ውድ ጓደኞቼ፣
ባለፈው ሳምንት የምክር ቤት አባል የሆኑት ጌብ አልቦኖዝ ከታህሳስ 1 2025 ጀምሮ ከምክር ቤት አባልነታቸው እንደሞለቁ አስታውቀው ነበር። እኛን የመሰሉ ታላቅ ችሎታ ያላቸው የስራ ባልደረባችንን በማጣታችን ምክር ቤቱ ቅር ቢለውም ይህን ውሳኔያቸውን ግን በመገንዘብ እናከብራለን።
ጌብ በምክር ቤት አባልነታቸው እና ቀደም ብለውም በበፊቱ የካውንቲው ስራ አስፈጻሚ አይዜያ ሌጌት ስር የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመዝናኛ መምሪያ የቀድሞ ዳይሬክተር ሆነው በሰጡት ታላቅ ህዝባዊ አገልግሎት ሞንትጎመሪ ካውንቲ አሁን ላለበት የተሻሻለ ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገዋል። እኚህ ግለሰብ እስካሁን ያአከናወኗቸው በርካታ የህግ ማርቀቅ ስራቸው ቁልፍ በሆኑ የህብረተሰብ ጤና እና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች፣ የህጻናት ቅድመ መደበኛ ትምህርት እና የህጻናት እንክብካቤ፣ እንዲሁም የከፋ ችግር ላለባቸው የካውንቲው ማህበረሰብ አባላት የሚጠቅሙ ግብአቶችን/ሃብቶችን በመስጠት ላይ ያተኮሩ ነበሩ። የጌብን ለኛ ማህበረሰብ ያላቸውን ጽኑነት ማሳያ የሚሆነው በተለይ የህዝባዊ የፖሊሲ ጉዳዮችን ለመቅረጽ እንዲሁም የጋራ መግባባትን ለማምጣት እና ዘላቂ ቅንጅቶችን ለመፍጠር የሚጠቀሙባቸው ብልህነት የተሞላባቸው ዜዴዎችና ስትራቴጂዎች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ጨዋነታቸው፣ ለሰው ያላቸው አዘኔታ እንዲሁም ያሳዩት የነበረው በአቋም የመጽናት ባህሪ በካውንስላችን ሲታወስ ይኖራል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ መተዳደሪያ ቻርተር ክፍል ቁጥር 106 እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ኮድ ክፍል ቁጥር 16-17 መሰረት የየአራት አመት ምርጫ ሊካሄድ አንድ አመት ሲቀረው ከታህሳስ 1 እለት ወይንም ከዛ በኋላ በካውንስሉ ውስጥ ክፍት የአባልነት ቦታ ከተፈጠረ ያ ቦታ አዲስ በሚሾም ጊዜያዊ አባል ይሞላል። የጌብ አልቦመዝን ቀሪ የስራ ዘመን ለመተካት አዲስ ጊዜያዊ የምክርቤት አባል የመሰየሙን ሂደት በምንጀምርበት በአሁኑ ወቅት ለካውንቲያችን ነዋሪዎች ማረጋገጥ የምንፈልገው የካውንስሉ ስራ አለምንም እክል ሳይቋረጥ እንደሚቀጥል ነው።
የሚሾመው የካውንስሉ ተተኪ አባል በሞንትጎመሪ ነዋሪ የሆነ እና ለመራጭነት በዲሞክራትነት ፓርቲ ስም የተመዘገበ መሆኑ የግድ ይላል፤ ይህም የሚሆነው የምክርቤት አባል አልቦሜዝ ከተመዘገቡበት የፖለቲካ ፓርቲ ጋር አንድ አይነት መሆን ስላለበትነው። በተጨማሪም ካውንስሉ በጊዜያዊነት የአባልነት ቦታውን ይዞ እንዲቆይ ለመሾም የሚፈልገው ሰው የካውንቲው ነዋሪ የሆነ፣ በበጀት አስተዳደር፣ በፓብሊክ ፖሊሲ እንዲሁም በህግ ማውጣት ስራ በቂ እውቀት ያለው መሆን ይኖርበታል።
በመሆኑም ለዚህ ክፍት ቦታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ሁሉ የማመልከቻ ደብዳቤ ወይንም የስራ ልምድ ማሳያ ሬዙሜያቸውን ለካውንስሉ የማቅረቢያ ቀነገደብ እስከ ህዳር 5, 2025 እስከ 5 ፒ ኤም ይሆናል። ማመልከቻችሁን በሚከተለው ኢሜይል አስገቡ፤ [email protected]. ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ይጫኑ.
