ውድ ጓደኞቼ፣
ወደበአል ሳምንቱ መጨረሻ እየተቃረብን ባለንበት በዚህ ወቅት ይህን መልእክቴን የምጀምረው እውነተኛ ሃገር ወዳድነት ምን ማለት እንደሆነ በማስታወስ እና በዜጎች ንቁ የሲቪክ ተሳትፎ፣ በዴሞክራሲያዊ ሂደት እንዲሁም በማህበረሰብ ሃይል ላይ ጽኑ እምነት በማስቀመጥ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ካውንቲያችንን ወክዬ በመስራቴ ምን ያህል ኩራት እንደሚሰማኝ በመግለጽ ነው።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ሃገርወዳድነታችን የምናሳየው ጎሬቤቶቻቻንን ለማገዝ ቀድሞ ደራሽ በመሆን፣ ለህገመንግስታዊ መብቶቻችን መከበር በጽናት በመቆም እና የዲሞክራሲ እሴቶቻችንን በማስጠበቅ ነው።
ሞንትጎመሪ ካውንቲ በመከከላችን ያሉ ልዮነቶችንን የሚያከብር እንዲሁም የተለያየ አይነት ልዩነቶች እና ማንነቶቻችንንም እንደ ታላቅ ሃይል የሚመለከት ማህበረሰብ ነው። መሰረታዊ መብቶቻችን ላይ ፈተና በተጋረጠበት እና ተግዳሮቶች እየገጠሙን ባለበት ሰአት እንኳን ሞንትጎመሪ ካውንቲያችን ለመላው ሃገራችን የተስፋ ጮራ እንዲሆን ለማስቻል ነዋሪዎቻችን ባላሰለሰ መልኩ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።
ይህ የሃምሌ አራት የክብር እለት ነጻነታችንን እና ማህበረሰባችንን ልዩ የሚያሰኙትን እሴቶቻችንን የምናከብርበት እለት ነው። በአንድ ላይ በመሆን በህይወት መኖርን፣ ነጻነትን እንዲሁም ምቾት እና ደስታን የመሻት እና ፍትህ ለሁሉም የሚሉትን መርሆዎች እናከብራለን።
በሚንትጎመሪ ካውንቲ በሙሉ በሰልፍ እና በተለያዩ ክስተቶች የሚከበረውን ደስታ የተሞላበት የነጻነት ቀን አከባበር ይከታተሉ። ጀርመንታውን ግሎሪ የሚባለው አመታዊ አከባበር በደቡብ ጀርመንታውን የመዝናኛ ፓርክ በሃምሌ 4 የሚከበር ሲሆን ሚድ ካውንቲ ስፓርክልስ የሚባለውም አከባበር በተከታዩ ምሽት ሃምሌ 5 በአልበርት አይንስታይን ትምህርት ቤት በ ነጻ የሪች ተኩስ ትርኢት ይታሰባል።
እኔም በታኮማ የሃምሌ አራት በአል የክብር ሰልፍ ላይ አብሬ የእግር ጉዞ የማደርግ ስለሆነ በዛው ስነስርአት ላይ እንደምንተያይ ተስፋ አደርጋለሁ!
ከሰላምታ ጋር
ኬት ስቴዋርት
የካውንስሉ ፕሬዚደንት
ባለፈው ሳምንት የወጣቶችን ተዋልዶ ጤና፣ የተዋልዶ ጤና የስራ ሃይል፣ የጤና አገልግሎት ፍትሃዊነት እንዲሁም ሌሎችንም ከአእምሮ ጤና እና ከጤና ተደራሽነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመወያየት የተጠራውን የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ሁለተኛ ስብሰባ እየመራሁ ነበር። በስብሰባው ወቅት ከወጣቶች ተዋልዶ ጤና እንክብካቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሚዳሥሠውን እና በቅርብ በለቀቀው የህግ አውጪዎች ተቆጣጣሪ ቢሮ ረፖርት ላይም ተወያይተን ነበር። የአእምሮ ጤና እኔ በፕዚደንትነት በምመራው ምክር ቤት ቁልፍ የሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሲሆን ይህን ወሳኝ ጉዳይ ለመታደግ የሁሉንም አካላት የጋራ ጥረት እና ድርጊት የሚጠይቅ መሆኑን ለማስገንዘብ እወዳለሁ።
የካውንስል አባል ጋቤ አልቦርኖዝ እና እኔ አብረን በመሆን የብሄራዊ የአእምሮ ጤና ግንዛቤ መታሰቢያ ወርን እውቅና የሚሰጠውን የካውንስሉን አዋጅ በተመለከተ አቅርበን አወያይተናል። የካውንቲ የስራ ሃላፊዎች፣ የጤና እንክንካቤ ሰጪዎች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች፣ ከኛ ጋር የተሳተፉ ሲሆን በወቅቱም እንዲሁ ቢ ዘ ዋን የተባሉት የወጣት አምባሳደሮች / BTheOne youth ambassadors/ የወጣቶች የአእምሮ ጤናን በተመለከተ የሚሉትን ለመስማት ችለናል።
