ውድ ጓደኞቻችን፣
የትራምፕ አስተዳደር በአሁኑ ጊዜ እየወሰዳቸው ባሉ እና ቤተሰቦችን፣ ጤናችንን እንዲሁም ደህንነታችንን እና መተዳደሪያችንን በሚፈታተኑ ውሳኔዎች ምክንያት ስጋት ያደረባቸው ነዋሪዎች በላኳቸው መልእክቶች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ቢሮዎቻችን ተጨናንቀው ሰንብተዋል። የፌደራል፣ የስቴት እና የካውንቲ አመራር እንደመሆናችን መጠን እኛም ከነዋሪዎቻችን ጋር በጋራ የምንቆም መሆናችንን እየገለጽን የዲሞክራሲ እሴቶቻችንን ለመጠበቅ እና ለማህበረሰቡቻችን እጅግ በጣም አስፈላጊ እና አብይ የሆኑ ድጋፎችን መስጠታችንንም እንደምንቀጥል ለማሳወቅ እንወዳለን።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ነዋሪዎችን የሚያሳስቡ እና ተጽእኖ ኢፈጥሩ የሚችሉ ብዙ ነገሮች እና ለውጦች እንዳሉ በእጅጉ እንደምንረዳ እና የነዋሪዎቻችንን መሰረታዊ መብቶች ለማስጠበቅም በቁርጠኝነት እንደምንቆምም ለማረጋገጥ እንወዳለን። በተጨማሪም ሁሉንም የማህበረሰባችንን አባላት በጋራ ለመደገፍ እና ለማገልገል እንዲሁም የእያንዳንዱን ነዋሪ ክብር እና ሰብአዊነት ለማስጠበቅ ጸንተን እንደምንሰራ ለመግለጽ እንገልጻለን።
በዚሁ አስተዳደር አማካኝነት የሚወሰዱ ኢ-ህገመንግስታዊ እና ህጋዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች ላይም እርምጃ መውሰዳችንን የምንቀጥል ሲሆን መሰረታዊ መብቶችንን ለማስጠበቅ እና የራሳችንንም የማስተዳደር ስልጣን ለማስጠበቅ እና ለማረጋገጥ በጋራ እንደምንታገል ለማሳወቅ እንወዳለን።
በዚህ በአሁኑ ፈታኝ እና ግራ በሚያጋባ ጊዜ ነዋሪዎቻችን ሊወስዷቸው የሚችሉ ሶስት እርምጃዎች፤ መብትን ማወቅ፣ ማግኘት ስለሚችሏቸው አገልግሎቶች ማወቅ እንዲሁም እገዛ ለማግኘት መጠየቅ የሚሉት ይገኙበታል። በዚህ ረገድም ከዚህ በታች የተጠቀሰው መረጃ ሊያግዝ ይችላል።
በነዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያት በጋራ መስራታችንን የምንቀጥል ሲሆን የማህበረሰባችን አባላትም መረጃን ለማግኘት እና ለማወቅ መጣር እንዲሁም እርስ በእርስም መደጋገፍ እንደሚኖርባቸውም እንመክራለን። በመሆኑም በመተጋገዝ እና አብረን በመስራት የአካታችነት፣ እርስ በእርስ የመደጋገፍ እና የመተዛዘን ባህላችንን በማጉላት ማህበረሰባችን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተመራጭ እንዲሁም ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለአምልኮ እና ለቤተሰብ እድገት ተስማሚ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ይኖርብናል/።
በቀጣይነት ምን ሊከሰት እንደሚችል ማወቅ ባንችልም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሜሪላንድን እሴቶች እና ቃልኪዳኖችን ለማስጠበቅ እና ለማጠናከር አቅማችን የሚችለውን ሁሉ እናደርጋለን።
አገልግሎት እየሰጡ ያሉ፣
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮንግሬስ ልኡካን
ዩ.ኤስ ሴኔተር ክሪስ ቫን ሆለን
ዩ.ኤስ ሴኔተር አንጄላ ኦልሶብሩክስ
ዩ.ኤስ ኮንግረስማን ጄሚ ራስኪን
ዩ.ኤስ ኮንግረስማን ግሌን ሌቪ
ዩ.ኤስ ኮንግረስውመን ኤፕሪል ማክ ክሌን ዴላኒ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእስቴት ልኡካን
የስቴት ሴኔት ሊቀመንበር ቤንጃሚን ክራመር
የስቴት ፓርላማ ሊቀመንበር ጁሊ ፓላኮቪች ካር
የምንትጎመሪ ካውንቲ ምክርቤት/ ካውንስል
የካውንስሉ ፕሬዚደንት ኬት ስቴዋርት
ምክትል ፕሬዚደንት ዊል ጃዋንዶ
የኮንግረስ ልኡካኖቻችን ካውንቲያችንን እና ስቴቱን በአሜሪካ ምክር ቤት ወክለው የተቀመጡ ናቸው። የተወካይዎን ስም ለማወቅ እና እንዴት እንደሚያገኟቸው ለመለየት ይህን ይጫኑ፤ Find your representative and how to contact them.
