Skip to main content

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - June 18, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቼ፣

እዚህ በሞንትጎመሪ ካውንቲያችን ውስጥ የሚገኙትን የኤልጂቢቲኪው አይ ኤ (LGBTQIA+) (ከመደበኛው የወንድ እና ሴት መገለጫ ውጪ የተለያየ የጾታዊ ግንኙነት እና የስነጾታ መገለጫ ያላቸው) የማህበረሰብ አባላቶቻችንን ማወደስ እና እውቅና መስጠት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል፤ እኔም በካውንቲው ውስጥ በተካሄዱ የፕራይድ/የማንነትኩራት አከባበር ስነስርአቶች ላይ በመሳተፌ ክብር ተሰምቶኛል። በሮክቪል በተካሄደው አመታዊ የፕራይድ የባንዲራ የመስቀል ስነስርአት ላይም ከኮንግረስ አባል ጄሚ ራስኪን፣ ከካውንቲው ዋና አስፈጻሚ ማርክ ኢርሊች፣ ከካውንስል አባል ኢቫን ግላስ እንዲሁም ከሁሉም የመንግስት አስተዳደር ደረጃዎች ከተውጣጡ የስራ ባልደረቦች ጋር በመሆን ተካፍያለሁ።

በተጨማሪም ትርምፕ የኬኔዲ ማእከልን በስሩ ካደረገ በኋላ በኬኔዲ ማእከል ከተያዘላቸው ወረፋ እንዲነሱ ከተደረጉት ከአለማቀፍ የፕራይድ ኦኬስትራ እና የተመሳሳይ ጾታ ወንዶች/ Gay Men’s Chorus/ ዘማሪያን ጋር አብረን በመሆን የአለም ፕራይድን በስትራትሞር አክብረናል። ስትራትሞር የአለም ፕራይድ አከባበር ስነስርአት ኮንሰርትን እንዲያዘጋጅ መጋበዙ በራሱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኘውንና አስደሳች የሆነውን የተለያዩ ማህበረሰቦች ስብጥር መሆናችንን ለማክበር የምናደርጋቸውን ጥረቶች የሚያሳይ የጋራ እሴቶቻችን መገለጫ ነው።

የፕራይድ ወርን በምናከብርት በዚህ ጊዜ የኤልጂቢቲኪው ፕላስ ጎረቤቶቻችንን /ለመንከባከብ/ለመጠበቅ/ እና ሞንትጎመሪ ካውንቲም ለኤልጂቢቲ ማህበረሰቦቻችን ወሳኝ የሆኑ የአጠቃላይ ጤና፣ የአእምሮ ጤና አንዲሁም የማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያቀርብ ለማድረግና ለማረጋገጥ ያለኝን ቁርጠኝነት በድጋሚ ለመግለጽ እወዳለሁ። በእለት ተ እለት ስራቸው የኤልጂቢቲኪው ፕላስ ማህበረሰቦቻችንን በመደገፍ ላይ ላሉ አካባቢያዊ ድርጅቶችም እንዲሁ ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁ።

እርስዎ ወይንም ሌላ የሚያውቁት ሰው እገዛ ወይንም መረጃ የሚፈልግ ካለ የሞንትጎመሪ ካውንቲን ኤልጂቢቲ ኪው ፕላስ የመረጃ ገጽ / LGBTQ+ resource page በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ ።.

ከማክበር ሰላምታ ጋር

ኬት ስቴዋርት

የካውንስሉ ፕሬዚደንት

የካውንስሉ አባላት እና የትራንስፖርት መምሪያ ዳይሬክተር ኮንክሊን የቀስተደመና በኩራት ከፕራይድ ጋር ይጓዙ የል ከተለጠፈበት የራይድ ኦን አውቶቡስ  ፍለፊት የፕራይድ ባንዲራዎችን ይዘው የሚያሳይ ፎቶ።

ጁንቲንዝ/Juneteenth አከባበር

ይህ የያዝነው አመት በሰኔ/ጁን 19 1865 እለት የተክከሰቱትን ሂደቶች የምናስብበት የ160ኛ አመት መታሰቢያ እና በአጠቃላይም የአፍሪካን አሜሪካውያን በአሜሪካ ከባርነት ነጻ የወጡበትን የምናስብበት ነው። ይህ ቀን በባርነት ውስጥ ሲማቅቁ የነበሩ ሰዎች በጋልቭስተን፣ ቴክሳስ የርስ በርስ ጦርነቱ ማለቁን እና እነሱም ከባርነት እንደሚላቀቁ በሃገሪቱ ካሉ ሰዎች ሁሉ በመጨረሻ በሚባል ሰአት የሰሙበት ቀን ነው።  ዜናው ለነሱ የተነገረው ፕሬዚደንት ሊንከን ሁሉንም በኮንፌዴሬት ስቴቶች ያልሉትን በባርነት የተያዙ ሰዎች ነጻ እንዲወጡ የሚያደርግ አዋጅ ከፈረሙ / Emancipation Proclamation/ ከሁለት አመታት በኋላ ነበር።

