ውድ ጓደኞቼ
የሃምሌ ወር የብሄራዊ ማይኖሪቲ የአእምሮ ጤና የሚታሰብበት ወር / National Minority Mental Health Month/ እና ይህም በሌላ አጠራር የጥቁሮችን፣ የሃገር በቀል/ Indigenous/ ነዋሪዎችን፣ እንዲሁም የተለያየ ቀለም ያላቸው የሰው ልጆች የአእምሮ ጤናን የምናከብርበት ወር ሲሆን አላማውም እነዚህ በዩ ኤስ አሜሪካ የሚኖሩ የህብረተሰባችን አካል የሆኑ ግለሰቦች የሚያጋጥሟቸውን ልዩ እና የራሳቸው ብቻ የሆኑ የአእምሮ ጤና ችግሮችን በተመለከተ ግንዛቤ ማሳደግ ነው።
ይህ የአእምሮ ጤና መታሰቢያ ወር በተለይ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ እና የአእምሮ ጤና ተሟጋች የነበረችውን የቤብ ሙር ካምቤልን /Bebe Moore Campbell/ ቅርስም በክብር የምናስብበት ወቅት ነው። የቤብ ያላሰለሰ ጥረት እና ቅስቀሳ በጥቁር የማህበረሰብ ወገኖቻችን እና በሌሎችም የተለያየ ቀለም ያላቸው አባላቶቻችንን የአእምሮ ጤና ፍላጎት ላይ ትኩረት እንድንሰጥ በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦ አድርጓል። የጥቁሮች፣ የሃገር በቀሎች፣ እንዲሁም የተለያየ ቀለም ያላቸው የሰው ልጆችን የአእምሮ ጤና የተመለከቱ መረጃዎችን ለማግኘት Mental Health America /የአእምሮ ጤና በአሜሪካ/ የሚለውን ድረገጽ ይጎብኙ።
ስር የሰደደ መዋቅራዊ እና ተቋማዊ ዘረኝነት፣ ፍትሃዊ ያልሆነ የጤና እንክብካቤ አቅርቦት፣ እንዲሁም ከባህል ጋር ተያይዘው የሚመጡ የመገለል ሁኔታዎች በአእምሮ ጤና አጠባበቅ ላይ ለሚታየው ችግር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። የምንሰጣቸው የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ከባህላዊ እሴቶች ጋር የሚጣጣሙ፣ እንዲሁም አካታች፣ ፍትሃዊ እና ከሁሉም ዝርያ ለተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎቻችን ተደራሽ መሆናቸውን ማረጋገጥ በካውንቲው ውስጥ የተቀናጀ የአእምሮ ጤና እንክብካቤ አሰጣጥ ዘዴን ለማጎልበት በጣም አስፈላጊ ነው።
በዚህ ረገድ እርስዎ ወይንም ሌላ የሚያውቁት ችግር የገጠመው ሰው ካለ በየአካባቢያችሁ ያሉ የአእምሮ ጤና ሃብቶችን ይጎብኙ።
እንደተለመደው ምንም አይነት ጥያቄ ካለዎት ወይንም እርዳታ ከፈለጉ ወደቢሮዬ በመደወል ማግኘት እና መወያየት ይችላሉ።
ከሰላምታ ጋር
ኬት ስቴዋርት
የካውንስሉ ፕሬዚደንት
በፌደራል ደረጃ በሚደረጉ የፖሊሲ ለውጦች እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ለሚያተኩሩ ስራዎች በሚመደበው በጀት ላይ የሚደረጉ ቅነሳዎች የሚያመጡት ተጽእኖ ከሃይል ፍጆታ ዋጋ እየጨመረ መሄድ ጋር አብረን ከግምት ውስጥ በማስገባት ባሁኑ ሰአት ያሉንን የሃይል ፍጆታ ወጪዎች ለማስተካከል እና የካውንቲውን የአካባቢ የመንከባከብ ስራ ለማመጣጠን የሚረዱንን ሁሉንም አማራጭ ዘዴዎች ማየት ይኖርብናል።
