Skip to main content
County seal
Montgomery County Council Legislative Branch

Council Spotlight

Keeping Up With Kate - Nov. 6, 2025 (Amharic/አማርኛ)

Keeping Up With Kate - Amharic Language Newsletter Banner

ውድ ጓደኞቼ

የፌዴራል መንግስቱ ዝግ እንደሆነ በቀጠለበት እና እንደ ተጨማሪ የአመጋገብ እገዛ ፕሮግራም (SNAP) ጥቅማጥቅሞችን የመሳሰሉ ለህብረተሰብ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ፕሮግራሞች ህጋዊ ባልሆነ መልኩ በትራምፕ አስተዳደር እንዲቆሙ በመደረጉ በጣም የተባባሰ የማህበረሰብ እገዛ ፍላጎት የሚታይበት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰናል። በመሆኑም በአሁኑ ሰአት የተግባር እርምጃ መውሰድ ግድ ይለናል።

በዚህ ወሳኝ በሆነ ሰአት ይህን ክፍተት ለመሙላት እራሳችንን ዝግጁ በማድረግ ለነዋሪዎቻችን እና የማህበረሰቦቻችንን በመጨመር ላይ ያሉ ፍላጎቶችን ለማሟላት እየሰሩ ላሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና አጋሮቻችን ተጨማሪ የሆኑ የአካባቢ ሃብቶችን እና እገዛዎችን ማቅረብ ግድ ይለናል።

እነኚህን እያደጉ ያሉ ፍላጎቶች/ችግሮች ለመፍታት ይረዳ ዘንድ፣ ካውንስሉ በዚህ ሳምንት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች እና እየቀጠለ ባለው የፌደራል መንግስት መዘጋት ምክንያት ተጽእኖ የደሰባቸውን ለትርፍ ያልጠቋቋሙ አጋሮቻችንን ለማገዝ የሚረዳ የ7.75 ሚሊዮን ዶላር የህዝባዊ ድጋፍ ፓኬጅ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በዚህ የገንዘብ እገዛ ፓኬጅ ውስጥ አምስት የትኩረት ርእሶች ይገኛሉ፤

  • ለህጻናት እና ለወላጆች የሚሆን የምግብ አቅርቦት፤
  • ለማህበረሰብ አጋሮች የሚሰጥ እገዛ፤;
  • የመኖሪያ ቤት እገዛ፤
  • የሰብአዊ መብት ጥበቃ፤ እና
  • የኢኮኖሚያዊ እድገት .

ወደ በአል ወቅት ከመግባታችን በፊት ይህንን እገዛ ለማህበረሰባችን በተቻለ መጠን በቶሎ ለማቅረብ ይረዳን ዘንድ የህዝብ ውይይት ችሎት እና ድምጽ የመስጠት ሂደት በህዳር 18 እለት እንደምናካሂድ ለመግለጽ እንወዳለን።

ከሰላምታ ጋር፣

ኬት ስቴዋርት

የካውንስሉ ፕሬዚደንት

የካውንስል አባላት እና የማህበረሰብ አጋዦች የህዝባዊ አገልግሎት ድጋፍ የሰው ሃይል ፓኬጅን በተመለከተ ጋዜጣሚ መግለጫ ሲሰጡ

የቬትራንስ /የቀድሞ ጦር አባላት/ ቀን

ወደ ቬትራንስ/ የቀድሞ ጦር አባላት/ ቀን በአል አከባበር መቃረቢያ አካባቢ ሞንትጎመሪ ካውንቲ በተከታታይ የቬትራንስ ቀን ዝግጅቶችን የሚያዘጋጅ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች በአረንጓዴ መብራት እንዲሸበርቁ እና ለቬተራንስ እና ቤተሰቦቻቸው የሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶችን በተመለከተ የማስተዋወቅ ስራዎችም ይሰራሉ። በዚህ ሳምንት ካውንስሉ የቬተራንስን ቀን የሚያከብር እና በማህበረሰባችን ውስጥ የሚገኙትንም ቬተርራንስ እውቅና የሚሰጥ አዋጅ አቅርቧል። በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም አገራችንን ላገለገሉ በአሁን ጊዜ ላሉ እና ለቀድሞ የአሜሪካ የጦር እና የመለዮ ለባሽ አባላት ጥልቅ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ።  

