ውድ ጓደኞቼ
ምክር ቤቱ በዚህ የመሀር ወቅት በጣም ብዙ በሆኑ የስራ ፕሮግራሞች የታጨቀ የጊዜ ሰሌዳ በመያዝ ወደ መደበኛ ጉባኤው ተመልሷል።
በዩኒቨርሲቲ ቡሊቫርድ ኮሪዶር መንገድ ላይ የሚገኘውን የትራፊክ ደህንነትን፤ የአካባቢ ጥበቃን/ዘላቂነትን እንዲሁም የእድገት እና የኢኮኖሚ ጉዳይን ለማሻሻል ያለመውን የዩኒቨርሲቲ ቡልቫርድ የኮሪደር ፕላንን ጨምሮ ብዛት ያላቸውን ጉዳዮችን በማንሳት ለመወያየት ተዘጋጅተናል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በመስከረም 10 በሞንትጎመሪ ብሌር ሃይስኩል እና በመስከረም 16 ደግሞ በምክርቤቱ የቢሮ ህንጻ ውስጥ የምሽት የህዝብ ችሎቶች ከ 7 ፒ ኤም ጀምሮ ይካሄዳሉ።
በተጨማሪም የካውንስሉ የኦዲት ኮሚቴ በአርብ መስከረም 26 ጀምሮ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፓብሊክ ስኩልስ የጀርባ ጥናት/ማጣራት ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በተመለከተ በዋናው ኢንስፔክተር የተዘጋጀውን ረፖርት /Office of Inspector General’s report on gaps in MCPS’ background check process/ እንዲሁም የተጠራቀሙ የሰራተኞች የጀርባ ጥናት ረፖርቶችንም በትመለከተ በበላይነት የማጣራት ችሎቶችን ያካሂዳል። ቀጣይ የትምህርት እና የባህል ክሚቴ ስብሰባዎችም እንዲሁ በመጪው መሀር የሚካሄዱ ይሆናል።
በዚህ የመሀር ወቅት በትምህርት ቤቶቻችን፣ በፍጆታ እቃዎች እና የሃይል ወጪዎቻችን ላይ ተጽእኖ የሚያደርጉ ነገሮች እንዲሁም የፐርፕል ላይን የቀላል ባቡርን የተመለከቱ ዜናዎችን እና ሌሎችንም ጉዳዮች እያነሳን የምንከልስ እና የምንወያይ ይሆናል።
በተጨማሪም ፤ በሶስተኛው አመታዊ የባኬትስ እና ቢትስ፤ ሲልቨር ስፕሪንግ ብሎክ የወጣቶች ፓርቲ /Buckets and Beats: Silver Spring Youth Block Party/ አርብ መስከረም 26 ከ 2-6 ፒ ኤም በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ በቬተራንስ ፕላዛ ውስጥ ስለሚዘጋጅ ይምጡና ይቀላቀሉን።
የቤዝቦል ውድድር የምናዘጋጅ ከመሆኑም በላይ የተለያዩ ጨዋታዎች፣ የአርት/ስነጥበብ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የወጣቶች ፕሮግራሞችን የተመለከቱ መረጃዎች እናዛጋጃለን። ለማጠቃለል ያህልም በቀጥታ የሚተላለፍ የዲጄ ሙዚቃ እና ለወጣት ተሳታፊዎችም ነጻ ምግብ እንዲሁም ለአሸናፊዎች የተለያዩ ሽልማቶችን እንሰጣለን። በባስኬት ጨዋታ ውድድር መሳተፍ የሚፈልጉ የመካከለኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችም በአክቲቭ ሞንትጎመሪ በሚለው ድረ ገጽ ላይ መመዝገብ ይችላሉ/sign up on Active Montgomery። እዛ እንደምትመጡ እና እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን!