ጁንቲንዝ በመላ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚከበረው የተለያዩ የአፍሪካን አሜሪካን ባህል እና ስኬቶችን የሚያሳዩሩ ክስተቶችን  በማዘጋጀት ሲሆን ዋና አላማውም በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ታላቅ ለውጥ የመጣበትን ይህን ክስተት በክብር ለማሰብ ነው። ከአመታዊው የስኮትላንድ ጁንቲንዝ ቅርስ ፌስቲቫል /Scotland Juneteenth Heritage Festival/ ጋር በተያያዘ በዚህ ሳምንት በሚዘጋጁት በጣም ብዙ ዝግጅቶች እና ክንውኖች እንዲሁም ቅዳሜ ሰኔ/ጁን 21 በሚዘጋጀው የብላክሮክ የስነጥበብ ማእከል የጁንቲንዝ አመታዊ ክብር /BlackRock Center for the Arts Juneteenth Celebration/ ላይ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል። በጆሲያህ ሄንሰን ሙዚየም /Josiah Henson Museum and Park / እና ፓርክ እንዲሁም ዉድላውን ማነር ባህላዊ ፓርክ / Woodlawn Manor Cultural Park./ በሚኖሩ ልዩ የጁንቲንዝ ስነስርአቶችም በመካፈል ከታሪክ ጋር በሰፊው ይተዋወቁ።  

መልእክት: ጁንቲንዝ፣ ሁሌም እንመክት /Pushing back/. ለነጻነት የሚደረገው ትግል አላለቀም

በፓይክ ዲስትሪክት ጥምረት የማህበረሰብ የጽዳት ዘመቻ ከኛ ጋር ይሳተፉ

የእኔ ቢሮ በመጪው እሁድ ቀን ሰኔ/ጁን 22 ከ11:30  ኤ ኤም እስክ 1:30 ፒ ኤም ከፓይክ ዲስትሪክት ጥምረት ጋር በመቀናጀት የማህበረሰብ የጽዳት ዘመቻ ያካሂዳል።የቆሻሻ ማንሻ መሳሪያዎችን እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ከረጢቶችን የመሳሰሉ እቃዎች ይቀርቡላችኋል። ሁሉም ከአዋቂ እድሜ በታች የሆኑ ልጆች በእለቱ መሳተፍ ከፈለጉ ወላጅ አሳዳጊ አብሮአቸው ሊመጣ ይገባል።

በሰኔ 22 ከኛ ጋር አብሮ ለመሳተፍ እዚህ ይመዝገቡ!

የማህበረሰብ የጽዳት ዘመቻ ቀን በራሪ ወረቀት። እሁድ፣ ሰኔ 22, 11:30 ኤ ኤም እስከ 1:30 ፒ ኤም።  በኋይት ፍሊንት ፕላዛ የሮድማንስ ዲስካውንት ጉርሜ፤ አድራሻ 5148 Nicholson Ln, Rockville, MD. አስፈላጊ ቁሳቁሶች ይቀርባሉ። ከመጀመራችን በፊት በቡና  እና ቀላል ቁርሶች ይዝናኑ!