የቬትራንስ /የቀድሞ ጦር አባላት/ ቀን

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ላለፉት ተከታታይ ሲያገኝ የነበረውን የትሪፕል ኤ ቦንድሬቴንግ /ደረጃን አሁንም ለ53ተኛ ጊዜ አገኘ

የካውንስሉ ፕሬዚደንት እንዲሁም የመንግስት የስራዘርፍ እና የፊስካል ፖሊሲ ኮሚቴ ሊቀመንበር እንደመሆኔ መጠን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትሪፕል ኤ ቦንድ ሬቲንግ /ሃላፊነት የተሞላው የክረዲት እና ፋይናንስ አጠቃቀምን የማስተግበር ችሎታን የሚለካበት ከፍተኛ ደረጃ/ እንደገና በማግኘቱ ኩራት ተሰምቶኛል። በተለይ በመላ ሃገሪቱ ካሉ ካውንቲዎች ውስጥ ሁለት ፐርሰንት የሚሆኑት ብቻ የዚህ ታላቅ እውቅና አሸናፊ መሆናቸውን በምናስብበት ወቅት ሞንትጎመሪ ካውንቲ የትሪፕል ኤ ቦንድ ደረጃን ማግኘቱ ካውንቲያችን ከነዚህ በሃገሪቱ ውስጥ እጅግ በጣም ምርጥ የበጀት አስተዳደር እና /ፊስካል/ ሃላፊነት አላቸው ከሚባሉት ተርታ መሰለፉን ያሳያል። የካውንቲው የረጅም ጊዜ የበጀት/ፋይናንስ አስተዳደር እስትራቴጂያዊ የአሰራር ስልትን የመጠቀም አሰራሩ ጤናማ ከሆነው የፋይናንስ መጠባበቂያ/ረዘርቭ አያያዛችን ጋር ተዳምሮ ካውንቲያችን የሚያጋጥሙ የበጀት ተግዳሮቶችን እንዲወጣ ያስቻለው ሲሆን የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን እና የወደፊቱንም እድገታችንን ለማሻሻል የሚረዱ ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንቶችንም እንድናስፋፋ አስችሎናል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትሪፕል ኤ ደረጃ / AAA bond rating/ መጎናጸፉን የሚያበስር ስእላዊ ፖስተር.

ለማህበረሰብ አማራጭ የሚያስገኝ የማጣጣት ስራ በተመጣጣን ዋጋ ለሚቀርብ እናንጹህ የሃይል ምንጭን ለማስፋፋት ይረዳል

ካውንስሉ በቅርቡ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተሻሻሉ ታዳሽ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የሃይል ምንጮችን ለማስፋፋት የሚረዳውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የማህበረሰብ የፍጆታ አጠቃቀም አማራጭ ማመጣጠኛ ፕሮግራምን / community choice aggregator/ የመመስረቻ ህግ አጽድቋል። የማህበረሰብ አማራጭ ማመጣጠኛ ፕሮግራሙ የአካባቢ የመንግስት መዋቅሮች ማህበረሰቦችን እና የንግድ ተቋማትን ወክለው የሃይል ግዢ እንዲያከናውኑ የሚያደርግ አሰራር ሲሆን የዚህ አላማም ለተጠቃሚዎች የፍጆታ ዋጋን ዝቅ ለማድረግ እና በአጠቃላይ ማህበረሰቦቻችንም አካባቢን የማይበክል /የአረንጓዴ / ሃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚረዳ ነው።

በ2021 የሜሪላንድ አጠቃላይ ጉባኤ ካውንቲው የሙከራ የማህበረሰብ አማራጭ ማመጣጠኛ ፕሮግራም /pilot Community Choice Aggregation program/ እንዲተገብር የፈቀደለት ሲሆን የዚህ ህግ መጽደቅም ነዋሪዎች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ሃይል አቅርቦት እንዲያገኙ እና ብሎም ወደፊት ንጹህ የሆነ የሃይል ምንጭ እንዲጠቀሙ ለማድረግ የተወሰደ የመጀመሪያ ደረጃ እርምጃ ነው። ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ይጫኑ

የማህበረሰብ አማራጭ ማመጣጠኛ ፕሮግራም እንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ በግራፍ የተደገፈ የመረጃ ፖስተር። ከ   አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን /EPA/ የተወሰደ.