ከሰላምታ ጋር፤
ኬት ስቴዋርት
የካውንስሉ ፕሬዚደንት
ከስምንት አሜሪካውያን አንዷ በህይወት ዘመኗ ውስጥ በአንድ አጋጣሚ የበሽታው ተጠቂ ሆና ልትገኝ እንደምትችል በሚታወቅበት በአሁኑ ወቅት የጡት ካንሰርን በተመለከተ ግንዛቤ መፍጠር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል። በተለይ በሽታው ከገፋ በኋላ በሚገኝባቸው እንዲሁም አስፈላጊውን ህክምና ለማግኘት በሚያጋጥማቸው ችግር ምክንያት ከፍ ባለ ሁኔታ የመሞት መጠን የሚታይባቸው የጥቁር እና የሂስፓኒክ ዝርያ ያላቸው በሽተኞች መሆናቸውን በምናይበት ጊዜ በጡት ካንሰር ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠሩ ስራ አስፈላጊነት በተለየ ሁኔታ ይታያል።
በ 2025 በዚህ ሃገር በቁጥር 317,000 ሴቶች እና 3,000 የሚጠጉ ወንዶች ወደ መላ ሰውነት ሊሰራጭ በሚችል አደገኛ በሆነ የጡት ካንሰር የመያዝ ፈተና እንደሚገጥማቸው እና 42,000 የሚሆኑ ሴቶችም በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሎ ይገመታል።
በመሆኑም ነዋሪዎች በነቃ ሁኔታ ሃኪሞቻቸውን ማማከር እና በመደበኛ በሆነ መልኩም የጡት ምርመራዎችን እንዲያደርጉ እናበረታታለን። በአንድ ላይ ሆነን ግንዛቤን በመፍጠር፣ ቀደም ብሎ በመመርመር እና በማወቅ፣ ላለባቸውም ፍቅርን በማሳየት ታካሚዎች ጤናቸው እንዲሻሻል እና በአጠቃላይም ከዚህ በሽታ ጋር የሚደረገውን ትግል መቀጠል እንደሚያስፈልግ መግለጽ እንወዳለን።
ካውንስሉ ሮክቪል በሚገኘው የካውንስሉ የጽህፈት ቤት ህንጻ ውስጥ ረቡእ ህዳር 5 ቀን በ7 ፒ ኤም ላይ አመታዊውን የወጣቶች የአዳራሽ ውስጥ ውይይት /ታውን ሆል/ እንደሚያዘጋጅ ይገልጻል። ይህ ዝግጅት ተማሪዎች እንዲወጡ እና ከአካባቢ ተወካዮቻቸው ጋር በመገናኘት በጣም የሚያሳስቧቸውን ጉዳዮች ደረጃ በደረጃ ለመወያየት እንዲችሉ ትልቅ እድል ይፈጥርላቸዋል። የተማሪዎቻችንን ፍላጎቶች እና ቀዳሚ ናቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች በተመለከተ መወያየት እና ማዳመጥ የካውንስሉን የፖሊሲ ማውጣት ስራ በአግባቡ እንዲወጣ ይረዳዋል። ለዚህ ተሳትፎአቸው ተማሪዎቹ ተጨማሪ የግልጋሎት መቀበያ የትምህርት ሰአታትን ያገኛሉ። ለበለጠ መረጃ እዚህ ይጫኑ።