የሁለተኛ ዙር  የፐርፕል ላይን የአነስተኛ ንግድ ተቋማት የገንዘብ ድጎማለማመልከት አሁን ክፍት ነው

በግንቦት 2025 የሜሪላንድ የትራንስፖርት መምሪያ ለመጀመሪያው ዙር የገንዘብ ድጎማ በሞንትጎመሪ እና ፕሪንስ ጆርጅስ ካውንቲ ለሚገኙ በፐርፕል ላይን ግንባታ ምክንያት ተጽእኖ ለደረሰባቸው 104 የአነስተኛ የንግድ ተቋማት የ$1 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ድጎማ መስጠቱን አስታውቋል። ለሁለተኛው ዙር ድጎማ ማመልከቻዎችን ለማስገባት አሁን ክፍት ስለሆነ እስከ ህምሌ 11 ድረስ ማመልከቻዎችን እንቀበላለን።  ብቁነታቸው የተረጋገጠ የንግድ ተቋማት በአንድ የድጎማ ፈረቃ እስከ $50,000 ዶላር የሚደርስ ድጎማ ሊያገኙ ይችላሉ፤  ነገር ግን በአንድ ካላንደር አመት ውስጥ ከሁለት ድጎማዎች በላይ ማግኘት አይቻልም። ንግድ ተቋማቱ ድጎማውን ለማግኘት በአዲሱ ኦንላይን ማመልከቻ ፖርታል  አማካኝነት እንዲያመለክቱ በእጅጉ ይበረታታሉ።

የፐርፕል ላይን ቀላል የሃዲድ ባቡር

ሜሪላንድ ሳን በክስ ፕሮግራም

የሜሪላንድ ሳን በክስ ፕሮግራም /Maryland SUN Bucks program/ የነጻ ወይንም የቅናሽ ዋጋ ምግብ የሚያገኙ በትምህርት ቤት እድሜ ላይ የሚገኙ ልጆች ላሏቸው  ቤተሰቦች  የትምህርት ቤት ምግብ በማይኖርበት በበጋ የእረፍት ወቅት የግሮሰሪ ሸቀጣሸቀጦችን መግዛት እንዲችሉ የሚያግዝ ፕሮግራም ነው። ለሜሪላንድ ሳን በክስ ፕሮግራም ተጠቃሚነት የሚመረጡ ቤተሰቦች ለሰኔ፣ ሃምሌ፣ እና ነሃሴ በየወሩ $40 ዶላር  (በድምሩ $120 ዶላር) ለየአንዳንዱ ብቁ ለሆነ ተማሪ ስም ድጎማ ያገኛሉ።

የበለጠ በማወቅ በፕሮግራሙ ዛሬውኑ ይመዝገቡ

የመገመጥ ምልክት ያለው አፕል የያዝዘ ወጣት ልጅ ፎቶ

ኬእት በማህበረሰቡ ውስጥ

አዲስ የ6ተኛ ዲስትሪክት ፖሊስ ጣቢያ ተከፈተ!

የጌርስበርግ እና ሞንትጎመሪ ቪሌጅ ማህበረሰቦችን ለማገልገል ተብሎ የተከፈተው አዲሱ የ 6ተኛ ዲስትሪክት ፖሊስ ጣቢያ የመክፈቻ ስነስርአት ላይ ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ሆነን የመክፈቻ ሪባን በመቁረጣችን ክብር ተሰምቶኛል። የዚህ ጣቢያ መቋቋም  ትርጉምነቱ የህዝብ ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ለአጠቃላይ ማህበረሰባችን መጠበቅ እንዲሁም ላአሁኑ እና ብሎም የወደፊቱን የሞንትጎመሪ ካውንቲያችን እድገት ለማቀላጠፍ የምናደርገው ቀጣይነት ያለው ስራ አካል ነው።  

በቪዲዮ የተቀረጸውን አጭር ማሳያ  እዚህ ይመልከቱ

የካውንቲው አመራሮች እና የህዝብ ደህንነት ባለስልጣናት በአዲሱ የ6ተኛው ዲስትሪክት ፖሊስ ጣቢያ ፊትለፊት ሰማያዊ ሪባን ሲቆርጡ።

የሊትንስቪል ማህበረሰብ የእግር ጉብኝት

የሊትንስቪል የኢንዱስትሪ ወረዳ ነዋሪዎቹ የሚያውቋቸውንና የሚወዷቸውን የአካባቢ የንግድ ተቋማት ያካትታል፤ ለምሳሌ ፓርቲ ዌርሃውስ፣ አርባን የወይን መጥመቂያ፣ ኤል ቪየጆ፣ ሳይን አ ራማ እናሌሎችንም! የሞንትጎመሪ የመኖሪያ ቤት ጥምረት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት መምሪያ ጋር በመሆን ወደነዚህ ቦታዎች የደህንነት ማረጋገጫ ጉብኝት እንድናደርግ እና የፐርፕል ላይን የባቡር ጣቢያ ሲከፈት ነዋሪዎች በሰላም ወደነዚህ የንግድ ተቅቋማት መሄድ እንደሚችሉ ለማረጋገጥ እንድንችል ስላደረገ ሊመሰገን ይገባል። በብሩክቪል መንገድ የተወሰኑ ልዩ ቦታዎች ላይ መሻሻል ያለባቸው ነገሮችን የለየን ሲሆን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት መምሪያ ሰራተኞችም እነዚህን ነገሮች ተመልክተው እንደሚያስተካክሉ ነግረውናል።  