እርስዎን ለመርዳት ሴኔተር ቫን ሆለን እንዴት እየታገሉ እንደሆነ ለማወቅ ይህን here በመጫን የዜና መጽሄቱን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
እንዴት ልናግዝዎ እንደምንችል:
ከፌዴራል መስሪያ ቤት ጋር የተገናኘ እርዳታ
የፌዴራል መስሪያ ቤትን የአሰራር ሁኔታ ለመገንዘብ እገዛ ይፈልጋሉ? የገጠመዎትን ማናቸውም ችግር ለመፍታት ወይንም ፍላጎትዎን ለማሟላት የሚረዳ አስፈላጊ መረጃ ለመስጠት የርስዎ የኮንግሬስ ተወካዮች ዝግጁ ናቸው። በፌዴራል መስሪያ ቤትም ሆነ በፈዴራል መስሪያ ቤት ቁጥጥር ስር ካለ አካል ጋር በተያያዘ ጉዳይ እገዛ ማድረግ እንችላለን። ይህም ከኢሚግሬሽን፣ በፈዴራል ደረጃ የጡረተኞች ጥቅማጥቅሞች፣ የሰራተኞች አስተዳደር ቢሮን የሚመለከት እና የስራ እድል እኩልነት ኮሚሽን (EEOC) ጋር የተያያዙ ጉዳዮችንና ሌሎችንም ያካትታል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልኡካኖቻችን ቦእስቴት ደረጃ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት በጣም ጠቃሚ እና ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልኡካኖችን ማንነት ለማወቅ / Meet the Montgomery County delegation/ የሚለውን በመጫን ማግኘት የሚቻል ሲሆን የስቴት ተወካዮቻችሁን ለመፈለግ ደሞ ይህን መስተጋብራዊ የካርታ ድረገጽ ይጫኑ፤ interactive map to find your state representatives. ከሜሪላንድ ስቴት መስሪያ ቤቶች ጋ የተያያዙ ጉዳዮችንም በተመለከተ እገዛ ማድረግ እንችላለን።
እንዴት ማገዝ እንደምንችል፤
ለፌዴራል ሰራተኞች እና ኮንትራክተሮች የሚያግዙ ሃብቶች
የሜሪላንድ የሰራተኞች ጉዳይ መስሪያቤት /The Maryland Department of Labor/ በፌደራል መንግስት ለውጥ ምክንያት ለተጎዱ የፌዴራል ሰራተኞች እና ሌሎችም ባልደረቦች እንደ የስራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማጥቅሞች፣ የሙያ ማጠናከሪያ መመሪያ እና ሌሎችንም የተመለከቱ የመረጃ ሃብቶችን በመስጠት እገዛ ያደርጋል። ይህን ይጫኑ https://labor.maryland.gov/federalworkers/።
በራሳቸው ጥፋት ባልሆነ ምክንያት ለስራ አጥነት የተጋለጡ ሰራተኞች እና በፌደራል ደረጃ በተደረገ ለውጥ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች ሰራተኞች ከሜሪላንድ የስራ አጥነት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ፤ Visit the Maryland Division of Unemployment Insurance to learn more። ከዚህ ጋር በተገናኘ ሂደቱን በማስረዳት ረገድ የሜሪላንድ ስቴት ተወካዮች ሊያግዙ ይችላሉ።
የስቴት ፕሮግራሞችንና አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚደረግ እገዛ
በሜሪላንድ እስቴት አማካኝነት የሚሰጡ ፕሮግራሞችንና አገልግሎቶችን በተመለከተ ከስቴት ተወካዮች እገዛ ለማግኘት ይህን መስተጋብራዊ ካርታ ይጠቀሙ ፤ interactive map to find and contact your state representatives።
የዲስትሪክት እና የአጠቃላይ የስቴት ተወካይ የምክር ቤት አባላት / at-large Councilmembers/ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ኤጀንሲዎች እና መምሪያዎች አማካኝነት የሚሰጡ አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞችን በመፈለግ እና በማግኘት ረገድ ትልቅ እገዛ ሊያደጉልዎት ይችላሉ። የካውንስል አባላትን ለማግኘት ይህን መስተጋብራዊ ካርታ ይጠቀሙ፤ Find your Councilmember using this interactive map።