የሞንትጎመሪ ካውንቲን ታሪክ የሚያወያይ ስብሰባ

ቅዳሜ ህዳር 8 በሞንትጎመሪ ኮሌጅ የጀርመንታውን ካምፓስ የሚካሄደውን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ ላይ የሚወያይ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። የዚህ አመት ስብሰባ የሚያተኩረው በሞንትጎመሪ ካውንቲ የ250 አመት ታሪክ ላይ ነው። እኔም “ሞንትጎመሪ ካውንቲ በ250ኛ አመት፤ ወደፊት ለመጓዝ የኋላውን መቃኘት”/ “Montgomery County at 250: Looking Back to Move Forward,”/ በሚልው ርእስ ላይ የተዘጋጀውን የፓነል ውይይት ከሜሪላንድ ዴሊጌት/ተወካይ ግሪጎሪ ዊምስ፣ ከዴሊጌት ሊልይ ዊምስ፣ ከደሊጌት ሊሊ ኪ፣ እና ሉዝ ቻቬዝ ጎንዛሌዝ ካር በመሆን እመራለሁ። ተጨማሪ መረጃ በማግኘት ይመዝገቡ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ አርማ እና የ250ኛ አመት አከባበር፣ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የታሪክ ስብሰባ፣ ህዳር 8, 2025, ጀርመንታውን ሜሪላንድ የሚል ጽሁፍ የያዘ ስእላዊ ፖስተር

ኬት በማህበረሰቡ ውስጥ፤

የወጣቶች የአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ

ከትምህርት ቦርድ የተማሪ ተወካይ አባል አኑቫ ማሎ፣ ከቦርድ አባላት፣ ከርእሰ ብሄር ዶ/ር ቶማስ ቴይለር እና ከሌኦችም ብዛት ካላቸው ተሳታፊ ተማሪዎች ጋር በአመታዊው የካውንስሉ የወጣቶች የአዳራሽ ውስጥ ውይይት በትናንት ማታ በመገኘታችን እጅግ በጣም ትልቅ ደስታን የሚሰጥ ነበር። ይህ ክስተት ተማሪዎቻችንን የሚያሳስቡ ወሳኝ እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ከራሳቸው ከተማሪዎቻችን አንደበት ለመስማት ልዩ የሆነ እድል አጎናጽፎናል። በብሄራዊ ደረጃ የሚወጡት ፖሊሲዎች በጣም የተወዛገቡ እና እኛን ለመከፋፈል የታለሙ ሆነው በተገኙበት ባሁኑ ወቅት የተማሪዎቻችን ድምጾች የወደፊት እጣችንን ለማሻሻል በምናደርጋቸው ጥረቶች ላይ እኛን አንድ የሚያደርጉን ነገሮች ላይ እንድናተኩር የሚያወሱ እና የሚያስገነዝቡን ናቸው።

Youth Town Hall

ዘ ባነር ሞንትጎመሪ የዜና አውታር

በቅርቡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ በተከፈተው አዲስ ዘ ባነር የተባለው የዜና ማእከል / The Banner’s new Montgomery County newsroom / በመምጣት የተቋሙ ዋና አስፈጻሚ ኤዲተር ከሆኑት ዙሪ ቤሪ ጋር ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የመድረክ ላይ ውይይት/ቃለመጠይቅ አድርጌ ነበር። እንደዚህ ያሉ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ የዜና ሽፋን የሚሰጡ በጣም የተካኑ የጋዜጠኞች ቡድን መኖራቸው ለኛ ታላቅ ደስታን ይሰጠናል!

የካውንስሉ ፕሬዚደንት ኬት ስቴዋርት በ ዘ ባነር ሞንትጎመሪ የዜና ማእከል ከዙሪ ቤሪ ጋር ሲወያዩ።.