ለአሽከርካሪዎች እና ለእግረኞች የተዘጋጀውን ጠቋሚ ሃሳብ በመውሰድና በመተግበር የሃሎዊን በአልን ደህንነት በተሞላው መልኩ ያክብሩ። አሽከርካሪዎች በሃሎዊን ክብር እለት ወይንም በዛ ሰሞን በዛ ያለ የትራፊክ መጨናነቅ እንደሚኖር ማወቅ ይገባቸዋል። ስለዚህ አሽከርካሪዎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችንን ማድረግ እና ለበአሉ በየመንደሩ የሚዞሩ የበአል ልብስ የለበሱ ህጻናት እና ኣዛውንቶች እንደሚኖሩ በመገንዘብ በደምብ መንገደኞችን ማስተዋል እና ተጠንቅቆ ማሽከርከር እንዲሁም ዝግ ብሎ መንዳት እና መንገድንም መቃኘት ይኖርባቸዋል። ሰክሮ የሚነዳ አሽከርካሪ ካስተዋሉ 9-1-1 በመደወል ያስታውቁ።
የግር መንገደኞችም ብቻቸውን ከመሄድ እንዲቆጠቡ፣ የመንገድ ደምቦችን እንዲያከብሩ እንዲሁም የትራፊክ ምልክቶችን እና መብራቶችን ልብ እንዲሉ እና እንዲሁም ሲሻገሩ የማቋረጫ ምልክቶች ባሉበት እንዲሻገሩ ይበረታታሉ። በጭለማ የሚወጡ ከሆነም በልብሶቻቸው እና ቦርሳዎቻቸው ላይ አንጸባራቂ ነገሮችን እንዲያደርጉ እና ብርሃን የሚያወጡ ከዘራዎችን እና የእጅ መብራቶችን ይዘው እንዲራመዱ ይመከራል።
የፓይክ ዲስትሪክት ጥምረት በነጻ የሚገባበትንና ባርክስ ኤንድ ብሪውስ ፌስቲቫል የተባለውን ፌስቲቫል ቅዳሜ ጥቅምት 25 ያከብራል። በእለቱ በሚቀርቡ የምግብ፣ የቀጥታ የመድረክ ሙዚቃ ዝግጅት እና በሃሎዊብን መዝናኛ ፕሮግራሞች ይደሰቱ! ውሻዎን (እና እራስዎንም) ልዩ የበአል ልብስ በማልበስ በኮስቲዩም/አለባበስ/፣ በሰልፍ ትርኢት እና በውድድር በመሳተፍ ጸሃይ ስትጠልቅ አካባቢ ለሚደረገውም የቤት ውጪ ፊልም ቀረጻ የራስዎን ወንበሮች እና ብርድልብሶች በማምጣት ይሳተፉ።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፓብሊክ ስኩልስ ተማሪ ልጆች ያሏቸው እና ለርዳታ ብቃታቸው የተረጋገጠ ቤተሰቦች አመቱን ሙሉ ለነጻ እና ቅናሽ ዋጋ ያላቸው ምግቦች ፕሮግራም (FARMS) ተጠቃሚ ለመሆን ማመልከት ይችላሉ። በአንድ ቤት ውስጥ አንድ ላይ ለሚኖሩ ሁሉም ተማሪዎች አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው ማስገባት የሚያስፈልገው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ለነዚህ ጥቅማጥቅሞች ለማመልከት ዛሬውኑ እዚህ ይጫኑ.