ከሰላምታ ጋር
ኬት ስቴዋርት
የካውንስሉ ፕሬዚደንት
የስቴዋርት ቡድን/ቲም በዚህ ባለፈው የበጋ ወራት በማህበረሰቡ ውስጥ ከሚገኙ ጓደኖች እና ጎረቤቶች ጋር መገናነት ችሎ ነበር። ይህን በተመለከተ የሚከተሉት ዋና ዋና ቅንጭብ መረጃዎች ይመልከቱ፤
ሞንትጎመሪ ካውንቲ በዋስሽንግተን ዲ ሲ የተደረገው የብሄራዊ ልዩ ጥበቃ ጓድ ምደባ እና በፌዴራል መንግስቱ ቤት አልባ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸውን ቦታዎች ለማጽዳት የወጣው መመሪያ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን ተጽእኖ ለመቋቋም በዝግጅት ላይ ይገኛል። ውቴታማ የሆኑ እገዛዎችን የመስጠት እና ሰዎችን ሰብአዊ እና በክብር በመያዝ ላይ የተመሰረተውን ጥረታችንን በተመለከተ በባልቲሞር ሰን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ዘገባ እዚህ ይመልከቱ። ውጤታማ የሆኑ እገዛዎችን የመስጠት እና ለሰዎች ሰብአዊ እና ክብር የተሞላበት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያተኮረውን ጥረታችንን በተመለከተ በባልቲሞር ሰን ጋዜጣ /The Baltimore Sun/ ላይ የወጣውን ዘገባ እዚህ ይመልከቱ።
የኔ ቡድን በቅርቡ የጤና እና የማህበራዊ አገልግሎት እገዛ ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ያለቀጠሮ እየመጡ አገልግሎት እና እገዛ የሚያገኙበትን የታኮማ የምስራቅ ሲልቨር ስፕሪንግ የማህበረሰብ ማእከልን /Takoma East Silver Spring (TESS) Community Action Center/ ጎብኝቷል። በዳውን ታውን ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ሼፐርድስ ቴብል በተባለው መጠለያ ቦታም ምሳ ስናበላ ቆይተናል። ለሁለቱም ለነዚህ ድርጅቶች እኛን ተቀብለው በተለያየ ሁኔታ የማህበረሰብ አባላትን የሚመግቡበትን እና የሚያግዙበትን የተለያዩ ዘዴዎች እና አሰራር ስላሳዩን ልናመሰኛቸው ይገባል።
አለም አቀፍ እጽ ከመጠን በላይ የመጠቀም ግንዛቤ የመፍጠር ቀን /International Overdose Awareness Day / ላይ ከማህበረሰብ አባላት ጋር አብሬ በመገኘት እጾችን ከመጠን በላይ በመጠቀም ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ለማሰብ እና በማገገም ላይ ላሉትንም የምንሰጠውን ቀጣይነት ያለው እገዛ ለማረጋገጥ እና ቁርጠንነታችንም ለማሳየት ሞክረናል። ግንዛቤን የማሳደግ፣ እንዲሁም እጽን አላግባብ የሚጠቀሙት ላይ ያለውንም ማግለል ለመቀነስ የምንሰራውን ስራ እና የምናደርገውን ትብብር አጠናክረን እንቀጥላለን።
ከካውንስሉ የ2025 የሰመር ሰልጣኞች ቡድን ጋር ጥሩ የሆነ ውይይት ለማድረግ በቅቻለሁ። ይህ በየአመቱ በደሞዝ የሚሰጠው የሰልጣኞች ፕሮግራም ተማሪዎች በካውንቲው በሚገኙ የተለያየ ስብጥር ያላቸው ማህበረሰቦች እና በአካባኢያዊ የመንግስት አስተዳደር የአሰራር ሂደትን በተመለከተ ቀትተና የሆነ እና ጠቃሚ የስራ ልምድ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። የ2025 የበጋ ወራት ሰልጣኖች ፕሮግራምን የተመለከቱ ዜናዎች እዚህ ያገኛሉ ፤/Check out highlights from the 2025 Summer Fellows Program/.
የፌደራል መንግስቱ አስተዳደር በሚወስዳቸው ጭካኔ የተሞላባቸው እርምጃዎች እና ፖሊሲዎች ምክንያት በማህበረሰባችን ውስጥ በጣም ከፍተኛ የሆነ ግራ የመጋባት እና አሳሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች እንዳሉ እናውቃለን። በዚህ የበጋ ወራት ካሳ / CASA/ ከተባለው ድርጅት እና ከ100 በላይ ከምሆኑ የነጻ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመቀናጀት እና በአካባቢያችን የሚገኑ የንግድ ተቋም ባለቤቶች በማነጋገር የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት በሚመጡበት/በሚያጎበኗቸው ጊዜ እንዴት አድርገው እራሳቸውን ማዘጋጀት እና ሰራተኖቻቸውንም መጠበቅ እንደሚችሉ ግንዛቤ እና የተለያዩ የመረጃ ሃብቶችን ለመስጠት ጥረት አድርገናል። እንዴት መሳተፍ እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማግኘት ይችላሉ.
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የፕራይድ ማእከል አሁን ክፍት ነው። ለኤል ጂ ቢ ቲ ኪው ኤ ፕላስ / LGBTQIA+/ የማህበረሰብ አባላት የመረጃ ሃብቶችንና እገዛዎችን በአካል መጥተው የሚያገኙባቸውን ቦታዎች ማመቻቸት በጣም ጠቃሚ ነው። እዚህ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ለለኤል ጂ ቢ ቲ ኪው ኤ ፕላስ የማህበረሰብ አባላቶቻችን ሁሌም ጥብቅና እንቆማለን፤ እንዲሁም እገዛም እናደርግላቸዋለን። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የፕራይድ ማእከል በሳምንት 7ቱንም ቀን ለአገልግሎት ክፍት ነው!
የዋና የመክፈቻ ስነስርአቱን እዚህ ይመልከቱ ዋና የመክፈቻ ስነስርአቱን እዚህ ይመልከቱ እንዲሁም ተጨማሪ የበጎ ፈቃድ እድሎችንም እዚህ በመጫን መረጃ ያግኙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ስለመስጠት ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ እዚህ ማግኘት ይቻላል.