የፌደራል ሰራተኞቻችንን መደገፍ

የሜሪላንድ ገዥ ዌስ ሙር በሞንትጎመሪ ካውንቲ የፌዴራል ተቀጣሪ ሰራተኞች ማስተባበሪያ እና የስራ ማፈላለጊያ ማእከል /Mobilize Montgomery Federal Workforce Career Center/ ተገኝተው ጉብኝት በማድረግ ከአካባቢ የስራ ሃላፊዎች እና ተጽእኖ ከደረሰባቸው የፌደራል ሰራተኞች ጋር የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት በማድረጋቸው በጣም ላመስገናቸው እወዳለሁ። በዚህ አጋጣሚም የካውንቲው እና የሜሪላንድ ስቴት መንግስታት በኩራት ስሜት አንድ ላይ በመሆን የፌደራል ሰራተኞችንን ለመደገፍ የቆሙ መሆናቸውን ለመግለጽ እና ለአጠቃላይ ማህበረሰባችንም በአንድነት የምንሰጠውን እገዛ እንደምንቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን።

የሜሪላንድ ገዥ ዌስ ሙር፣ የካውንስሉ ፕሬዚደንት ኬት ስቴዋርት ከካውንስል አባላት ጋር ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት

የአፕካውንቲ እና ሚድካውንቲ ሃብ ሃርቨስት የምግብ እደላ

የኔ ቡድን እና እኔ አንድ ላይ ሆነን በቅርቡ በሃርቨስት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ከሚገኘው ከሚድ ካውንቲ ሃብ ጋር በመሆን የምግብ እደላ ስራዎችን ለማገዝ ተገኝተን ነበር።

በተጨማሪም ከምክርቤት አባል ኤፕሪል ማክዴላኔይ ጋር አብሬ በመሆን የአፕ ካውኒ ሃብን 5ተኛ አመት ያከበርን ሲሆን በዛውም አፕ ካውንቲ ሃብ ለህዝብ ትምህርት ቤቶች በየሳምንቱ መጨረሻ የሚያድላቸውን የመክሰስ/ስናክ ፓኬቶች በማቀናበር አግዘናል።

በፌዴራል መንግስቱ አስተዳደር ህገወጥ እርምጃዎች እና በፌዴራል መንግስት መዘጋት ምክንያት ቤተሰቦች የተጨማሪ የምግብ እገዛ (SNAP) ጥቅማጥቅሞችን እያጡ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ድንቅ የሆኑት የማህበረሰብ አጋሮቻችን ለህጻናት፣ ለቤተሰቦች እና ለነዋሪዎች የምግብ እገዛን ለማድረግ እጅግ በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

የአፕካውንቲ እና ሚድካውንቲ ሃብ ሃርቨስት የምግብ እደላ

የሊንደን እና የኖርዝ ዉድሳይድ ሲቪክ ማህበር የሃሎዊን የደጋፊዎች ፌስቲቫል

በኖርዝ ዉድሳይድ እና ሊንደን ሲቪክ ማህበር የተዘጋጀውን የ2025 የሃሎዊን የበልግ ወቅት የአድናቂዎች ፌስቲቫል/ Halloween Fall Funfest 2025/ ላይ አብሬ በመገኘቴ ደስ ብሎኛል። ለሁሉም በቦታው ለተገኙት እንዲሁም ከበአሉ ጋር የሚሄድ አለባበስ  በመልበስ ይህን ፌስቲቫል በማዘጋጀት ለተባበሩ ሁሉ ምስጋና እናቀርባለን!

የሊንደን እና የኖርዝ ዉድሳይድ ሲቪክ ማህበር የሃሎዊን የደጋፊዎች ፌስቲቫል

የአእምሮ ጤና ኮርነር፤

አሜሪካን ዳይቨርሲቲ ግሩፕ

አሜሪካን ዳይቨርሲቲ ግሩፕ (ADG) የተባለው የአሜሪካ የብዝሃነት ቡድን የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን ለሌላቸው ሰዎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያችላቸውን ብቃት ለመገንባት የሚያስችል የአእምሮ ጤና ምክር እና ቴራፒ/ህክምና አገልግሎት ፕሮግራም መጀመሩ ታውቋል። የምክክር ክፍለጊዜያቱ በየሳምንቱ ቅዳሜ ቅዳሜ የሚካሄዱ ሲሆን ወጥነት ያለው እና አጋዥ የሆነ የእድገት አውድ እንደሚፈጥሩም ይጠበቃል። በውይይት ክፍለጊዜዎቹ ለመካፈል ስልክዎን [email protected] በሚለው ኢ ሜይል ይላኩ። ለመስተናገድ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል።

የአሜሪካን ዳይቨርሲቲ ግሩፕ አርማ