በማህበረሰብ የእግር ጉብኝቱ ወቅት የማህበረሰብ አባላት ቢጫ እና አንጸባራቂ ጃኬቶችን ለብሰው በእግረኛ መንገድ ላይ ቆመው የሚያሳይ ፎቶ

ብሄራዊ በሳምንት መጨረሻ ብርቱካናማ ቀለም የመልበስ ክንውንከ

የመሳሪያ ጥቃት ደርሶባቸው የተረፉ ሰዎችን ለመታደግ እና ዛሬም ሆነ ነገ ከመሳሪያ ጥቃት ነጻ የሆነ አለም እንዲኖር ለማድረግ በሞንጎመሪ ካውንቲ ቅርንጫፍ የእናቶች የድርጊት እንቅስቃሴ/ሞምስ ዲማንድ አክሽን/  /Moms Demand Action/ በተዘጋጀው #ቢጫ የመልበስ አመታዊ ስነስርአት/ኩነት ላይ በመሳተፌ ኩራት ተሰምቶኛል።  እኛ አሁን እዚህ በየአመቱ በሰኔ ወር ላይ በ#ቢጫ የመልበስ ስነስርአት /#WearOrange/ ለማክበር እንሰባሰብ እንጂ የእናቶች የድርጊት እንቅስቃሴ/ሞምስ ዲማንድ አክሽን እና ተባባሪ ድርጅቶችቻቸው ግን በማህበረሰቦቻችን እና ብሎም በመላ ሃገሪቱ የሚከሰትን በመሳሪያ የታገዘ የሰዎች ጥቃት ለመከላከል ቀን ተ ቀን በመስራት ላይ ይገኛሉ።  

በሳምንቱ መጨረሻ የብርቱካናማ ከለር የመልበስ ስነስርአት ላይ የካውንቲው አመራሮች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በአንድ ላይ ተሰባስበው ብርቱካናማ /የመሳሪያ ጥቃት ይቁም/ የሚሉ ቲሸርቶችን ለብሰው የሚያሳይ ፎቶ

የአ እምሮ ጤና ኮርነር

የወላጆች ማበረታቻ እና የቤተሰቦች የመቋቋም ችሎታ ማዳበር ፕሮግራም (PEP-FRP)

ይህ ፕሮግራም (PEP-FRP) በነጻ የሚሰጥ እና በኢንተርኔት መረብ/ቨርቹዋል የሚካሄድ የስምንት ሳምንት ፕሮግራም ሲሆን በሳምንት አንዴ ለ90 ደቂቃ ይሰበሰባል። ፕሮግራሙ ቤተሰቦች እና እንክብካቤ ሰጭዎች የሰውነት ጉዳትን በተመለከተ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እንዲሁም የስነልቦናዊ ወይንም ስሜታዊ ድጋፍን በጥሩ ሁኔታ በሚሰጥ መልኩ ከህጻናት ጋር ያላቸውን ኝኙነት ማጠናከር እንዲችሉ እገዛ ይሰጣል። ፕሮግራሙ ከሚያካትታቸው ስራዎች መሃል በህጻናት የአእምሮ ጤና ላይ የተኮሩ ሁለት የስልጠና ክፍለጊዜዎችን እንዲሁም ሃይለኛ/ጎጂ ስሜቶችን ለመቆጣጠር፣ ጤናማ የሆኑ የግንኙነት መስመሮችን ለማበጀት እንዲሁም በቤተሰቦች ላይ የሚፈጠርን መጨናነቅ ለማስወገድ በሚረዱ ዘዴዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል።  

ፕሮግራሙ የሚሰጠው በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ነው። ቢያንስ አምስት ክፍለጊዜያትን እና የግምገማ ክፍለጊዜን መከታተል የሚችሉ ተሳታፊዎች የ$50 ዶላር የስጦታ ካርድ ያገኛሉ። በፕሮግራሙ በመመዝገብ የበለጠ ለማወቅ pep-frp.org የሚለውን ይጫኑ።

የፕሮግራም ምልክት. መልእክት: የወላጆች ማበረታቻ ፕሮግራም። ጽናት ያላቸውን ቤተሰቦች ለመገንባት ማገዝ።