እርዳታ የምናደርግባቸው መንገዶች፤
የስደተኛ/ኢሚግራንት ማህብረሰባችንን መጠበቅ
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ጊልክሪስት የኢሚግራንት የሃብት ማእከል Gilchrist Immigrant Resource Center በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ እና /family preparedness information/ የቤተዘብ ዝግጁነት መረጃን ጨምሮ መብትዎን ለማሳወቅ የሚረዱ መረጃዎች አዘጋጅቶ አቅርቧል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርትቤቶች (MCPS) ለተማሪዎች እና ለወላጂቻቸው የተላለፈ ዲስትሪክት አቀፍ ፖሊሲ አለው። ኤም ሲፒኤስ የእያንዳንዱ ህጻን የኢሚግሬሽን ሑኔታ ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ተማሪዎች በእኩልነት አገልግሎት በመስጠት ሁሌም ደህንነቱ የተጠበቀ እና እንግዳ ተቀባይ ተቋም እንደሆነ ይቀጥላል። የኢሚግሬሽን አስፈጻሚዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመጡ ምን ማድረግ እንደሚገባ የሚገልጽ እና ሌሎችንም መረጃዎች ኤምሲፒ ኤስ ያቀረበ ሲሆን በዚህ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል፤ what happens if immigration law enforcement officers come to a school, እና ተጨማሪ መረጃዎችም በ helpful information for families ድረገጽ ይገኛሉ።
ለኤል,ጂ,ቢ,ቲ,ኪው ፕላስ /LGBTQ+/ ማህበረሰቦቻችን የሚሰጥ ድጋፍ
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕራይድ /Montgomery County Pride’ የተባለው ድርጅት ለኤል,ጂ,ቢ,ቲ,ኪው ፕላስ ‘መብታችሁን እወቁ ‘ የተባለ እና ሌሎችም እጅግ በጣም ወሳኝ የሆኑ የጤና እና የማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚጠቁም የመረጃ ሃብት ድረገጽ /resource page/ አቅርቧል።
የምግብ እገዛ አገልግሎቶች/ሃብቶች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ በመደበኛነት የምግብ እደላ ፕሮግራሞችን የሚያደርግ ሲሆን በዚህም አማካኝነት በነጻ ወይንም በቅናሽ ምግቦችን በትምህርት ቤት የሚያቀርብ ሲሆን ለእድሜ ባለጸጎች/ሲኒየርስ/ እና ለሌሎች የትራንስፖርት ችግር ላለባቸው እና ምግብ ለማዘጋጀት እርዳታ ለሚፈልጉ የማህበረሰብ አባላትም የተዘጋጀ ምግብ እና ከግሮሰሪ ገዝቶ የማቅረብ አገልግሎት አማራጮችን ያቀርባል።
የምግብ እደላ የጊዜ ሰሌዳ እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በሞንትጎመሪ ካውንቲ የምግብ ጉዳዮችና መቋቋሚያ ቢሮ ድረገጽን Office of Food Systems Resilience በሚለው ይጎብኙ።
የአእምሮ ጤና እገዛ
እርስዎ ወይንም ሌላ የሚያውቁት ሰው አደጋ ላይ እንደሆነ ካወቁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአደጋ ማእከል /Montgomery County Crisis Center/ በቀን 24 ሰአት እና በአመት 365 ቀናት ነጻ የአደጋ መቋቋሚያ አገልግሎት እንደሚሰጥ ልብ ይበሉ። አገልግሎቶቹን ለማግኘት በስልክ ቁጥር (240) 777-4000 በመደወል ወይንም በአካል 1301 Piccard Dr. Rockville /ሮክቪል/ በመምጣት ማግኘት ይቻላል። (ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግም)።
ሌሎች በካውንቲው የሚሰጡ የእገዛ አገልግሎቶችን 311 በመደወል ወይንም Council’s community resource webpage የሚለውን የካውንስሉን ድረገጽ በመጎብኘት ማግኘት ይቻላል።