እርስዎ ወይንም ሌላ የሚያውቁት በመንግስት ስራ መዘጋት ምክንያት የተጎዳ ሰው ካለ እና የምግብ እገዛ የሚፈልግ ከሆነ በአጠቃላይ በመላው በክልሉ የተለያዩ የምግብ ማደያ ዝግጅቶች ስለሚገኙ መሄድ እና መጠቀም ይችላል። የካፒታል ኤሪያ የምግብ ባንክ በሞንትጎመሪ ካውንቲ በሚገኘው በ”ሶ ዋት ኤልስ” በሚባለው ጣቢያ (የሚገኝበት አድራሻ 6116 Executive Blvd., North Bethesda, MD 20852) በኩል አገልግሎት ስለሚሰጥ ሁሌ እሮብ ከ10 ኤ ኤም እስከ 11:30 ኤ ኤም የምግብ እደላ ይደረጋል። ምግብ ለመቀበል ነዋሪዎች የመንግስት የስራተኛ መታወቂያ ማሳየት ይኖርባቸዋል።
በነጻ የሚታደሉ የግሮሰሪ ውጤቶችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚፈልጉ ነዋሪዎች/ጎረቤቶቻችን የካፒታል ኤሪያ የምግብ ባንክን ድረገጽን /Capital Area Food Bank website/ መጎብኘት ይችላሉ። .
ለሁሉም ለሚያከብሩት ደስታ የተሞላው ዲዋሊ ይሁንላችሁ ብለናል! ይህ የብርሃናት ፌስቲቫል ደስታን፣ ብልጽግናን፣ እና ሰላምን ለርስዎ እና ለወዳጆችዎ ሁሉ እንዲያመጣላችሁ እንመኛለን። በዚህ በአል ላይ መኖሪያ ቤቶቻችንን እና ማህበረሰቦቻችንን በመብራት ስናንቆጠቁጥ በዛውም የደግነትን፣ የአንድነትን አና የተስፋ እሴቶችንም እንድናሰራጭ በማሰብ ይሁን።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ እና ብሎም በመላው ሜሪላንድ ለህዝባዊ አገልግሎት ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው በመሆኑ የፌደራል ተቀጣሪ ስራተኞቻችን ህዝባችንን እና ብሎም መላውን የአለም ማህበረሰብ ለመርዳት ላበረከቱት ማናቸውም አስተዋጽኦ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን። ከወርክ ፎርስ ሞንትጎመሪ ጋር በመቀናጀት የተፈጠረውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የፌደራል ሰራተኞች የስራ ማፈላለጊያ ማእከል ለመክፈት በተዘጋጀው የሪባን ቆረጣ ስነስርአት ላይ በመካፈሌ ኩራት ተሰምቶኛል። ይህ ከስራ የተፈናቀሉ የፌደራል ሰራተኞች ትርጉም ያለው ስራ እንዲያገኙ ለመርዳት ተብሎ የተቋቋመ በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነ የስራ ማፈላለጊያ ማእከል ነው። በማእከሉ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች ለማወቅ mobilize-montgomery.com የሚለውን ድረገጻቸውን ይጎብኙ።
በቅርቡ ከሜሪላንድ የህግ አውጪ የላቲኖ ኮከስ አባላት፣ ከተወካይ ሊቀመንበሩ አሻንቲ ማርቲኔዝ፣ ተወካይ ቴሬሳ ዉርማን እና ተወካይ ጂኔል ዊልኪንስ እና ከካሳ /CASA/ ጋር በመሆን የማህበረሰብ ውይይት አካሂደን ማህበረሰባችንን ለመጠበቅ፣ አካባቢያዊ አገልግሎቶችን ለማጠናከር እና እያንዳንዱ ነዋሪ መብቱን እንዲያውቅ ለማድረግ ለማስቻል እንዴት የስቴት እና የማህበረሰብ መሪዎች አብረው እየሰሩ እንደሆነ ለመወያየት ችለናል።
የምክር ቤት አባላት ኢቫን ግላስ፣ ክሪስቲን አና እኔም እራሴ አብረን በመሆን የካውንስሉን የአለማቀፍ የተውላጠ ስም አከባበር ቀን እውቅና ለመስጠት የተካሄደውን የእወጃ ስነስርአት መርተናል። ግለሰቦች የሚመርጡትን የራሳቸውን ተውላጠ ስም መጠቀም ማስቻል አንዱ እና መሰረታዊ የሆነ እነሱን የምናከብርበት እና ማንነታቸውንም እውቅና የምንሰጥበት መንገድ ነው። የአሁኑ የፌደራል አስተዳደር የኤል ጂ ቢ ቲ ኪው ፕላስ ማህበረሰብ አባላትን መብት እየገፈፈ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሞንትጎመሪ ካውንቲ ለሁሉም ነዋሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሁሉን ተቀባይ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ የግድ እና ወሳኝ ተግባር ነው። የሌሎችን መጠሪያ ተውላጠስም መጠየቅ እና ማክበር አካታች የሆነ ባህላችንን ለማስጠበቅ የሚረዳ ተግባር ነው። ስለተውላጠ ስም አጠቃቀም የበለጠ ለማወቅ ይህንን ድረገጽ ይጫኑ፤ https://pronouns.org/what-and-why። .