የኢትዮጵያን ብዝሃነት እና የዳበረ የባህል ቅርስ ለማክበር በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ የተካሄደው የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫል በጣም በጥሩ ሁኔታ አክብረናል። ይህ ቀን እውን እንዲሆን ለአደረጉት የሜሪላንድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማእከል እንዲሁም ሌሎች ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን።
ብዙ የፐርፕል ላይን መቆሚያዎች ያሉበትን ወረዳ ወክዬ የተመረጥኩ ሃላፊ እንደመሆኔ መጠን የፐርፕል ላይን ፕሮጀክቱ ወደፊት እየተጓዘ መሆኑን ስመለከት ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል። ለኛ ወረዳ ነዋሪዎች እና የንግድ ተቋማት ግምባታው ምን ያህል ከባድ ሁኔታ እንደፈተረባቸው ስለምናውቅ ለማህበረሰባችን ጥብቅና መቆማችንን እንቀጥላለን። በቅርቡም ከዚህ ጋር በተያያዘ እየተመዘገቡ ያሉትን አመርቂ ሂደቶች የማየት ታላቅ እድል ገጥሞኛል!
ያውቁ ኖሯል፤ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የ250ኛ አመት ክብረ በአሉን በ2026 እንደሚያከብር? በዚህ የበጋ ወር የሞንትጎመሪ ሂስትሪ ከተባለው ድርጅት ጋር አብሬ በመሆን የአይስ ክሬም ማህበራዊ ግብዣ በማድረግ አመት ሙሉ የሚቆየውን ክብረ በአል አስጀምረናል።
በሚቀጥለው ሳምንት የሞንትጎመሪ ካውንቲን 250ኛ አመት ክብረ በአል ለማክበር እሮብ መስከረም 17 በ 1፡00 ፒ ኤም ላይ ሮክቪል በሚገኘው የካውንስሉ የጽህፈት ቤት ህንጻ በምናዘጋጀው ልዩ የፓነል ውይይት በመሳተፍ የካውንቲው የኋላ ታሪክ እና የወደፊት ጉዞን በተመለከተ ሃሳብዎን እንዲሰጡ ተጋብዘዋል። ተጨማሪ መረጃ .
በሮክቪል የሚገኘው የኢሊ የአእምሮ ጤና ማእከል ጥራት ያለው የአእምሮ ጤና እንክብካቤ ለሁሉም እንዲዳረስ የሚሰራ አካታች እና በማህበረሰብ ላይ መሰረት ያደረገ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው። ኢሊ ማእከል የእያንዳንዱን ግለሰብ ክብር እና እንክብካቤ በሚያጎናጽፍ መልኩ ለግለሰቦች፣ ለጥንዶች፣ ለህጻናት እና ለቤተሰቦች እንዲሁም ለቤተሰቦች ህክምና/ ቴራፒ/ የሚሰጥ ማእከል ነው። ክሊኒኩ የተለያዩ እና ስፋት ያላቸው የአእምሮ ጤና ችግሮች ያላቸውን ሰዎች የማገዝ አቅም ያላቸው የስነልቦና አማካሪዎችን እና የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪዎችን ጨምሮ የተለያየ ስብጥር እና ፈቃድ/ ላይሰንስ/ ያላቸው የባለሞያዎችን የያዘ ድርጅት ነው። የሮክቪሉ ክሊኒክ በማእከሉ ውስጥ የስነጥበብ/ አርት/ ቴራፒ የሚሰጥ ሲሆን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕራይድ ማእከል ጋር በመተባበር የተለያዩ የእገዛ ግሩፖችን እና የማህበረሰብ የዮጋ ትምህርት ክፍለጊዜዎችን ከዚህ የመሀር ወቅት ጀምሮ መስጠት ይጀምራል።
በሃርትዉድ ፕሮግራም የሚገኘው የስነጾታ የጤና ክሊኒክ የተሻጋሪ ጾታ፣ ነን ባይናሪ፣ ነን ቾንፎርሚንግ ጾታ / gender nonconforming/ ኢንተርሴክስ አና ጾታቸውን ያልለዩ ግለሰቦችን ጨምሮ ከኤል ጂ ቢ ቲ ኪው ፕላስ ወጣቶች ፍላጎቶች ጋር የሚጣጣሙ የስርአተ ጾታ ማረጋገጫ ቴራፒ፣ የአጋዥ ቡድኖች እንዲሁም የክሊኒካል ምርመራዎችን ያካሂዳል። የስርአተ ጾታ የጤና ክሊኒክ ጊዜ ወስዶ ፍላጎትዎን ለመረዳት ጥረት የሚያደርግ እና ለቀጣይ የአእምሮ ጤና የህክምና ጉዞዎች ግላዊ የሆኑ ምክሮችን የሚሰጥ ክሊኒክ ነው። ክሊኒኩ የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው ፕላስ ጎረምሶችን እና ወጣት ልጆችን የሚያገለግል ክሊኒክ ነው።
የሃርትላንድ ፕሮግራምን የስርአተ ጾታ ጤና ክሊኒክ በበለጠ ለማወቅ እዚህ ላይ ይጫኑ.