የካውንቲው የአካባቢ ጥበቃ የድርጊት መርሃ ግብር የኮሙኒቲ ቾይስ አግሪጌሽን / Community Choice Aggregation (CCA)/ ወይንም በሌላ አጠራር የማህበረሰብ የሃይል አጠቃቀም ምርጫ በመባል የሚታወቀው አሰራር በ2035 ያሰብናቸውን የአካባቢ ጥበቃ የድርጊት አላማዎች ለማሳካት የሚረዳን እንደ አንድ አይነተኛ እና ቀዳሚ ዘዴ አድርጎ ይወስደዋል። ላዛም ነው የአካባቢ አስተዳደሮች ነዋሪዎችን፣ የንግድ ተቋማትን እንዲሁም የከተማ ልማት/ማዘጋጃ ቤት ግምጃ ቤቶችን በመወከል የኤሌክትሪክ ሃይልን እንዲገዙ የሚያስችለውን የተቀናጀ ማህበረሰብ ምርጫ እቅድ ለማውጣት የታለመ ረቂቅ ህግ ያዛጋጀሁት። ይህ ህግ ካውንቲው ለነዋሪዎች የዋጋ መረጋጋትን እና የወጪ ቅነሳን እንዲያደርግ እና በዛውም በዛ ያሉ የታዳሽ የሃይል ምርጫዎችን ለማቅረብ ያስችለዋል።
የኤሌክትሪክ ክፍያዎቻችሁን ለመቀነስ እርዳታ ከፈለጋችሁ የሚከተሉትን ፕሮግራሞች እና የመረጃ ሃብቶች ተመልከቱ፤
ሃምሌ የብሄራዊ የፓርኮች እና የመናፈሻ አገልግሎቶች መታሰቢያ ወር መሆኑን ያውቃሉ? በዚህ የበጋ ወራት ፓርኮቻችን፣ የፓርክ ውስጥ መንገዶች፣ እንዲሁም የመዝናኛ አገልግሎቶቻችን ምን ምን እንደሚያቀርቡላችሁ ለማወቅ ሞክሩ። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ከአትክልት መደቦች እስከ የተፈጥሮ ማሳያ ማእከላት እንዲሁም የቤት ውስጥ እና የቤት ውጪ መዋኛ ገንዳዎች እና በአዲስ የተገጠሙ የቢክልቦርድ መጫወቻ ቦርዶችን ጨምሮ እናንተን ለማስደሰት በሚል ቀርበዋል። በዚህ በበጋ ወራት በአቅራቢያዎ የሚኖሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፓርኮች የሚዘጋጁ ልዩ ዝግጅቶችን በመከታተል ያጣሩ!
በዋሽንግተን ሰበርባን ሳኒታሪ ኮሚሽን /WSSC/ የሚተገበረው እና ተወዳጅ የሆነው የ ‘ጌት ከረንት /Get Current/ ጊዜያዊ የውሃ ፍጆታ ክፍያ እገዛ ፕሮግራም እንዲራዘም አና እንዲያድግ ተደርጓል። የፕሮግራሙ /Get Current 2.0/ መራዛም እና እንዲያድግ መደረግ እስከ ጥቅምት 31 ይቀጥላል። ይህ የእገዛ ፕሮግራም ከሰኔ 1, 2025 ጀምሮ ያልተከፈለ ሂሳብ ላለባቸው ለእገዛ ብቁ የሆኑ ደምበኞች የተወሰነውን የእዳቸውን መጠን የሚሰርዝ እና 100 ፐርሰንት የሚሆነውን የዘገ የክፍያ ቅጣት እና የተቋረጠ የፍጆታ አገልግሎት ማስቀጠያ ክፍያንም የሚያስቀር ነው።
የሃምሌ ወር የአካል ጉዳተኝነት የማንነት ኩራት መታሰቢያ ወር ሲሆን የአካል ጉዳተኛነት ያለባቸው ሰዎችን ያስመዘገቡትን ስኬት እና ልምድ የምናከብርበት እንዲሁም በ1990 የተፈረመውን ጉዳት ያለባቸው አሜሪካውያን ደምብ ተብሎ የሚታወቀውን ህግ የምናስብበት ወቅት ነው። በዚህ ወር እና ብሎም አመቱን ሙሉ የአካልጉዳተኛ ሰዎችን መብቶች በተመለከተ ግንዛቤን የምናስፋፋበት እና በትምህርት፣ በስራ ቅጥር ፣ ጥራት ያለው የመኖሪያ ቤት እና የጤና እንክብካቤ አሰጣጥ ረገድ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እና አቃፊ የሆነ አገልግሎት እንዲፈጠር የምናደርግበት አጋጣሚ ነው።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ መይን ስትሪት ሮክቪል / Main Street in Rockville/ የተባለው እና አካታች/አቃፊ የሆነ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ብቻ ሳይሆን አዳጊ የሆኑ ማህበረሰብ ተኮር እድሎችን እና ልምዶችን የሚያበረታታ የአፓርትመንት ፕሮግራም መኖሩ ለኛ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በሜን ስትሪት የመኖሪያ ሰፈር የድህንነት/ሴፍቲ/ ማክበሪያ እለት ተገኝቼ ጥሩ ጊዜን ያሳለፍኩ ሲሆን በእለቱም ሙዚቃ፣ ምግብ እንዲሁም የደህንነት ጥበቃን የተመለከቱ ማሳያዎች እና ሌሎችም ጥሩጥሩ ነገሮች ቀርበዋል!