የ2025 የዲዛይን ስራ የላቀ ደረጃ ሽልማት አሸናፊዎችን እውቅና በመስጠታችን እጅግ በጣም ተደስቼ ነበር። ሽልማቶቹ የተዘጋጁት የሞንትጎመሪ ካውንቲን እጅግ በጣም የላቁ የስነህንጻ/ አርኪቴክቸር/፣ የከተማ ዲዛይን እና የመኖሪያቤት አሰራር በምሳሌነት የሚያሳዩ የልማት ፕሮጀችቶችን እውቅና ለመስጠት ነበር። የዚህን አመት አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። ከግሮስቬኖር ባቡር ጣቢያ ጎን የሚገኘው ፋይቭ ስኩዌርስ ዴቨሎፕመንት ፎር ስትራስሞር ስኩዌር የተባለው እጅግ በጣም ልዩ ለሆነ የከተማ ዲዛይን ስራው እውቅና ተሰጥቶት የግዌን ማርከስ ራይት የዲዛይን የላቀ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። በተጨማሪም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሊጂት የሂሳብ እና የሳይንስ ትምህርት ህንጻ ዲዛይነሮች እና አርኪቴክቶች ክብር እና እውቅና ሲሰጣቸው ሳይ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል። ሁለቱም እነዚህ ፕሮጀክቶች ዲስትሪክታችን እንዲለወጥ እና በሁሉም እድሜ ላሉ ነዋሪዎች የበለጠ ምቹ እንዲሆን አስችለዋል።
ተርንቴብል ካውንስሊንግ የሚባለው በበርተንስቪል የሚገኝና የጥቁር ዝርያ እና ቀለም ያላቸው ማህበረሰቦችን ያማከለ ልዩ የሆነ ‘ክዊር ጾታ ካላቸው ጋር የሚጣጣም፣ ግልጽ የሆነ እና የአእምሮ ጠና አገልግሎት የሚሰጥ ፕሮግራም ነው። የተርንቴብል የምክር አገልግሎት ባህልን ከግምት ውስጥ ያስገባ፣ ለህጻናት፣ ለአዋቂዎች፣ ለጥንዶች እንዲሁም ለቤተሰቦች በነጻነት ላይ ያተኮረ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ይሰጣል። ቡድኑ በስሜት መጫጫን፣ በአካላዊ/አ እምሯዊ ጉዳት መጨናነቅ በርቀት በኢንተርኔት/ ቨርቹዋል እና በአካል በመቅረብ በሚሰጡ ትምህርቶች፣ ከአንጎል እና ነርቭ ጋር የተያያዙ፣ ከስሜት እና ፍርሃት በሽታዎች፣ ከባህል ማንነት መጋጨት ጉዳዮችን፣ ከርስበርስ ኝኙነት ጋር የተገናኙ ችግሮች እና የህይወት ሽግግር ክስተቶች ጋር በተገናኘ ለደምበኞቹ እገዛ እና ትምህርቶችን ይሰጣል። የበለጠ ለማወቅ እና ከስልጠና ቀጠሮ ለማስያዝ የህን ድረገጽ turntablecounseling.com ይጎብኙ ወይንም በዚህ ኢ ሜይል [email protected] ይጠይቁ።