Skip to main content

Press Releases - County Council

For Immediate Release: Thursday, November 21, 2024

ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት እና የዋና ሥራ አስፈፃሚው /ቤት

የአካባቢው አመራር አባላት የነዋሪዎችን ተሳትፎ ያበረታታሉ

በአስቸኳይ የሚሠራጭ - ሰኞ ኖቬምበር 25, 2024

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንድሩ ፍሪድሰን፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ኬይት ስቱዋርት፣ የምክር ቤት አባላት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚው ማርክ ኤርልሪሽ የማህበረሰብ አገልግሎት አቅራቢ እና ነዋሪዎች ''አገልግሎት በሕብረት '' United in Service” እና የማህበረሰብ ድጋፍ ትርዒት እሁድ ዲሴምበር 8, 2024 ሮክቪል በሚገኘው የኤግዜክዩቲቭ ጽህፈት ቤት ሕንጻ ከቀኑ 1 ኤም እስከ 4 .ኤም ስለሚካሄድ እንድትሳተፉ ጋብዘዋል። በፌዴራል ማእቀፍ ውስጥ ሊመጡ የሚችሉ ለውጦችን በማሰብ ነዋሪዎች ሊኖሯቸው የሚገቡ የመረጃ አይነቶች በአግባቡ ይደርሳቸው ዘንድ የሚያረጋግጥ ሁኔታን የሚያመቻች ይሆናል።

 

ይህ ከክፍያ ነፃ የሆነ የማህበረሰብ መረጃ ማስጨበጫ መርሃግብር ነዋሪዎች ፈርጀ-ብዙ መረጃ ማለትም የማህበረሰብ ጤናና ደህንነት የሥነ-ተዋልዶ መብት፣ የሥራና የሙያ ሥልጠና አማራጮች፣ በአጠቃላይ ለነዋሪዎች መብታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ የሚቀርቡ አገልግሎቶችን የሚያሳውቅ መድረክ ይሆናል። ነዋሪዎች መብቶቻቸውን እንዲገነዘቡ የኮንትራት ሥራ ክህሎት ስልጠና  እና የተለያዩ መረጃዎች ይቀርቡበታል።

 

''በዋሽንግተን ዲሲ የሚነገርም ሆነ የሚፈጠር ማንኛውም ሁኔታ ጥረታችንን የሚጋፋና የማህበረሰባችንን አገልግሎት የሚቀናቀን እንዲሆን ፈጽሞ አንፈቅድም '' ይላሉ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አንድሩ ፍሪድሰን። '' ማህበረሰባችንን ከሚያግዙ ተቋማትና ከነዋሪው ጋር በጥምረት በመቆም ሞንትጎመሪ ካውንቲ እንደሁልጊዜውም ለመኖር የተመቸ፣ ነዋሪዎቹም ሠርተው በየእምነታቸው የታነፁ ቤተሰቦች አስተዳድረው የሚኖሩበት መሆኑን እናረጋግጣለን። ''

 

ምክትል ፕሬዝዳንት ኬይት ስቱዋርት በበኩላቸው እንደገለፁት ''በፌዴራል አስተዳደሩ በኩል አዲስ ለውጥ የሚጠበቅ ቢሆን የኛ ቀዳሚ ትኩረት የማህበረባችን ምቾት ሳይጓደል መቀጠሉ ላይ ነው'' የኛ ኃላፊነት ነዋሪውን ለማገዝ ምን አገልግሎት እንደምናቀርብለት ማሳወቅና በማንኛውም ጊዜ እገዛ ሲፈልግ ከጎኑ መሆናችንን ማረጋገጥ ነው'' ብለዋል ኬይት ስቱዋርት

 

የካውንቲው ኤግዚኪዮቲቭ ማርክ ኤርልሪሽ በበኩላቸው '' በፌዴራሉ አስተዳደር ምንም ዓይነት ለውጥ ቢመጣ የሞንትጎመሪ ነዋሪዎች ከበፊቱ አገልግሎት ምንም ሳይጎድልባቸው እንዲቀጥሉ በዚህ ዝግጅት ላይ የምናረጋግጥበት አጋጣሚ ይፈጠራል'' ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤልሪክ።

 

በህብረት መቆምና ነዋሪዎቻችንን ማገልገል የማያወላውል አቋማችን መሆኑን በዚህ ዝግጅት ለመግለጽ እንሻለን '' የዋና ሥራ አስፈፃሚው ቃል ነው።

 

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ  የመርጃ አቅራቢ ወይም የማህበረሰብ አጋር ከሆኑ እና መረጃን እና ግብዓቶችን ከነዋሪዎች ጋር ለማጋራት ወይም ጥያቄ ካሉዎት እባክዎን ያነጋግሩ።

[email protected].

 

የአስፈጻሚው ቢሮ ህንፃ በሮክቪል 101 ሞንሮ ጎዳና ላይ ይገኛል። የማህበረሰብ የመርጃ ትርኢት በካፍቴሪያው ውስጥ ይካሄዳል።

 

ነፃ የመኪና ማቆሚያ በካውንስሉ /ቤት ህንፃ ጋራዥ በሞንሮ ጎዳና እና ፍሊት ጎዳና ወይም በምስራቅ ጀፈርሰን ጎዳና (መንገድ 28) እና ሞንሮ ጎዳና ጥግ ላይ በሚገኘው የዳኞች ማቆሚያ ቦታ ያለው ጋራዥ ይገኛል

 

በሜትሮ ቀይ መስመር ላይ ያለው የሮክቪል ጣቢያ ለኮሚኒቲው የመርጃ ትርኢት በጣም ቅርብ የሆነ ማቆሚያ ነው።



Release ID: 24-418
Media Contact: Lucia Jimenez 240-777-7832