ከካውንቲው ሃላፊዎች እና ከህብረተሰብ ጤና ባለሞያዎች ጋር አብሬ በመሆን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤትን (DHHS) 30ኛ አመት በማክበራችን ደስታ ተሰምቶኛል። ይህ አከባበር የጤና መምሪያው ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ጊዜ ለነዋሪዎች ለመስጠት በሚያስችል መልኩ የመቀናጀቱን ሁኔታ እውቅና የሚሰጥ ነው። ዲ ኤች ኤች ኤስ የማህበረሰቦቻችን ፍሬ የሆኑት የህጻናትን፣ የአዋቂዎችን እና የእድሜ ባለጸጋ የካውንቲው ነዋሪዎችን ቁልፍ እና ወሳኝ የሆኑ መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት የሚሰራ ሲሆን በተጨማሪም የኢንሱራንስ ሽፋን ለሌላቸው፣ መኖሪያ /መጠለያ ለሌላቸው ወይንም ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ከባድ ችግር የሚገጥማቸውን ነዋሪዎች ለማገዝ ተግቶ ይሰራል። ዳይሬክተሩ ጄምስ ብሪጀርስ እና የካውንቲው የጤና መኮንን ዶ/ር ኪሻ ዴቪስን ጤናማ የሆነ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጽናት ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ላደረጉት የአመራር ስራ እና ብቃት ልናመሰግናቸው እንወዳለን።
ለ2025-2026 የትምህርት አመት ለአንድ አመት በአባልነት ለማገልገል በሃምሌ 1 ቃለመሃላ የፈጸመችውን አዲሷን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች/ኤም ሲ ፒ ኤስ/ የትምህርት ቦርድ የተማሪዎች ተወካይ አባላችንን ሚስ አኑና ማሎን እንኳን ደስ አለሽ ለማለት እንወዳለን። ሚስ ማሎ በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተና ደረጃ ት/ቤት በማደግ ላይ ያለች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ስትሆን የትምህርት ቦርዱ 48ኛ የተማሪ ተወካይ አባል ነች። ከሷ ጋር አብረን ለመስራት እና በመጪው አመት የኤም ሲ ፒ ኤስ ተማሪዎችን ወክላ የምታከናውናቸውን ታላቅ ስራዎችም ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን። በተጨማሪም አባልነቱን የጨረሰውን ፕራኔል ሱቫርናን ለኤም ሲ ፒ ኤስ ማህበረሰብ ስለሰጠው አገልግሎት እናመሰግናለን። ወደሚቀትለው የህይወት ምእራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅትም መልካሙን ሁሉ እንመኝንለታለን።
ከላቲን አሜሪካን የወጣቶች ማእከል ለተመረቁ ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ባዘጋጀው እና በሲልቨር ስፕሪንግ በተካሄደው የ2025 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የጨረሱ ተማሪዎች ዝግጅት / GED commencement ceremony/ ላይ የመገኘት ክብር አግኝቼ ነበር። የተለያዩ ተግዳሮቶችን ተቋቁመው የነበረባቸውን ፈተና ወደጥንካሬ በመቀየር አመርቂ ጥረት ያስመዘገቡ 28 ግለሰቦችን እውቅና መስጠታችን በጣም አነቃቂ ስሜት የሚፈጥር ክስተት ነበር። ይህ ድርጅት አዳዲስ በሮችን/እድሎችን መክፈት ብቻ ሳይሆን መሰናክሎችን በመበጣጠስ ወጣቶቹ ከግራ የመጋባት ስሜት ወደ አበረታች እድል ወደመፍጠር እንዲያቀኑ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ይገኛል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የላቲን አሜሪካውያን የወጣቶች ማእከልን የመሳሰሉ አጋሮች መኖራቸውን በታላቅ የምስጋና ስሜት የምናየው ሲሆን እነኚህ ማእከላት ወጣቶች በተሳካ ሁኔታ ወደ አዋቂነት እንዲሸጋገሩ የሚያስችሉ ትምህርታዊ እና የስራ ዝግጁነት እድሎችን በማዘጋጀት አይነተና ሚና ይጫወታሉ።
480 ክለብ የአራት ቀን የሚቆይ በማህበረሰብ የታገዘ ጉባኤ የሚያዘጋጅ ሲሆን አላማውም የወጣት አትሌቶችን የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ሊያሳድጉ የሚችሉ ተከታታይ የሆኑ በባለሞያ የሚሰጡ አውደጥናቶችን እና የስልጠና ክፍለጊዜዎችን ማቀናበር ነው። ጉባኤው ከሚያካትታቸው መካከል ግለሰባዊ ህይወት እና ክህሎትን ማሳደግ፣ እስፖርታዊ ብቃቶችን የሚያሳድጉ የአእምሮ ክህሎቶች፣ ማገገም እና ስነምግብ እንዲሁም የአመራር ብቃት እና የቡድን ስራ የሚሉት ይገኙበታል። እነኚህ እርእሶች የተመረጡት የተማሪ አትሌቶቹን ዘርፈብዙ ፍላጎቶች ለማሟላት ታስቦ ሲሆን __ የሚያተኩሩትም በስፖርታዊ ብቃት/አተገባበር ብቻ ላይ ሳይሆን በአእምሮ ጤና፣ በግለሰብ ባህርይ አና አጠቃላይ ደህንነት ላይ ይሆናል። ስለደህንነት/ጤና ጉባኤው ተጨማሪ መረጃ ይህን በመጫን ያገኛሉ በተጨማሪም በቪዲዮ የተዘጋጀውን ቅንጭብ ማስተዋወቂያ እዚህ ይመልከቱ።
