ ድረገጽ እዚህ ይጎብኙ.

MCPD 主頁,其中有一個指向公共政策評論網站入口的箭頭。

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሃይል አቅርቦት ከፍተኛ ስብሰባ/ሳሚት

በቅርቡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ባካሄደው የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ተካፍዬ የነበረ ሲሆን የስብሰባውም አላማ ለነዋሪዎቻችን የሃይል ወጪዎችን በማቃለል እና የአየር ብክለት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጭሶችን በመቀነስ ረገድ ምን ያህል መሻሻል አሳይተናል የሚለውን ለመገምገም ነበር። ይህንን አመታዊ መድረክ በማዘጋጀት ነዋሪዎች፣ የሃይል ኤክስፐርቶች፤ እንዲሁም መንግስታዊ እና የግል የአጋር ድርጅቶች በቅርብ እንዲገናኙ በማድረጉ የአካባቢ ጥበቃ መምሪያው ሊመሰገን ይገባል!

理事會主席Stewart 在蒙哥馬利郡綠色銀行的桌子和橫幅前與郡環保領導人交談。

አረንጓዴ ፌስቲቫል/ግሪንፌስት - 10 አመቱን ያከብራል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአረንጓዴ ፌስቲቫል /ግሪንፌስት በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተመሰረተበትን 10ረኛ አመቱን ለማክበር ተዘጋጅቷል! ግሪንፌስት በሞንትጎመሪ ካውንቲ በየአመቱ የሚካሄድ እጅግ በጣም ጥልቁ ፌስቲቫል ነው። ግሪንፌስት 2025ን ቅዳሜ ሚያዝያ 26 ከ 11 ኤ ኤም እስከ - 4 ፒ ኤም ዊተን በሚገኘው በማሪያን ፍራየር ታውን ፕላዛ በመገኘት ቀጣይነት ያለው እድገትን፣ፈጠራን እና ለምለማማ/አረንጓዴ የሆነ አኗኗርን ያክብሩ! ለዝርዝሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ግሪንፌስት ድረገጽን ይጎብኙ.

第 10 屆蒙哥馬利郡綠色節,請記住這個日期! 2424 Reedie Dr,惠頓,馬裡蘭州。MontgomeryCountyGreenFest.org。

የአእምሮ ጤና ኮርነር

የቫይብ ምርመራ

የቫይብ ምርመራ/VIBE CHECKUP የሚባለው ሽልማት የተቸረው በወጣቶች የሚመራ ደህንነትን/ጤና ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ሲሆን አላማውም ለወጣቶች ወቅታዊ የሆኑ የአእምሮ ጤናን የተመለከቱ መረጃዎችና ሃብቶችን እንዲሁም አዳዲስ እራስን የመግለጫ እድሎችን እና የ አቻ ለአቻ እገዛ መድረኮችን ማመቻቸት ነው። በአሁኑ ሰአት እየተንቀሳቀሰ ያለው በሞንትጎመሪ ካውንቲ የመናፈሻ አካባቢዎች እና አራት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሲሆን አላማውም ተደራሽ የሆኑ የጤና እና አጋዥ የሆኑ የማህበራዊ ተሳትፎ መድረኮችን በማመቻቸት የወጣቶችን አቅም ማጎልበት እና ማበረታታት የሚል ነው። የቫይብ መፈለጊያ /ቸክ አፕ/ የሞባይል ስልክ አፕሊኬሽን በቅርቡ በአፕል እና በጎግል ፕሌይ ይለቀቃል።

አራት ሴቶች አንደናዋ አፕሊኬሽኑን የሚያሳየውን የስልክ ስክሪን ይዛ የሚያሳይ ፎቶ። ጽሁፉም፤ ያንቺ ቫይብ ምንድነው? ለመገናኘት ለማሰብ እና እንደገና ለማበብ ጊዜን ውሰጂ የሚል ነው።