የሞንጎመሪ ካውንቲ የህጻናት እንክብካቤ ሰጪ ድርጅቶች በስራ ላይ መቆየት እንዲችሉ የሚያግዘውን እና መጠነ ሰፊ እና በበለጠ ሁኔታ ዳጎስ ያለ የንብረት ግብር ክሬዲት የሚሰጥ ረቂቅ ህግ በቅርቡ አቅርቤ ነበር። የቀረበው ረቂቅ ህግ አሁን ያለውን የህጻናት እንክብካቤ የግብር ክሬዲት ብቁነትን የሚያስፋፋ እና የተፈቀደውን የክሬዲት መጠን ከ$3,000 ወደ $10,000 ከፍ እንዲል የሚያደርግ ነው። ተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ያለው የህጻናት እንክብካቤ ማግኘት የወላጅነት/ቤተሰብ አስተዳደር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢኪኖሚም ጉዳይ ነው። የህጻናት እንክብካቤ ሰጪዎቻችንን መደገፍ ነዋሪዎቻችን በመተማመን ስሜት በካውንቲው ውስጥ እንዲኖሩ እና እንዲሰሩ መቻላቸውን ለማረጋገጥ የሚረዳ ቁልፍ እና ለኢኮኖሚያዊ እድገታችንም በጣም ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው። በሃምሌ/ጁላይ 8 የህዝብ ችሎት ይካሄዳል። ይህን ለማድረግ የሚረዳውን ረቂቅ ህግ በአናፖሊስ በተደረገው የመጨረሻው ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ ላደረጉት የሜሪላንድ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ጁሊ ፓልኮቪች ካር ምስጋና እናቀርባለን።
በሲልቨር ስፕሪንግ የዜጎች አማካሪ ቦርድ የሚገኙ 13 ክፍት የአባልነት ቦታዎችን ለመሙላት እንዲሁም በ ሲልቨር ስፕሪንግ የከተማ አጥቢያ የአማካሪዎች ኮሚቴ የሚገኙ ስምንት ያአባልነት ቦታዎችን ለመሙላት ካሁን ጀምሮ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል። የሲልቨር ስፕሪንግ የዜጎች አማካሪ ቦርድ በሲልቨር ስፕሪንግ ነዋሪዎች እና በካውንቲው የመንግስት አስተዳደር መካከል እንደመገናኛ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ይህንንም የሚያደርገው በአካባቢው እና በንግድ ድርጅቶች አካባቢ የሚነሱ ጉዳዮችን በመለየት እና ለካውንቲው ባለስልጣናትም የመፍትሄ ሃሳቦችን በማቅረብ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢ ያሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ለሲልቨር ስፕሪንግ የሪጅን አገልግሎት ማእከል የማማከር ስራ ያከናውናል። የሲልቨር ስፕሪንግ የከተማ አጥቢያ አማካሪ ኮሚቴ ለካውንቲው አስተዳደር መረጃ እና ምክር የሚሰጥ ሲሆን ለሲልቨር ስፕሪንግ ሪጅን አገልግሎት ማእከል ህላፊ ደግሞ የሰራተኛ እድገትን፣ የጥገና፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ እንዲሁም ለማእከላዊው የሲልቨር ስፕሪንግ ዲስትሪክት ከበጀት ጋር የተያያዘ አቅጣጫ የማሳየት እና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል።
ለእነዚህ ክፍት ቦታዎች የማመልከቻ የመጨረሻ ቀነ ገደቡ ሃምሌ 4 ነው። ለቦታው ብቁነትዎን እዚህ በመጫን ማረጋገጥ እና ማመልከት ይችላሉ።
ጁንቲንዝ በመላው ማህበረሰባችን ዘንድ ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ በጣም ብዙ ለሆኑት የካውንቲው ተቀጣሪዎች፣ ለነጻ ኣገልግሎት ሰጪዎች እና ለማህበረሰብ አደራጆች ያለንን ምስጋና ለመግለጽ እወዳለሁ። በብላክ ሮክ የአርት ማእከል በተካሄደው ስነስርአት የካውንቲውን ሊቪንግ ለጀንድ /በህይወት ያሉ ዘላለማዊ ክብር ባለቤቶች/ ሽልማት ለተቀበሉት የካውንቲው ስድስት የአፍሪካ አሜሪካን የማህበረሰብ መሪዎች ሁላችንም አብረን እንኳን ደስ ያላችሁ እንድላቸው እጠይቃለሁ። ጀምስ ቤከር፣ ዶ/ር ቤቲ ሆልስተን፣ እና የሜሪላንድ ስቴት ምክርቤት አባል ግሬገሪ ዊምስ ህይወታቸውን ሙሉ ላሳዩት የአመራር ብቃት፣ ለህዝብ ጥቅም የመሟገት እንቅስቃሴ እና በአጠቃላይ ለህዝብ በሰጡት አገልግሎት የዚህ ክብር ተሸላሚ ሆነዋል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ያላቸው ጽናት ሁሉንም ነዋሪዎቻችንን ከፍ ያደረገ ተግባር በመሆኑ ለማህበረሰቦቻችን ለሰጡት እጅግ የላቀ አገልግሎት ልናመሰግናቸው እንወዳለን።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ እና የማዳን አገልግሎት / MCFRS/ የማስተዋወቂያ ዝግጅት ላይ በመሳተፌ ክብር የተሰማኝ ሲሆን በዚህም ዝግጅት የአስተዋዋቂዎቹን እና ቤተሰቦቻቸውን ጽናት፣ ጠንካራ ስራ፣ እንዲሁም ድፍረት እና አገልግሎት ለማክበር አስችሎናል። እጅግ የላቀ አገልግሎት የሰጡትን የመጀመሪያ ደረጃ ምላሽ ሰጪዎችቻችን ለአገልግሎታችሁ እያመሰገንን የእሳት አደጋ አገልግሎት ዋና ሃላፊ ኮሬይ ስሜድሌይንም እንዲሁ ለሰጠው አመራር ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን።
የማንነት ኩራት/ፕራይድ ወር አከባበርን ያጠናቀቅነው በዳውንታውን/መሃል ከተማ ሲልቨር ስፕሪንግ እሁድ እለት በተደረገው ፕራይድ በ ፕላዛ / Pride in the Plaza/ የክብር ስነስርአት ነበር። በሞንትጎመሪ ካውንቲ በሰኔ ወር ሙሉ በተከበረው የፕራይድ ወር አከባበር ላይ በመሳተፋችን ክብር ተሰምቶናል። የሰኔ ወርን እንደ ፕራይድ ማክበሪያ ወር እውቅና ብንሰጠውም ቅሉ እጅግ በጣም ጽኑ አጋራችን ከሆኑት የማህበረሰብ አባላቶቻችን እና ከሌሎችም ለትርፍ ካልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር በመሆን የኤልጂቢቲኪው ፕላስ / LGBTQ+/ ማህበረሰብ አባላቶቻችንን ለመደገፍ፣ ለመጠበቅ/መንከባከብ እና ከፍ ለማድረግ ቀን ተ ቀን እንሰራለን። መልካም የፕራይድ አከባበር!
የካውንስሉን የፕራይድ ወር ዋና ዋና መግለጫዎች ድረገጽ በመጫን ያንብቡ።
ጄኤሴኤስኤ /JSSA/ በማይንድክራፍት ፕሮግራም / MindCraft program,/ አማካኝነት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች እና ከማህበረሰብ የጤና ሃብት ማእከል ጋ በመተባበር በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ትምህርት ቤትን ማእከል ያደረጉ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን የሚያቀርብ ተአማኒነት ያለው የማህበረሰብ ጤና እና የማህበራዊ ደህንነት ተቋም ነው። የማይንድክራፍት ፕሮግራሙ የሰለጠኑ የጄኤሴስኤ የአእምሮ ጤና አስተባባሪዎችን እና ሃኪሞችን በ 90 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች ውስጥ በማሰማራት ተማሪዎች በትምህርት ቀናት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። ያማይንድክራአፍት ፕሮግራም ባይኖር ኖሮ ብዙ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ /ቤቶች ተማሪዎች በትምህርት ቤትም ሆነ በበኖሪያ ቦታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ህይወት ቀያሪ የሆኑ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ማግኘት አይችሉም።
ዉምኮ ሄልፕ /WUMCO Help, Inc. የተባለው በፑልስቪል፣ ባርንስቪል፣ ቢልስቪል አና ከነዚህም ባሻገር የሚገኙ አካባቢዎችን ጨምሮ በምእራብ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ገጠራማ ማህበረሰቦችን የሚያገለግል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። ከሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መስሪያ ቤት ባለው ጠንካራ ቅንጅት በመጠቀም ዉምኮ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ፣ የምግብ እና የመኖሪያ ፍጆታ እገዛዎች፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የማህበራዊ እገዛ አስተዳደር/ case management/ ድጋፍን ጨምሮ ለአካባቢው ነዋሪዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ ድጋፍ አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል። ዎምኮ እና የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤቱ አንድ ላይ በመስራት የተለያዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እና እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን በቀጥታ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋሉ።
